Get Mystery Box with random crypto!

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም አጋማሽ ድረስ ይፋ ይደረጋል። የ12ኛ ክፍል | ትምህርት ሚኒስቴር

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም አጋማሽ ድረስ ይፋ ይደረጋል።

የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም 2016 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ ይፋ እንደሚደረግ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።

በጥቅምት 2016 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመጀመር ዕቅድ መያዙንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በፀጥታ ችግር ምክንያት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ሦስት ፈተናዎች ያልወሰዱ ተማሪዎች በቅርቡ ፈተናቸውን ይወስዳሉም ብለዋል።

በ2015 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን ሲወስዱ የነበሩት የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች፣ የመጨረሻዎቹን ሦስት ፈተናዎች አለመፈተናቸው ይታወቃል።

እነዚህ ተማሪዎች በዚህ ዓመት መጨረሻ ድረስ ፈተናቸውን እንዲያሚያጠናቅቁ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በኦንላይን እንደሚሰጥም ጠቁመዋል።

@News_For_Student
@News_For_Student