2022-06-16 23:26:48
#የዛሬ (ሠኔ 9/2014)
#የዶሮበሽታ
በኢትዮጵያ "የዶሮ በሽታ" መከሰቱን ተከትሎ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰቢያ ተላልፏል። የኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያሳየው የዶሮ በሽታ በኦሮሚያ እና አዲስ አበባ ከተማ ተከስቷል።
በሽታው እስካሁን በቢሾፍቱ፣ በአቃቂ ቃሊቲ እና ኮልፌ ክፍለ ከተሞች መከሰቱን እና ከ50 ሺህ በላይ ዶሮዎች ሞተዋል። በሽታው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይሰራጭ ልዩ ክትትል በመደረግ ላይ መሆኑንና የሞቱ ዶሮዎችንም ሳይንሱን በጠበቀ መንገድ በማስወገድ ላይ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ በሽታው የተከሰተባቸው አርቢዎች ገበያ ባለማውጣት እና የሞቱ ዶሮዎችን በመቅበር እንዲሁም በሽታው የተከሰተባቸውን የእርባታ ጣቢያዎች ኬሚካል መርጨት ይገባል ብለዋል።
||
#አጣዬ
ከዚህ ቀደም በተፈፀመባት ጥቃት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የወደመችው አጣዬን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገው ጥረት ደካማ መሆኑን እና ለዚህም ትኩረት የሚሰጥ የመንግስት አካል ማጣቷ ተነግሯል። ፌዴራል እና የክልል መንግስት ከተማውን እንዲያቋቁሙ ጥሪ ቀርቧል።
አጣዬ በተፈፀመባት ጥቃት 1400 መኖሪያ ቤቶች፣ ሆቴል፣ ግሮሰሪ ፣ መጋዘን እንዲሁም 50 ቤቶች፣ ጥቃቅን እና አነስተኛ ማምረቻ ተቋማት 1550 ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው ነበር።
ከተቃጠሉት ምን ያህሉ ተሰሩ ? ለሚለው የከተማው ከንቲባ አሰለፍ ደርቤ ሲመልሱ ''የሞከርነው በዋና ቤት ደረጃ የተቃጠሉትን ከ423 ቤት ውስጥ በመንግስት 45 ቤት፣ በይፋት ልማት ማህበር 10 ቤት አሁን በአልማ 10 ቤት እየሰራን ነው በድምሩ 65 ቤት ነው እየተሰራ ያለው'' ብለዋል።
||
#ስፖርት
በኦስሎ ከተማ ዳይመንድ ሊግ ውድድር እየተካሄደ ሲሆን ከጥቂት ደቂቃ በፊት በተጠናቀቀው የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር ዳዊት ስዩም (የግል ሰዓቷን በማሻሻል 14:25.84)፣ ጉዳፍ ፀጋይና ለተሰንበት ግደይ ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት ማሸነፍ ችለዋል። በተመሳሳይ በወንዶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድርም ጥላሁን ሃይሌ፣ ሳሙኤል ተፈራና ጌትነት ዋሌ በተከታታይ ከአንድ እስከ ሦስት በመግባት አሸንፈዋል።
የሀያ ስድስተኛው ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በ ባህር ዳር ስታዲየም መካሄዱን ሲቀጥል ሰበታ ከተማን የገጠመው ፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ጅማ አባ ጅፋር በበኩሉ ተጋጣሚውን ሀዲያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
5.9K viewsedited 20:26