በ11 ወራት ከተሞከሩ የሳይበር ጥቃቶች ከ97 በመቶ ከሽፏል ተባለ
በኢትዮጵያ በ11 ወራት ከተሞከሩ የሳይበር ጥቃቶች ከ97 በመቶ የሚልቀውን በማክሸፍ የ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ኪሳራ ማዳን መቻሉ ተነግሯል።
የሳይበር ጥቃቱ በፋይናንስ እና የሚዲያ ተቋማት ላይ በብዛት ኢላማ ያደረገ መሆኑም ታውቋል።
የሳይበር ምሕዳር በባህሪው ድንበር የለሽና ኢ-ተገማች በመሆኑ ዓለም በዚህ መጠነ ሰፊና ተለዋዋጭ ወንጀል በየቀኑ በአማካይ 16 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ሀብት ታጣለችም ተብሏል።
የሳይበር ወንጀል በአውፓዊያኑ 2015 በዓለም ላይ 3 ትሪሊየን ዶላር ካደረሰው ኪሳራ በእጅጉ እያንሰራራ መጥቶ በ2021 ደግሞ 6 ትሪሊየን ዶላር አሳጥቷል።
ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው በየዓመቱ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣው ዓለም ዐቀፍ የሳይበር ወንጀል በ2025 ከ10 ነጥብ 5 ትሪሊየን ዶላር በላይ ሊያሳጣ እንደሚችል ተገምቷል።
@tikvahethmagazine @tikvahmagbot