Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-12-10 08:57:52
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ በማምጣት ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ 222 ተማሪዎች እንዲሁም በሪሚዲያል ፕሮግራም በዲላ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩና ማለፍያ ነጥብ ያስመዘገቡ 1,936 ተማሪዎች በድምሩ 2,158 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል።

@News_For_Student
@News_For_Student
18.9K views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-08 21:45:08
የሪሚዲያል ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ምደባችሁን ለማየት የቀረቡ አማራጮች፦

በድረ-ገፅ፦
https://placement.ethernet.edu.et

በቴሌግራም ቦት፦
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ #የማያስተናግድ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የተመደባችሁበት የትምህርት ተቋማት ጥሪ በመጠበቅ ትምህርታችሁ መከታተል ትችላላችሁ ተብሏል።

@News_For_Student
@News_For_Student
21.4K views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-07 14:45:38
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ፤ ነገር ግን በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በራያ ዩኒቨርሲቲም ሆነ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ምንም ትምህርት ያልጀመራችሁ ተማሪዎች በሙሉ እስከ ታህሳስ 03/2016 ዓ.ም በራያ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራር ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ ራያ ዩኒቨርሲቲ ጥሪ አድርጓል፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
19.1K views11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-06 13:09:49
#MattuUniversity

በ2016 ዓ.ም ወደ መቱ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ (Freshman) ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በመቱ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፈያ ውጤት ያስመዝግባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 01 እና 02/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

➢ ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና አንድ ኮፒ፣
➢ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ፣
➢ የስፖርት ትጥቅ፡፡

Note:
በ2015 ዓ.ም በመቱ ዩኒቨርሲቲ በደሌ ካምፓስ በሪሚዲያል መርሐግብሩ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ ተማሪዎች ምዝገባችሁ በበደሌ ካምፓስ የሚካሔድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@News_For_Student
@News_For_Student
19.3K views10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-05 13:33:16 የ2016 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን እንደሚከተለው ይሆናል።

¤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 5 እና 6
¤ መቀለ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 28 - 30
¤ ሀዋሳ ዩኒቨረሲቲ ታህሳስ 8 እና 9
¤ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 30
¤ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 1 እና 2
¤ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 24 እና 25
¤ አክሱም ዩኒቨርሲቲ ህዳር 27 እና 28
¤ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 5 እስከ 7
¤ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 24 እና 25
¤ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 21 እና 22
¤ ኦዳ ቡሉቱም ህዳር 24 እና 25
¤ አርሲ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 4 እና 5
¤ ቀብሪዳር ዩኒቨርሲቲ ህዳር 13 እና 14
¤ ራያ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 17 እና 18
¤ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 10 እና 11
¤ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 3 እና 4
¤ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 3 እና 4
¤ ደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 10 እና 11
¤ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 1 እና 2
¤ ጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 19 - 26
¤ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 30 - ታህሳስ 2

ቀሪዎቹን የዩኒቨርሲቲ ጥሪዎች ተከታትለን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

@News_For_Student
@News_For_Student
19.2K views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-04 11:57:35
በ2016 ዓ.ም ወደ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እና በ2015 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፍያ ነጥብ ያስመዘገባችው ተማሪዎች፤ የ2016 ዓ.ም ምዝገባ የሚከናወነው ታህሳስ 03 እና 04/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
- የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሚዛን አማን በሚገኘው ዋናው ጊቢ
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ጊቢ

ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

➢ ከ9ኛ እስከ 2ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ሦስት ኮፒ፣
➢ የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ሦስት ኮፒ፣
➢ ዘጠኝ 3 x 4 የሆ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ፣
➢ የስፖርት ትጥቅ፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
19.9K views08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-02 10:06:10
በ2016 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች መግቢያ እሁድ ኅዳር 30/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲው አሳውቋል፡፡

አቀባበል ሰኞ ታኅሣሥ 01/2016 ዓ.ም፣ ምዝገባ ማክሰኞ ታኅሣሥ 02/2016 ዓ.ም እንዲሁም ትምህርት የሚጀመረው ረቡዕ ታኅሣሥ 03/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች፦
አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው ዓባያ ካምፓስ

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች፦
የስም ዝርዝራችሁ ከ“A” እስከ “S” የሚጀምር በጫሞ ካምፓስ፣ አርባ ምንጭ ከተማ
የስም ዝርዝራችሁ ከ“T” እስከ “Z” የሚጀምር በሳውላ ካምፓስ፣ ሳውላ ከተማ

ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

➢ የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ሁለት ኮፒ፣
➢ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ሁለት ኮፒ፣
➢ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ሁለት ኮፒ፣
➢ ሁለት ፓስፖርት መጠን ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ፣
➢ የስፖርት ትጥቅ፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
21.7K views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-01 21:12:45
#AssosaUniversity

በ2015 ዓ.ም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም የተከታትላችሁና የማለፊያ ነጥብ ያመጣቹ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችው አዲስ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 01 እና 02/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በመሆኑም በተገለፁት ቀናት ብቻ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት በአካል በመገኝት እንድትመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

➢ ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች፣
➢ 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ፣
➢ የስፖርት ትጥቅ፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
17.4K views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-30 11:07:54
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት አዘጋጅቷል።

የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዘገባ ህዳር 24 እና 25/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው መግለጹ ይታወቃል፡፡

የዩኒቨርሲቲው አውቶብሶች መነሻ ቦታዎች፦

➧ አዲስ አበባ መርካቶ መናኸሪያ

➧ አዲስ አበባ ቃሊቲ መናኸሪያ

➧ አዳማ ፍራንኮ አካባቢ

➧ አዳማ ሚጊራ መናኸሪያ

@News_For_Student
@News_For_Student
19.4K views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-29 16:59:21
#AAU

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ታህሳስ 05 እና 06/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
በየተመደባችሁበት የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች

ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ከመምጣታችሁ በፊት https://portal.aau.edu.et ላይ በመግባት Freshman የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የግል መረጃቻችሁን እንድታሟሉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

➢ የ12ኛ ክፍል ፈተና ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➢ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
➢ የስፖርት ትጥቅ፡፡

Note:

በተጠቀሱት ቀናት ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች በመገኘት ዩኒቨርሲቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡

ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉት ታህሳስ 08/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር መልሶ ቅበላ ከታህሳስ 08 እስከ 12/2016 መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦
https://portal.aau.edu.et/ ወይም http://aau.edu.et

@News_For_Student
@News_For_Student
18.6K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ