Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-10-26 08:21:52
ሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎችን መረጃ በአስቸኳይ እንዲልኩ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

ተቋማቱ በየፕሮግራሙ ያሉ ተማሪዎች መረጃን እስከ ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም እንዲልኩ ሚኒስቴሩ ጠይቋል።

በተጠቀሰው ጊዜ መረጃውን የማያሳውቅ የትምህርት ተቋም ተፈታኝ ተማሪ እንደሌለው እንደሚታሰብ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በ2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የመውጫ ፈተና በመንግሥት እና በግል ተቋማት በድምሩ 150,184 ዕጩ ተመራቂዎች ፈተናውን ወስደው 61,054 ተፈታኞች ወይም 40.65 በመቶዎቹ ማለፋቸው ይታወሳል።

(በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጄና (ዶ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።)

@News_For_Student
@News_For_Student
16.0K views05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-24 08:58:34 " እባክችሁ መፍትሄ ስጡን ፤ ጊዜው ያለ ትምህርት እየሄደብን ነው " - ተማሪዎች

በአማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የሚማሩ ተማሪዎች እስካሁን ወደ ትምህርት እንዳልተመለሱ በመግለፅ ትምህርት ሚኒስቴር መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጥሪ አቀረቡ።

መልዕክታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ ተማሪዎች እስካሁን የሚማሩባቸው ግቢዎች እንዳልጠሯቸው በማመልከት ያለ ትምህርት መቀመጣቸውን ገልጸዋል።

በእነሱ እድሜና ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃ የሚገኙ በሌሎች ክልሎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ጓደኞቻቸው ትምህርታቸውን ለመጀመር ወደ ሚማሩበት ተቋም ከበርካታ ቀናት በፊት መግባታቸውን እነሱ ግን እስካሁን መቼ እንኳን እንደሚጠሩ እንደማያውቁ በመግለፅ ትምህርት ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ መፍትሄ ቢሰጥ ብለዋል።

ተማሪዎቹ ከእኩዮቻቸው ወደ ኃላ እየቀሩ መሆኑን አመልክተው ይህም የሚያሳድረው ጫና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የፊልድ ምርጫ ካደረጉ በኃላ ወደቤት ተመልሰው ከወራት በላይ ያለትምህርት መቀመጣቸውን አመልክተዋል።

" ትምህርት ሚኒስቴር ስለኛ ጉዳይ ችላ ማለት የለበትም " ሲሉ ያሳስቡት ተማሪዎቹ የትግራይ ተማሪዎች አይነት ዕጣ ፋንታ እንዳይደርሰን ከወዲሁ አፋጣኝ መፍትሄ ይፈለግልን ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ፤ በአማራ ክልል ባለው ተለዋዋጭ የሆነ የፀጥታ ሁኔታ ከአማራ ክልል ወደ ተለያዩ ክልሎች ወደሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሄደው መማር ያልቻሉ ተማሪዎች ስለመኖራቸው ለማወቅ ተችሏል።

ተማሪዎቹ በፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ለመሄድ መንገዶች ፈታኝ እንደሆነባቸው አመልክተዋል።

አቅም ያላቸው በአየር ትራንስፖርት ፤ አንፃራዊ ሰላም ያለባቸው ቦታዎች የሚኖሩ በብዙ ብር በየብስ ትራንስፖርት ወደ ሚማሩበት ተቋም መግባታቸውን ነገር ግን የፀጥታና ደህንነት ሁኔታው ባልተሟላባቸው በተለይ ጎጃም አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች ወደ ትምህርት መመለስ እንዳልቻሉ የደረሱን መልዕክቶች ያስረዳሉ።

ያለው የትራንስፖርት ዋጋም ውድ በመሆኑና መንገዶችም ስለሚያሰጉ እንደ " ቀይ መስቀል " አይነት ተቋማት እስካሁን ወደ ተቋማቸው ያልገቡ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ተቋማቸው የሚወስዱበት መፍትሄ እንዲፈለግ ጠይቀዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ተወካይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑን ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

ዶ/ር ሰለሞን ፤ የደህንነት ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደ ተቋማቸው የመመለሱ ስራ የሚሰራው ከወታደራዊ ኮማንድ ፖስት ጋር በመተባበር ነው ብለዋል።

" አሁን ባለው ሁኔታና ካለው የፀጥታ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ዩኒቨርሲቲዎች በሴኔት ተማሪዎችን የሚቀበሉበትን ቀን እየወሰኑ ተማሪዎችን እየጠሩ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። ይሄ ደግሞ እየተሰራ ያለው በዋናነት የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች በአካባቢው ከሚገኙ የኮማንድ ፖስት አካላት ጋር በቅርብ እየተወያዩ ለተማሪዎች ካለው Safety እና Security አኳያ እየተገመገመ እየተሰራ እንደሆነ እናውቃለን " ብለዋል።

" እንደ ትምህርት ሚኒስቴርም ያለው concern ትክክለኛ ስለሆነ በቅርብ እየተከታተልን ነው። የሚፈለገው የድጋፍ እና ክትትል ስራ እየሰራን ነው። እስካሁን የጎላ ችግር አልቀረበም በኛ በኩል ቀጣይ የሚነሱ ችግሮች ካሉ በዛው ካለው የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ ሆነን እንሰራለን " ሲሉ ተናግረዋል።

@News_For_Student
@News_For_Student
12.9K views05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-23 14:27:52
#GAT የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

" 62 (50%) እና በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ / 80 ፐርሰንታይል ያገኙ በሚፈልጉበት ተቋም ገብተው መማር ይችላሉ "

የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ የአገራዊ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (National GAT) የመቁረጫ ነጥብ አሳውቋል።

በዚህም መሠረት ፤ አጠቃላይ ከተፈተኑት ጥያቄዎች ውስጥ 62 (50%) እና በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ ወይም 80 ፐርሰንታይል (80 Percentile) ያገኙ ተፈታኞች #ብቻ ለመማር በሚፈልጉበት ተቋም አመልክተው መማር የሚችሉ እንደሆነ ተገልጿል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመልካቾች ለማመልከት ሲመጡ ውጤታቸውን እንዲያቀርቡ በማድረግ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestingStatus በመግባት እና የተማሪውን የመግቢያ ስም (Username) እና የይለፍ ቃል (Password) በመጠቀም ማረጋገጥ ይቻላሉ ተብሏል።

በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ መሰረት ፤ በሁሉም የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር የሚፈልጉ አመልካቾች በሙሉ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (National Graduate Admission Test-NGAT) ተፈትነው ያለፉ ብቻ መሆን እንዳለባቸው አቅጣጫ መቀመጡ ይታወሳል።

(ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ/ም በትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

@News_For_Student
@News_For_Student
13.8K views11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-23 06:32:30
በ12ኛ ክፍል ፈተና ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን እስከ ጥቅምት 14 ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ ተገለጸ

በ2015 የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች፤ የዩኒቨርሲቲና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በኩል እስከ ጥቅምት 14/2016 ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሰታውቋል።

በልዩ ኹኔታ በአዳማና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር ለሚፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ በመሆኑ፤ ምርጫቸው ውስጥ በማካተት መመደብ እንደሚችሉም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በዚህም መሰረት በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት ለመማር ያለፋ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ጥቅምት 14/2016 ድረስ ማስተካከል  እንደሚችሉ ተመላክቷል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.5K views03:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-22 08:34:13
የ2015 የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት በአማካይ ነጥብ በተለያዩ #መቁረጫ ነጥቦች የተማሪዎች ብዛት

፨ 50%ና ከዚያ በላይ ያመጡ 27,267 ተማሪዎች
፨ 40%ና ከዚያ በላይ ያመጡ 63,694
፨ 35%ና ከዚያ በላይ ያመጡ 102,177
፨ 34%ና ከዚያ በላይ ያመጡ 113,625
፨ 33%ና ከዚያ በላይ ያመጡ 127,017
፨ 32%ና ከዚያ በላይ ያመጡ 143,625
፨ 31%ና ከዚያ በላይ ያመጡ 164,110

@News_For_Student
@News_For_Student
14.7K views05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-20 19:30:43
" ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተዛውሮ መማር አይቻልም " - ትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ በ2015 ዓ/ም የሬሜዲያል ትምህርት ተከታትለው 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች የፍሬሽማን ኮርስ እንዲማሩ መወሰኑን አስታውሷል።

በዚህም መሰረት ፦

- ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተዛውሮ መማር እንደሚችሉ፤

- ከአንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ ሌላ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተዛውሮ መማር እንደሚችሉ እና

- ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተዛውሮ መማር የማይችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አስገንዝቧል።

ተማሪዎች ከአንድ ተቋም ወደ ሌላ ተቋም ሄደው መማር የሚፈልጉ ከሆነ መረጃቸው በአግባቡ ተደራጅቶ እንዲሰጣቸው ትምህርት ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ አሳስቧል።

(በሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ ተፅፎ ለተቋማት የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

@News_For_Student
@News_For_Student
15.0K views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-19 17:27:54
በ 2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ)  ለመማር ያለፋችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርትቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፡

 በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ምርጫችሁ ውስጥ በማካተት መመደብ የምትችሉ መሆኑ እናሳውቃለን።

የትምህርት ሚኒስቴር

@News_For_Student
@News_For_Student
15.6K viewsedited  14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-19 11:54:33
" ዘንድሮ 164,242 ተማሪዎችን በሬሜዲያል እንቀበላለን " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ በዘንድሮው ዓመት 164,242 ተማሪዎች በአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራም እንደሚታቀፉ አሳውቀዋል።

እንዚህ ተማሪዎች በግልና በመንግሥት ተቋማት የሬሜዲያል ትምህርት የሚከታተሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ፕ/ር ፕርሃኑ ነጋ ምን አሉ ?

- በ2014 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ፦

• ወደ መንግሥት ተቋማት ተመድበው የሬሜዲያል ትምህርት ከተከታተሉት 105,00 ተማሪዎች 63,033 ተማሪዎች አልፈዋል።

• በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ተከታትለው  ከተፈተኑት ውስጥ 44,500 ተማሪዎች 27,587 ተማሪዎች አልፈዋል።

በአጠቃላይ ወደ 145,000 ገደማ ተማሪዎች ሬሜዲያል ገብተው በዛው በተቋማቸው ከ30% እንዲሁም ከማዕከል 70% ተፈትነው ከ50% እና በላይ አምጥተው ያለፉት 90,620 ተማሪዎች ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች ዘንድሮ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ።

- በ2015 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ያለፉት ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች 27,267 ገደማ ናቸው። በቀጥታ ፌሽማን / አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ።

- በአጠቃላይ በ2014 ዓ/ም ተፈትነው ሬሜዲያል ያለፉና በ2015 ዓ/ም 50 በመቶ አምትጥተው በቀጥታ ያለፉትን ጨምሮ 117,887 ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ። (90,620 ከሬሜዲያል፤ 27267 ከ2015 ዓ/ም አላፊዎች)

- ዘንድሮ በአጠቃላይ በዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡት 191, 509 ተማሪዎች ናቸው። ከነዚህ ውስጥ 164,242 የሬሜዲያል ተማሪዎች ናቸው፤ እነዚህ በግል እና በመንግሥት ተቋማት ገብተው እንዲማሩ ይደረጋል

@News_For_Student
@News_For_Student
14.1K views08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-18 08:19:33
በአማራ ክልል በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና 497 ትምህርት ቤቶች ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

በክልሉ በ2015 ዓ.ም በመደበኛ፣ በማታ እና በግል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ 214,997 ተማሪዎች ምዝገባ ያደረጉ ሲሆን 210,323 ተማሪዎች ወይም 97.8 በመቶ ፈተናውን መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡

በክልሉ 574 ትምህርት ቤቶች የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ማስፈተናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ከነዚህም 497 ትምህርት ቤቶች ቢያንስ አንድ ተማሪ 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የገለጹት ኃላፊዋ፤ በ77 ትምህርት ቤቶች ደግሞ አንድም ተማሪ የማለፊያውን ነጥብ እንዳለመጣ ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ 60 ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት (600 እና በላይ ለተፈጥሮ ሳይንስ ፤ 500 እና በላይ ለማኅበራዊ ሳይንስ) ማስመዝገባቸውን ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
16.0K views05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-15 18:55:55
"በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የያዝነው አቅጣጫ የሚቀጥል ነው። ወደኋላ የምንመልሰው አይደለም።"

- የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የትምህርት ዘርፍ ማሻሻያዎች እና የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን አስመልክተው የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከኢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

መንግሥት በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ የያዘውን አቅጣጫ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

"የመልቀቂያ ፈተና አሰጣጡን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ይሠራል" ብለዋል።

በዚህም በግንቦት ወር መጨረሻ የሚከናወነው የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ድብልቅ / Hybrid በሆነ መልኩ እንደሚሰጥ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

ፈተናው በከፊል በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በአካል፥ በከፊል ደግሞ በኦንላይን (በተለይ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች) የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ፈተናውን መስጠት የመንግሥትን ወጪ ይቀንሳል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህን ለማሳካት ለፈተናው የሚሆኑ ታብሌቶችን የማሰባሰብ ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባም በኦንላይን ይከናወናል ብለዋል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.1K views15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ