Get Mystery Box with random crypto!

ወርልድ ሬሚት ከአራት የኢትዮጵያ ባንኮች ጋር መስራት አቆመ ወርልድ ሬሚት የተሰኘው አዓለምአቀፍ | TIKVAH-MAGAZINE

ወርልድ ሬሚት ከአራት የኢትዮጵያ ባንኮች ጋር መስራት አቆመ

ወርልድ ሬሚት የተሰኘው አዓለምአቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ኩባንያ ከአራት የኢትዮጵያ ባንኮች ጋር የነበረውን የስራ ውል ማቋረጡን አስታወቀ።

ወርልድ ሬሚት ስሞኑን ለደንበኞቹ ባሰራጨው መልእክት በወጋገን ፤ ዓባይ ንብ እና ኦሮሚያ ባንክ በኩል ሲሰጥ የቆየውን የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት እንዳቆመ አስታውቋል።

"ኩባንያችን ለደንበኞቹ ምርጥ አገልግሎት ለመስጠት ይተጋል ። ይህን ለማስጠበቅ በማይችልበት ወቅት አገልግሎቱን ለማቋረጥ ይገደዳል ።" ያለው ኩባንያው ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት በሌሎች ባንኮች በኩል እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ምንጭ: ኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot