Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናው መቼ ይሰጣል? ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የ12ኛ ክ | ትምህርት ሚኒስቴር

የ12ኛ ክፍል ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናው መቼ ይሰጣል?

ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለጹ ይታወቃል።

ተማሪዎቹ ፈተናውን እንዲወስዱ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ተናግረዋል።

ለዚህም የፈተና ህትመት፣ የሰው ኃይል እና የበጀት ዝግጅት እየደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ተማሪዎቹ በስነ-ልቦና ለፈተና ዝግጁ ሲሆኑ እንዲሁም ፈተናው በሚሰጥባቸው አካባቢዎች አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ መኖሩ ሲረጋገጥ "በአጭር ጊዜ ውስጥ" ፈተናው እንዲሰጥ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመዋል።

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለፈተና ተቀምጠው የመጨረሻ ቀናት ሦስት ፈተናዎችን ያልወሰዱ ተማሪዎች በዚህ ዓመት መጨረሻ ፈተናቸውን እንዲያሚያጠናቅቁ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) መናገራቸው ይታወሳል፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student