Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-02-18 11:01:37 በዚህ ቻናል ላይ ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ

• ሽያጮች (ልብስ, ጫማ, Electronics..)
• ድርጅት / ሱቅ
• የፀጉር, የፊት, የፂም ትሪትመንቶች
• የConsultancy companys
•  እንዲሁም ማስተዋወቅ ሚፈልጉትን ሁሉ ማስተዋወቅ ይችላሉ !
        
           ያናግሩን

         @News_Promotion_Bot
13.0K viewsedited  08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-15 18:52:18
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ እየተካሔደ ነው።

ተፈታኝ ተማሪዎችን የመመዝገብ ሥራ ከየካቲት 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 30/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል።

ምዝገባ የጀመሩ አካባቢዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ምዝገባ ያልተጀመረባቸው አካባቢዎች በቀጣይ ምዝገባውን እንደሚያካሒዱ የአገልግሎቱ ም/ዋ/ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ገልጸዋል።

በመደበኛ እና በማታ መርሐግብር የመልቀቂያ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች ይከናወናል የተባለ ሲሆን በግል፣ በርቀት እና በበይነ መረብ ተምረው የሚፈተኑ ተማሪዎች ምዝገባ በክ/ከተማ፣ በልዩ ወረዳ እና በወረዳ የትምህርት ጽ/ቤቶች እንደሚካሔድ ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በ2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ከ870 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ይጠበቃል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.6K views15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-25 22:03:43
#JimmaUniversity

በ2016 ዓ.ም ጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ጥር 27 እና 28/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦

የተፈጥሮ ሣይንስ ተማሪዎች በአጋሮ ካምፓስ (አጋሮ ከተማ) እና የማኅበራዊ ሣይንስ ተማሪዎች በጅማ ግብርናና እንስሳት ሕክምና ኮሌጅ (ጅማ ከተማ)

ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

➢ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➢ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➢ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.3K views19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-29 17:19:30
በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል በተፈጠረው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በ2016 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያዉ ወሰነ-ትምህርት ተማሪዎቻቸውን ለመጥራትና መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸዉን ሙሉ ለሙሉ ለመጀመር አልቻሉም ነበር ብሏል ሚኒስቴሩ።

በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር ከክልሉ ኮማንድፖስት፣ የጸጥታ አደረጃጀቶችና የሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን ሲያካሂድ መቆየቱ ተገልጿል።

" የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ፣ የአስሩ ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ ጸጥታ አካላት ትናንት ታህሳስ 18/2016 ዓ.ም በጉዳዩ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን አሁን በክልሉ አንጻራዊ ሰላም የተፈጠረ በመሆኑ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን መጥራትና ማስተማር እንደሚችሉ ውሳኔ ላይ ተደርሷል። " ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ከጥር 1/2016 ጀምሮ ባሉ ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን ጠርተው የመማር ማስተማር ስራቸውን ይጀምራሉ ተብሏል።

በመሆኑም በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲዎቹ የሚያደርጉትን ጥሪ እንዲከታተሉ ጥሪ ቀርቧል።

@News_For_Student
@News_For_Student
14.4K views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-26 17:28:40
በትግራይ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በዚህ ሳምንት ይሰጣል፡፡

ፈተናው ለሦስት ቀናት ከታህሳስ 18 አስከ 20/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ 60 ሺህ ተማሪዎች መመዝገባቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለጹ ይታወሳል፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
14.3K views14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-19 07:12:32
በ2016 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሐግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በየተመደባችሁበት የዩኒቨርሲቲው ካምፓስ ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 09 እና 10/2016 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡

ለመመዝገብ ከመሔዳችሁ በፊት https://portal.aau.edu.et ላይ በመግባት ➧ Freshman ➧ Student Profile የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የግል መረጃቻችሁን ማሟላታችሁን አትዘንጉ።

@News_For_Student
@News_For_Student
25.5K views04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-18 06:26:32
አክሱም ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ለተመደቡለት የሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ #ያላደረገ መሆኑን ገልጿል።

በመሆኑም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የ2016 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ተቋሙ ጥሪ እስከሚያደርግ በትዕግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

የመግቢያ ጊዜ በቀጣይ እንደሚገለፅም ዩኒቨርሲቲው ጠቁሟል።

@News_For_Student
@News_For_Student
21.9K views03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-13 17:15:06
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስኮቻቸው የፈቃድ ወቅታዊ መረጃን ይፋ አድርጓል፡፡

በአጠቃላይ የ 382 ተቋማት ወቅታዊ የፈቃድ መረጃን ይፋ የተደረገ ሲሆን፦

◉ 366 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
- 5 የግል ዩኒቨርሲቲዎች
- 6 የግል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች
- 6 ኢንስቲቲዩቶች
- 349 የግል ኮሌጆች

◉ 16 የመንግሥት ከ/ት/ተቋማት
- 4 የርቀት ትምህርት ፈቃድ የወሰዱ
- 12 የመደበኛ ትምህርት ፈቃድ የወሰዱ

የተቋማቱን የትምህርት መስኮች የፈቃድ ጊዜ ያለበትን ደረጃ ለማሳየት በየትምህርት መስኩ፣ በካምፓሱ እና በፈቃድ ጊዜው ላይ በአረንጓዴ፣ በቢጫ፣ በቀይ እና በወይን ጠጅ ቀለማት ምልክት ተደርጎበታል፡፡

አረንጓዴ የተደረገባቸው
- የፈቃድ ጊዜያቸው ከ6 ወራት በላይ የሚቆይ እና አዲስ ተማሪ መመዝገብ የሚችሉ

ቢጫ የተደረገባቸው
- የፈቃድ ጊዜያቸው ከ1 እስከ 6 ወር በላይ የሚቆይና አዲስ ተማሪ መመዝገብ የሚችሉ፡፡ ነገር ግን በቀሩት 6 ወራት ፈቃድ ሳያድሱ አዲስ ተማሪ መመዝገብ አይችሉም፡፡

ቀይ ቀለም የተደረገባቸው
- የፈቃድ ጊዜያቸው ያለፈ ስለሆነ አዲስ ተማሪ መመዝገብ አይችሉም፡፡ ፈቃድ አላደሱም፡፡

ወይን ጠጅ ቀለም የተደረገባቸው
- ያቋረጡ ስለሆነ አዲስ ተማሪ መመዝገብ አይችሉም፡፡ የተመዘገቡ ተማሪዎች ግን ማስጨረስ ይችላሉ፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ ያገኙበትን የትምህርት መስክ፣ ካምፓስ እና መርሐግብር አሟልቶ የያዘና በየጊዜው ወቅታዊ የሚደረግ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፦ https://bit.ly/43Z1Rck

@News_For_Student
@News_For_Student
26.3K viewsedited  14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-12 15:58:46
#MoE

የሪሚዲያል ፕሮግራም ምደባ መመልከቻ፦

በድረ-ገፅ፦
https://result.ethernet.edu.et

በቴሌግራም ቦት፦
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ #የማያስተናግድ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

@News_For_Student
@News_For_Student
22.1K views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-10 19:32:14
ማስታወቂያ፦

ከታች የተዘረዘሩት ዩኒቨርሲቲዎች በ2015 ዓ.ም ሪሜዲያል ተፈትነው በማለፍ በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ቆርጠው ይፋ አድርገዋል፦

@News_For_Student
@News_For_Student
22.0K views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ