Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-09-06 14:10:00
#WallagaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የመደበኛ እና የተከታታይ (CDEP) መርሐግብር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡

የሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የቅድመ ምረቃ እና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 21 እና 22/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ምዝገባው በዩኒቨርሲቲው ሦስቱም ካምፓሶች (ነቀምቴ፣ ጊምቢ እና ሻምቡ) እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
13.6K views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-06 06:56:15
የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር አመራሮች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በትምህርት፣ በመምህራን ጉዳዮች እና በአጠቃላይ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ትኩረት ማድረጉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

መምህራን የደረጃ ዕድገት፣ የመኖሪያ ቤት እንዲሁም የደመወዝ ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

ምስል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

@News_For_Student
@News_For_Student
13.8K views03:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-05 08:15:40
የ12ኛ ክፍል ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናው መቼ ይሰጣል?

ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለጹ ይታወቃል።

ተማሪዎቹ ፈተናውን እንዲወስዱ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ተናግረዋል።

ለዚህም የፈተና ህትመት፣ የሰው ኃይል እና የበጀት ዝግጅት እየደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ተማሪዎቹ በስነ-ልቦና ለፈተና ዝግጁ ሲሆኑ እንዲሁም ፈተናው በሚሰጥባቸው አካባቢዎች አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ መኖሩ ሲረጋገጥ "በአጭር ጊዜ ውስጥ" ፈተናው እንዲሰጥ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመዋል።

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለፈተና ተቀምጠው የመጨረሻ ቀናት ሦስት ፈተናዎችን ያልወሰዱ ተማሪዎች በዚህ ዓመት መጨረሻ ፈተናቸውን እንዲያሚያጠናቅቁ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) መናገራቸው ይታወሳል፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
12.7K views05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-03 15:34:04
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም አጋማሽ ድረስ ይፋ ይደረጋል።

የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም 2016 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ ይፋ እንደሚደረግ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።

በጥቅምት 2016 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመጀመር ዕቅድ መያዙንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በፀጥታ ችግር ምክንያት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሦስት ፈተናዎች ያልወሰዱ ተማሪዎች በቅርቡ ፈተናቸውን ይወስዳሉም ብለዋል።

በ2015 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን ሲወስዱ የነበሩት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች፣ የመጨረሻዎቹን ሦስት ፈተናዎች አለመፈተናቸው ይታወቃል።

እነዚህ ተማሪዎች በዚህ ዓመት መጨረሻ ድረስ ፈተናቸውን እንዲያሚያጠናቅቁ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በኦንላይን እንደሚሰጥም ጠቁመዋል።

@News_For_Student
@News_For_Student
15.1K views12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-02 08:12:50
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ፍሬሕይወት ታምሩን የቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ ሾሟል፡፡

ቦርዱ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ፍሬህይወት ታምሩን የቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ መሾሙን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ደግሞ ከነሐሴ 24/2015 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን ገልጸዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) መሾማቸው ይታወቃል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ራስ ገዝ እንዲሆን በአዋጅ የተፈቀደ ቢሆንም፣ ሙሉ በሙሉ ራስገዝ ሆኖ ሥራ የሚጀምረው የሚተዳደርበት መመሪያዎች ዝግጅት ተጠናቀው ሲፀድቁ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሆን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

@News_For_Student
@News_For_Student
12.8K views05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-31 08:54:45
በ7ኛው የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር ላሸነፉ ተማሪዎች ሽልማት ተበረከተ፡፡

በቻይና ሼንዘን ከተማ ከግንቦት 16 እስከ 20/2015 ዓ.ም በተካሄደው ውድድር ዘጠኝ ኢትዮጳውያን ተማሪዎች መሳተፋቸው አይዘነጋም፡፡

በውድድሩ ሦስተኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁ ዘጠኝ ተማሪዎች ታብሌቶች እንዲሁም ለአኅጉር አቀፍ ውድድር አሸናፊዎች ደግሞ የሁዋዌ አርም ባንድ ሽልማት በሁዋዌ ተበርክቶላቸዋል፡፡

ሁዋዌ የ2023-24 የአይሲቲ ውድድር መከፈቱን ይፋ አድርጓል፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
13.0K views05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-30 12:28:57
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን የሚቀበልበት መስፈርት እንደሚከተለው ይሆናል፡-

1. እንደማንኛውም ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ወጪያቸውን በመንግስት የሚሸፈንላቸውን ተማሪዎችን ፈትኖ ይቀበላል፣

2. በአሁኑ ሰዓት በማታው ክፍለ ጊዜ (Extension) በግል እየተማሩ እንደሚገኙ ተማሪዎች በመደበኛው ክፍለ ጊዜም (Regular) ተመሳሳይ ተማሪዎችን ተቀበሎ በመጠነኛ ክፍያ የሚያስተምር ይሆናል፣

3. ዩኒቨርሲቲው በፊት ከነበረው ከትምህርት ሚኒስቴር ከሚላክለት የተማሪዎች ቅበላ ውጭ በልዩነት ፈትኖ ተማሪዎችን ቢቀበልም ከዚህ በፊት በመንግስት ከሚመደብለት የተማሪዎች ቁጥር ያነሰ አይሆንም፤

4. አዋጁ በግልጽ እንዳስቀመጠው ሁሉንም የኢትዮጵያ ተማሪዎችን ታሳቢ ያደረገ የትምህርት ተቋም እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው ይገልፃል

በመሆኑም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም ኢትዮጵያዊ መዳረሻ ፣ የእውቀት መገብያ መናኸሪያ እንዲሆን እንጂ ራስ ገዝ አስተዳደር ያስፈለገው የገንዘብ አቅም ያላቸው ተማሪዎችን ብቻ ተቀብሎ የሚያስተምር ተቋም እንዳይሆን ታስቦ እንደሆነ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ይህ ማለት አንድ ተማሪ ወደ ተቋሙ ለመማር አስቦ ሲመጣ እንደማንኛውም ተማሪ ከክፍያው በፊት የተቋሙን የትምህርት መመዘኛ መስፈርቶች (Admission paper) ሲያገኝ ብቻ ይሆናል::

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
@News_For_Student
@News_For_Student
13.6K views09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-28 08:44:28
የ 12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ከሁለተኛው ዙር ፈተና በፊት አይገልጽም !

በመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 19-28 የተሰጠ ሲሆን ውጤቱ ከሁለተኛው ዙር ፈተና ጋር ተጠቃሎ ሚገለጽ ይሆናል

የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤታችሁን በትዕግስት እንድትጠብቁ እያሳሰብን ውጤት ሲለቀቅ በዚሁ @News_For_Student ቻነል የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

@News_For_Student
@News_For_Student
15.0K views05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-26 08:25:14
በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይተገበራል፡፡ -ትምህርት ሚኒስቴር

በ2016 ዓ.ም አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም የመንግሥት እና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚተገበር የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ከዓለም አቀፍና ከውጭ የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች በስተቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በሚያስተምሩ ሁሉም የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች እንደሚተገበር በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ስርዓተ ትምህርቱ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል እንዲሁም በትግራይ ክልል በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል እንደሚተገበር ተናግረዋል።

ስርዓተ ትምህርቱ ከሥራና የተግባር የትምህርት አይነቶች በስተቀር በሁሉም የቀለም ትምህርት ዓይነቶች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንደሚተገበር ጠቁመዋል፡፡ በሥራና የተግባር ትምህርት አይነቶች ላይ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ይተገበራል ብለዋል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ2015 ዓ. ም ጀምሮ መተግበር መጀመሩ ይታወቃል። #MoE

@News_For_Student
@News_For_Student
14.6K views05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-25 21:27:51
#Oromia

የ8ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ተደረገ።

የኦሮሚያ ክልል የ2015 የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ከክልሉ የትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የ2015 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም  ስማቸውን እና የID. ቁጥራቸውን በማስገባት ዉጤታችሁን ማየት እንደሚችሉ ቢሮው አሳውቋል።

Website:- https://oromia.ministry.et/#/result

@News_For_Student
@News_For_Student
13.9K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ