Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.57K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 229

2022-06-16 17:28:09
በ11 ወራት ከተሞከሩ የሳይበር ጥቃቶች ከ97 በመቶ ከሽፏል ተባለ

በኢትዮጵያ በ11 ወራት ከተሞከሩ የሳይበር ጥቃቶች ከ97 በመቶ የሚልቀውን በማክሸፍ የ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ኪሳራ ማዳን መቻሉ ተነግሯል።

የሳይበር ጥቃቱ በፋይናንስ እና የሚዲያ ተቋማት ላይ በብዛት ኢላማ ያደረገ መሆኑም ታውቋል።

የሳይበር ምሕዳር በባህሪው ድንበር የለሽና ኢ-ተገማች በመሆኑ ዓለም በዚህ መጠነ ሰፊና ተለዋዋጭ ወንጀል በየቀኑ በአማካይ 16 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ሀብት ታጣለችም ተብሏል።

የሳይበር ወንጀል በአውፓዊያኑ 2015 በዓለም ላይ 3 ትሪሊየን ዶላር ካደረሰው ኪሳራ በእጅጉ እያንሰራራ መጥቶ በ2021 ደግሞ 6 ትሪሊየን ዶላር አሳጥቷል።

ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው በየዓመቱ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣው ዓለም ዐቀፍ የሳይበር ወንጀል በ2025 ከ10 ነጥብ 5 ትሪሊየን ዶላር በላይ ሊያሳጣ እንደሚችል ተገምቷል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
21.3K viewsedited  14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 17:27:10
ወርልድ ሬሚት ከአራት የኢትዮጵያ ባንኮች ጋር መስራት አቆመ

ወርልድ ሬሚት የተሰኘው አዓለምአቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ኩባንያ ከአራት የኢትዮጵያ ባንኮች ጋር የነበረውን የስራ ውል ማቋረጡን አስታወቀ።

ወርልድ ሬሚት ስሞኑን ለደንበኞቹ ባሰራጨው መልእክት በወጋገን ፤ ዓባይ ንብ እና ኦሮሚያ ባንክ በኩል ሲሰጥ የቆየውን የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት እንዳቆመ አስታውቋል።

"ኩባንያችን ለደንበኞቹ ምርጥ አገልግሎት ለመስጠት ይተጋል ። ይህን ለማስጠበቅ በማይችልበት ወቅት አገልግሎቱን ለማቋረጥ ይገደዳል ።" ያለው ኩባንያው ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት በሌሎች ባንኮች በኩል እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ምንጭ: ኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
18.7K viewsedited  14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 17:12:57
ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ከሐምሌ 1/2013 እስከ ግንቦት 30/2014 ዓ.ም 984 ሚሊዮን 702 ሺህ 16ብር ተሰብስቧል፡፡

ድጋፉ የተሰበሰበው ከሀገር ውስጥ ቦንድ ሽያጭና ስጦታ፣ ከዲያስፖራ ቦንድ ሽያጭና ስጦታ፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ስጦታ አካውንት ገቢ፣ ከፒን ሺያጭ ገቢና ከ8100 አጭር የሞባይል ስልክ መልዕክት አገልግሎት የተገኘ መሆኑንም ታውቋል፡፡

የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት 2003 ዓ.ም እስከ ግንቦት 30/2014 ዓ.ም ድረስ ከሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ከሚገኙ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት እንዲሁም ከልዩ ልዩ ገቢዎች በአጠቃላይ 16 ቢሊዮን 713ሚሊዮን 716 ሺህ 691 ብር ተሰብስቧል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
1.3K viewsedited  14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 17:12:43
Register at https://www.effsaa.org/short-term-training-program-registration-form/ after the settlement of the training fee.
Venue
At the training hall of Ethiopian Freight Forwarders and Shipping Agents Association (EFFSAA) which is located at Kazanchis, Nigist Towers Hotel & Apartments 4th Floor (In front of Elilly International Hotel)
For More Information,
Call us at +251 115 589045 / +251 903 182525
OR
Visit our telegram channel
https://t.me/EFFSAAOfficial
1.2K views14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 17:12:18
ግብይት በመሰረቱ የአዛምድ ፈተና ነው። ለምንሸጠው ዕቃ ተገቢዉን ገዢ የመፈለግ ሙከራ! ታዲያ ባሁኑ ጊዜ ዓለም በዲጂታል መረብ አንድ በሆነችበት ዘመን ይህንን ፈተና እንዴት በቴክኖሎጂ ማለፍ እንደሚችሉ በተግባር ለማሳየት መልኅቅ ማርኬቲንግ እና ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት የዲጂታል ማርኬቲንግ፣ የሽያጭና ማርኬቲንግ እና የማይንሴት ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል። የተወሰኑ ክፍት ቦታዎች ስላሉን በ0967280828 በፍጥነት ይደውሉና ይመዝገቡ!

#MelhikMarketingandLeadershipInstitute #MMLI #Salesandmarketing #Digitalmarketing #Mindset #Training
1.4K views14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 12:10:53
በአርቲስትት ሄለን በድሉን ላይ የስም ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል የተባለው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበ።

የአርቲስት ሄለን በድሉን ልጅች ላይ የማገትና የአካል ጉዳት ሙከራ በማድረግና በተለያዩ ማህበራዊ ገጾች ላይ እንደሞተች አድርጎ የስም ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል የተባለው ተጠርጣሪ ቢኒያም ጭፍረው ሲሳይ ፍርድ ቤት ቀርቧል።

መርማሪ ፖሊስ ግለሰቡ አርቲስት ሄለን በድሉ እና ባለቤቷን አቶ ሚካኤል መኮንን እና ቤተሰቦቿን ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ የሚገኙ በተደራጁ ቡድኖች በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች የስም ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን አስረድቷል። በልጆቿ ላይ የዕገታና አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ሙከራ ተደርጓል ብሏል ፖሊስ ለፍርድ ቤት።

የተለያዩ ገጾችን በመክፈት አርቲስቷ በባለቤቷ አሲድ እንደተደፋባት፣ በባለቤቷ በጥይት ተመታ እንደተገደለች እና ባለስልጣን አጎት እንዳላት እንዲሁም ባለቤቷ ባለስልጣን ዘመድ እንዳለውና የገንዘብ ስጦታ እንደተሰጠው ተደርጎ በሀሰት መረጃ በመጻፍና በማቀነባበር በማሰራጨት የተጠረጠረ መሆኑን ፖሊስ አብራርቷል።

ተጠርጣሪው በበኩሉ ከ4 አመት በፊት የከፈትኩት ገጽ ነው የጻፍኩት እንጂ ህጻናቱን አላገትኩም በቡድንም ተደራጅቼ አልሰራሁም ሲል ተከራክሯል።

ፖሊስ በበኩሉ ከተለያዩ ቡድኖች ጋር በመቀናጀት አንዱ ለአንዱ ምንጭ በመሆን የተሰራጨ ሀሰተኛ መረጃ እውነት ለማስመሰል ለህዝብ ሲያደርሱ ነበር ሲል ገልጿል።

ጉዳዩን የተከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ለመርማራ ፖሊስ ምርመራውን አጣርቶ እንዲቀርብ የ11 ቀን ጊዜ ፈቅዷል።

ምንጭ: ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
21.1K viewsedited  09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 10:38:53
የድሬዳዋ ምድር ባቡር ስፖርት ክበብ ሜዳ የባለቤትነት ጥያቄ ላይ ውሳኔ ተሰጠ።

በርካታ ውዝግብ ሲያስነሳ የቆየው የድሬዳዋ ምድር ባቡር ስፖርት ክበብ ሜዳ የባለቤትነት ጥያቄ አስመልክቶ የአስተዳደሩ ስፖርት ኮሚሽን በባለቤትነት እንዲስተዳድረው መወሰኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር አስታውቀዋል።

ከንቲባው የስፖርት ማዝወተሪያ ቦታ እንዲለማ የጠየቀውም አካል ምትክ ተለዋጭ ቦታ እንደየአስፈላጊነቱ ታይቶ የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል።

በአስተዳደሩ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራ ግንባታ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

መረጃው የከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
22.0K viewsedited  07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 10:28:02
የ9 ዓመት ህጻን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰ ግለሰብ በ12 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።

በሀዲያ ዞን ሶሮ ወረዳ የ9 ዓመት ህጻን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰ ግለሰብ በ12 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለጸ።

በክስ መዝገቡ እንደተመለከተው ተከሳሽ በቀን 20/04/2014 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 6 ሰዓት አካባቢ የግል ተበዳይ እና እድሜዋ 9 የሆናትን ህጻን ከጊምቢቹ መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወጥታ ወደ መኖሪያ ቤቷ በመሄድ ሳለች በማታለልና በማስፈራራት ወስዶ ነው ድርጊቱን የፈጸመው።

በዚህም ተከሳሽ ቦክሰር ሞተር ሳይክል በመያዝ ቀርቦ እናቷን እንደሚያውቃትና ቤት አደርስሻለው ሞተር ላይ ውጪ በማለት አታሎ በማስፈራራት በሶሮ ወረዳ 1ኛ ሰልፌ ቀበሌ በልዩ ስሙ አገባ ተብሎ በሚጠራበት ቦታ ምንም አይነት ሰው በሌለበት ቤት አስገብቶ በፈጸመው የአስገድዶ መድፈር በህጻት ልጆች ላይ በሚፈጸም የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል።

አቃቤ ህግ በተከሳሹ ላይ የሰው የሰነድና የህክምና ማስረጃ አቅርቦ ተከራክሯል። ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኝ ምስክሮችን አድምጦ ግንቦት 29/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን ጥፋተኛ በማለት የቅጣት ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህ መሠረት ተከሳሹ እጁ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ በ12 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የውሳኔ መዝገብ ያስረዳል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
20.4K viewsedited  07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 10:27:19
በ45 ሚሊየን ብር ወጪ እድሳት የተደረገለት የሀገር ፍቅር ቴ/ቤት በ2 ወራት ተጠናቆ አገልግሎት ይጀምራል ተባለ።

በአፍሪካ አንጋፋው ቴአትር ቤት (የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት) በሀገር ወዳዶች አደራጅነት ሐምሌ 11 ቀን 1927 ዓ.ም የተመሰረተው የሀገር ፍቅር ቴአትር በሁለት ወራት ውስጥ ዕድሳቱ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል።

ኢትዮጵያን ከፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ለመታደግ ጥበብ ያላትን የመቀስቀስ ሚና በመረዳት ‘የኢትዮጵያ ሕዝብ የሀገር ፍቅር ማህበር’ በሚል ስያሜ የተቋቋመው ቤተ-ጥበብ ከተመሰረተ የፊታችን ሐምሌ 87 ዓመታትን ይደፍናል።

በኮቪድ 19 ዋዜማ ጀምሮ በዕደሳት ላይ የቆየው ቴአትር ቤቱ አሁን ላይ የእድሳት ስራ እየተጠናቀቀ ሲሆን፤ የወንበር መግጠም፣ መጋረጃ እና መሰል የፊኒሺንግ ስራዎችን የማሟላት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የቴአትር ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አብዱልከሪም ጀማል ገልጸዋል።

ቴአትር ቤቱ ለህዝብ ክፍት ሲደረግም ቀደም ሲል ለተመልካች ዕይታ ቀርበው ከተቋረጡ ሁለት ተውኔቶች በተጨማሪ አራት አዳዲስ ተውኔቶች ለመድረክ ዕይታ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት 128 ቋሚ ሰራተኞች የሚያስተዳድር ሲሆን ስራ አቁሞ በቆየበት ላለፉት 19 ወራት ገደማ ዕድሳት ላይ በቆየበት ጊዜ የተቀነሰ ሰራተኛ እንደሌለው ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ኮንስትራክሽን ቢሮ በኩል ዕድሳት የተደረገለት ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ለአጠቃላይ ዕድሳቱ 45 ሚሊየን ብር እንደፈጀ ተገምቷል። (ENA)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
16.6K viewsedited  07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 10:26:49
Sejoy Blood pressure

0911284606
    ሀኪሞን በእጆ , ጤናዎትን በየግዜዉ ሳይጨነቁ በፈለጉበት ቦታ ና ግዜ ይወቁ
የደም መጠን ሚለካ 
የልብ ምት መጠንን ሚለካ
ሰለደም ግፊት አጠቃላይ መረጃ ሚሰጥ
ዋጋ- 1900  birr
Bole medanialem
14.0K views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ