Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-10-08 12:18:26
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ  ፈተና ውጤት ነገ ይፋ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህም ዙሪያ ትምህርት ሚኒስቴር ነገ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

@News_For_Student
@News_For_Student
14.8K views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-08 09:03:51
ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ ይሰጣል።

ሚኒስቴሩ ነገ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 ጀምሮ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን በተመለከተ በሚኒስቴሩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አመለወርቅ ህዝቅኤል ተፈርሞ ለተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የተላከው ደብዳቤ ትክክለኛነትን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል።

በሐምሌ 2015 ዓ.ም መጨረሻ በሁለት ዙር የተሰጠውን የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ 840 ሺህ በላይ ተፈታኞች መውሰዳቸው ይታወሳል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.0K views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-05 13:34:37
ለመላው መምህራን እንኳን ለዓለምዓቀፋ የመምህራን ቀን አደረሳችሁ፡፡

በዓለምዓቀፍ ደረጃ የዛሬዋ ቀን የመምህራን መታሰቢያ በመሆን እንድትከበር ከተወሰነ ዛሬ 29 ዓመት ሆኗል፡፡

በዓለማቀፍ ደረጃ ዩኔስኮ እያከበረዉ የሚገኘው “The teachers we need for the education we want: The global imperative to reverse the teacher shortage” በሚል መሪ መልእክት ነው ፡፡

ክብር ለመምህራን ይሁን!

@News_For_Student
@News_For_Student
19.2K views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-03 15:09:34
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት በዚህ ወር መጨረሻ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

በፀጥታና ሌሎች ምክንያቶች ፈተና ሳይወስዱ የቆዩ ተማሪዎች ከሁለት ሳምንት በፊት ፈተናቸውን መውሰዳቸው ይታወቃል።

የነዚህ ተማሪዎችን ፈተና ውጤት በሐምሌ 2015 ዓ.ም ከተፈተኑ ተማሪዎች ጋር አብሮ ይፋ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመስከረም መጀመሪያ ሳምንት ፈተና የወሰዱ ተማሪዎችን ጨምሮ ውጤት ይፋ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማሳወቁ አይዘነጋም።

"እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ውጤቱ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል" የአገልግሎቱ ከፍተኛ ኃላፊ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ውጤት ይፋ የሚደረግበትን ቀንና ተያያዥ መረጃዎችን የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር የምናደርሳችሁ ይሆናል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.2K views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-01 08:37:20
#Update

ብሔራዊ የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና / Graduate Admission Test ከመስከረም 28 እስከ 30/2016 ዓ.ም በበይነ-መረብ ይሰጣል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ምርምር ኢንስቲትዩት- የፈተና ማዕከል ጋር በመተባበር የሚሰጠው ፈተና በተጠቀሱት ቀናት በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይከናወናል።

ለፈተናው የተመረጣችሁ ተፈታኞች ከመስከረም 21 እስከ 25/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው የGAT መመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et ላይ ምዝገባ ማድረግ ይጠበቅባችኋል።

ከመስከረም 23 እስከ 25/2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት የሙከራ ፈተና ይሰጣል።

(ለመመዝገብ እና ፈተናውን ለመውሰድ የይለፍ ቲኬት ለማግኘት ሊከተሏቸው የሚገቡ ቅደም-ተከተሎች ከላይ ተያይዟል።)

@News_For_Student
@News_For_Student
16.0K views05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-27 07:14:53
#ማስታወቂያ

የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ምዝገባና ፈተና ጊዜ ተራዝሟል።

የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (Graduate Admission Test)  ከመስከረም 28-30/2016 ዓ.ም ጀምሮ  የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ይሰጣል።

በመሆኑም የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ከመስከረም 21-25/2016 ዓ.ም  በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፖርታል https://portal.aau.edu.et በመጠቀም እንድትመዘገቡ እንገልጻለን ።

@News_For_Student
@News_For_Student
16.8K viewsedited  04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-25 07:52:27
በትግራይ ክልል ከ11 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት በመከታተል ላይ ይገኛሉ።

ተማሪዎቹ በክልሉ በሚገኙት መቐለ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጣቸው መሆኑ ተገልጿል።

ተማሪዎቹ በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ የነበሩና መልቀቂያ ፈተናውን ሳይወሰዱ የቀሩ ናቸው።

ፈተናው ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ.ም በክልሉ በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የክልሉ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ዳይሬክተር ክንፈ ፍስሃ ለኢዜአ ተናግረዋል።

@News_For_Student
@News_For_Student
17.5K views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-23 07:38:03
ሁለተኛው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ( Exit Exam ) ጥር ወር ላይ ይሰጣል

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በትናንትናው ዕለት ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ ላይ ተቋማት የመደበኛ ተማሪዎቻቸውን እንዲሁም 2015 ላይ የመውጫ ፈተና ወስደው ያላለፉ ተማሪዎችን መረጃ እስከ ጥቅምት 10/2016 ድረስ ይልኩ ዘንድ አሳስቧል።

ባለስልጣኑ ለግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ ላይ ቀጣዩ ማለትም ሁለተኛው የመውጫ ፈተና ጥር ወር ላይ በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሰጥ ጠቁሟል።

የመውጫ ፈተና በየ ስድስት ወሩ የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚንስቴር መግለፁ ይታወሳል።

@News_For_Student
@News_For_Student
14.5K views04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-21 06:52:17
በፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ ከ11,500 በላይ ተማሪዎች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ መግባታቸው ተሰምቷል፡፡

ፈተናቸውን ለማጠናቀቅ በድጋሚ ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የገቡትን ተማሪዎች በተረጋጋ መልኩ ለማስፈተን ዝግጅት ማድረጉን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ተማሪዎቹ በሦስት ዞኖች እና በጎንደር ከተማ የመጡ መሆናቸውን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ልጅዓለም ጋሻው ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎቹ ያቋረጧቸውን የኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እንዲሁም የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር የትምህርት አይነቶች ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል። #አሚኮ

@News_For_Student
@News_For_Student
12.8K views03:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-20 06:17:42
በፀጥታ እና በሌሎች ምክንያቶች ፈተና ላልወሰዱ ከ15 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከመስከረም 08 እስከ 11/2016 ዓ.ም ፈተና ይሰጣል መባሉ ይታወቃል።

በጎንደር እና በጋምቤላ ሙሉ በሙሉና በከፊል ፈተና ያልወሰዱ እንዲሁም በማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ ተፈታኞች ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጳጉሜን 03/2015 ዓ.ም ማሳወቁ አይዘነጋም።

በፈተናው ዙሪያ የሚወጡ መረጃዎችን እናደርሳችኋለን።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.9K views03:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ