Get Mystery Box with random crypto!

#የዛሬ (ግንቦት 3/2014) ኢትዮጵያ የሶማሌላንድ መንግስት በበርበራ ወደብ ላይ የባለቤትነት | TIKVAH-MAGAZINE

#የዛሬ (ግንቦት 3/2014)

ኢትዮጵያ የሶማሌላንድ መንግስት በበርበራ ወደብ ላይ የባለቤትነት መብትን አስመልክቶ ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ባለመቻሏ በበርበራ ወደብ ላይ ያላትን የ19 በመቶ ድርሻዋን ማጣቷን ተሰምቷል። የሶማሌላንድ ገንዘብ ሚኒስቴር እንደገለጸው ከቅድመ-ሁኔታዎች አንዱ ለወደቡ ግንባታ የገንዘብ መዋጮ ሲሆን ኢትዮጵያ ይህን ማድረግ ሳትችል ቀርታለች። የኢትዮጵያ መንግስት መረጃውን እያጣራ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተፈጸሙ በተባሉ ጥሰቶች ላይ ተመድ [UN] ሊያደርገው ያቀደው #ተጨማሪ ምርመራ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። በኢሰማኮ እና በተመድ የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የጋራ ሪፖርት ላይ የተመላከቱ ምክረ ሀሳቦችን ለመተግበር መንግስት ዝግጁ ነው ብለዋል። ነገር ግን በተመድ በኩል ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ የሚደረገው አካሄድ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኔ 3/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞ የዋስትና ጥያቄ ላይ ብይን የሰጠ ሲሆን በ30,000 /ሰላሳ ሽህ ብር/ ዋስትና #እንዲወጡ አዟል። ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላም ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ከእስር መለቀቃቸውን ቤተሰቦቻቸው አሳውቀዋል።

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት፤ በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል የሚባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲመረምር ያቋቋመውን ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ኮሚሽን በሊቀመንበር ሲመሩ የነበሩት ፋቱዋ ቤንሱዳ በብሪታኒያ እና በጋራ ብልጽግና (ኮመን ዌልዝ) አገራት የጋምቢያ ከፍተኛ ኮሚሽነር ሆነው በሀገራቸው መንግስት በመሾማቸው ምክንያት ከኃላፊነታቸው #መልቀቃቸውን አሳውቀዋል። በምትካቸው ኬንያዊቷ የህግ ባለሙያ #ካሪ_ቤቲ_ሙሩንጊ ተሹመዋል።

ቴሌግራም አሁን #በነፃ እየሰጠ ያለው አገልግሎት #እንደተጠበቀ ሆኖ ተጨማሪ አገልግሎት የሚሰጥበትን እና ድርጅቱም ገቢ የሚያገኝበትን በክፍያ የሚሰጥ " ቴሌግራም ፕሪሚየም " የተሰኘ አገልግሎት በዚህ ወር ያስጀምራል።

በደሴ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ስልክ አምባ ትምህርት ቤት በተለምዶ ሚካኤል ጀርባ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በነበረ የቆሻሻ ማቃጠያ ቦታ ከቆሻሻ ማቃጠያው የወዳደቁ የቁራሊዬ እቃዎችን እየሰበሰቡ የነበሩ ሶስት #የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች የከባድ መሳሪያ ተተኳሽ ፈንድቶ በሶስቱም ላይ ጉዳት አድርሷል። ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎችም በአሁኑ ሰአት የህክምና አገልግሎት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot