Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ፍሬሕይወት ታምሩን የቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ ሾሟል፡፡ ቦርዱ የኢ | ትምህርት ሚኒስቴር

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ፍሬሕይወት ታምሩን የቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ ሾሟል፡፡

ቦርዱ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ፍሬህይወት ታምሩን የቦርድ ሊቀመንበር አድርጎ መሾሙን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ደግሞ ከነሐሴ 24/2015 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን ገልጸዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) መሾማቸው ይታወቃል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ራስ ገዝ እንዲሆን በአዋጅ የተፈቀደ ቢሆንም፣ ሙሉ በሙሉ ራስገዝ ሆኖ ሥራ የሚጀምረው የሚተዳደርበት መመሪያዎች ዝግጅት ተጠናቀው ሲፀድቁ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሆን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

@News_For_Student
@News_For_Student