Get Mystery Box with random crypto!

#የዛሬ (ሰኔ 4/2014) በነገው ዕለት የዓለምዓቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር መዝጊያ ፕሮግራም | TIKVAH-MAGAZINE

#የዛሬ (ሰኔ 4/2014)

በነገው ዕለት የዓለምዓቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር መዝጊያ ፕሮግራም በስታድየም ይደረጋል ተብሎ የተገለጸ ቢሆንም አንዳንድ ዶክመንቶች በጊዜ ባለማሟላታቸው እንዲሁም አዲስ አበባ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት የተቆፋፈረና ምቹ ባለመሆኑ የመዝጊያው ፕሮግራም ከስታዲየም ውጪ እንዲደረግ ተወስኗል። ከሀገሪቱ ጫፍ እስከ ጫፍ ወደ አ አበባ እየመጣችሁ ያላችሁ እንግዶች እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይህንን በመገንዘብ ሳትለፉ ባላችሁበት እንድትከታታሉ አዘጋጆቹ ጠይቀዋል።

የትምህት ሚኒስቴር ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆኖ ራሱን የሚያስተዳድር ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን አስታውቋል፡፡ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ÷ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲን ተከትሎ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ከሁለት እስከ አምስት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በሂደት ወደ ነጻ ዩኒቨርሰቲነት እንደሚቀየሩ ተናግረዋል።

እስካሁን ድረስ ከፍተኛ ነው የተባለ የሰብዓዊ ድጋፍ ኮንቮይ ትግራይ መግባቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) አሳውቋል። ድርጅቱ በዚህ ሳምንት 308 ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ መግባታቸውን ያመለከተ ሲሆን 800 ሺህ ለሚደርሱ ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ በቂ ምግብ የያዙ ናቸው ብሏል።

የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ሴካፋ የሴቶች ሲንየር ሻምፒየን ሺፕ በዩጋንዳ ሲካሄድ ኢትዮጵያ ከ ታንዛኒያ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ 2 - 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች። የሉሲዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ቱሪስት ለማ እና ብዙአየሁ ታደሰ አስቆጥረዋል።

በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩና ቀሪ ትምህርታቸውን በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ያጠናቀቁ 417 ተማሪዎች ዛሬ ተመርቀዋል። ተመራቂዎቹ በተለያዩ መስኮች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን 164ቱ ሴት ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የሜዳውን ጨዋታ ለማድረግ በማላዊ ባደረገው ቆይታ ግብፅ ላይ ካስመዘገበው ጣፋጭ ድል በተጨማሪ ከወጪው በላይ ገቢ በማስገባት ትርፍ ማስመዝገብ ችሏል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከግብፅ ጋር ባደረገው ጨዋታ 68 ሺህ ዶላር የተጣራ ገቢ ማግኘቱ ነው የተገለጸው።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot