Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2023-08-13 09:11:53
#EAES

የ2015 ዓ.ም ቀጣይ ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል።

በኢትዮጵያ ውስጥ በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ እንዲሁም በውጭ ሀገር ሆነው በኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት ለተማሩ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በነሐሴ ወር መጨረሻ የመልቀቂያ ፈተና ይሰጣል።

በተመሳሳይ በትግራይ ክልል ለሚገኙ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ.ም የመልቀቂያ ፈተናው እንደሚሰጥ አገልግሎቱ ጠቁሟል።

@News_For_Student
@News_For_Student
14.8K views06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-10 15:04:56
12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የነበሩና ወደየመጡበት መመለስ ያልቻሉ መምህራንን በቻርተርድ አውሮፕላን ከክልሉ ለማስወጣት ፈቃድ እየተጠበቀ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

የመልቀቂያ ፈተና ለመስጠት በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የነበሩ መምህራን ወደየመጡበት መመለስ ባለመቻላቸው ችግር ላይ እንደሚገኙ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በጎንደር እና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸውን የተናገሩት መምህራኑ፤ የተሰጣቸውን አበል እንደጨረሱና የዕለት ምግብና መጠጥ ለማግኘት እንዳልቻሉም ገልጸዋል፡፡

የሚመለከታቸው አካላት ይታደጉን ሲሉ የተማፀኑት መምህራኑ፤ መንግሥት በአፋጣኝ ካሉበት የፀጥታ ስጋት አውጥቶ ወደየመጡበት እንዲመልሳቸውም ጠይቀዋል፡፡

መምህራኑን ካሉበት አውጥቶ ወደየመጡበት ለመመለስ እየሠራ እንደሚገኝ የትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡
 
መምህራኑ የደህንነት ችግር እነዳይደርስባቸው ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት መደረጉን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

"በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ላሉ መምህራን ህብረተሰቡ ምግብ እያቀረበ ነው" ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ መምህራኑ ከክልሉ በአፋጣኝ የሚወጡበት መንገድ እየተመቻቸ ነው ብለዋል፡፡

መምህራኑን በቅርብ ጊዜ ውስጥ በቻርተርድ አውሮፕላን ለማስወጣት የሚመለከተው አካል ፈቃድ እየተጠበቀ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ውጪ መመህራኑ ካሉበት ለመውጣት ሲሉ የደህንነት ዋስትና የሌለው አማራጭ እንዳይጠቀሙ ዋና ዳይሬክተሩ አሳስብዋል፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
18.5K views12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-09 17:26:13
በተለያዩ የጤና ሙያ መስኮች ሰኔ 30/2015 ዓ.ም የመውጫ እና የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ ውጤታችሁን ከነገ ጀምሮ ማየት ትችላላችሁ፡፡

ዳግም ተመዛኞች hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስምና በጤና ሚኒስቴር የተሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን ከነሐሴ 04/2015 ዓ.ም ጀምሮ መመልከት እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡

አዲስ ተመዛኞች (በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ምዝገባ ያካሄዳችሁ በሙሉ) በትምህርት ሚኒስቴር የማለፊያ ነጥብ አሟልታችሁ ዲግሪ መያዝና የጤና ሚኒስቴርን የማለፊያ ነጥብ ማሟላት የሚጠበቅባችሁ ሲሆን ሁለቱንም መስፈርቶች አሟልታችሁ ያለፋችሁ ተመዛኞች ስም ዝርዝራችሁ ለክልል የጤና ተቆጣጣሪ አካላት የሚላክ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የተለያዩ ጥያቄዎች ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0118275936 ወይም በኢ-ሜይል hpcald@moh.gov.et ላይ ሙሉ ስም፣ ሙያ፣ የፈተና መለያ ቁጥር እና የተማራችሁበትን ተቋም በማስቀደም ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ በአካል የሚቀርቡ ጥያቄዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
16.1K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-09 10:03:19
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የሬሚዲያል ተማሪዎችን ውጤት ይፋ አድርጓል።

ውጤት ለመመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦

https://portal.du.edu.et/NewStudents/Remedial?fbclid=IwAR0tmFAZBkIWj5GWjbHJ01If_B__jShKfGX8MgQdevTeSBXBqwBTF7Zyx8A

Note:

➧ "Academic Year" በሚለው ቦታ 2022/23 የሚለውን ይምረጡ፣

➧ "Student ID No." በሚለው ቦታ የዩኒቨርሲቲውን ID ቁጥራችሁን ወይም የ12ኛ ክፍል Registration No በመጠቀም ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ።

@News_For_Student
@News_For_Student
15.7K views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-07 08:01:28
#ArbaminchUniversity

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial) ውጤት ይፋ አደረገ።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial) ማጠቃለያ ውጤት በመረጃ መረብ (Online) መለቀቁን አሳውቋል።

ተማሪዎች ከታች የቀረበውን ሊንክ በመጫን (ወይም ሊንኩን በዌብ ፔጅ ላይ ኮፒ-ፔስት በማድረግ)፣ መለያ ቁጥር (ID Number) በማስገባት፣ Search እና View Result በመጫን ማየት ይችላሉ ተብሏል።

በውጤቱ ላይ ቅሬታ ያለው ተማሪ ካለ ከሰኞ እስከ ረቡዕ (ከነሐሴ 1 እስከ 3/ 2015 ዓ.ም) ባለው ጊዜ ውስጥ አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተር ቢሮ (የአምዩ አስተዳደር ሕንጻ 2ኛ ፎቅ) ማመልከት ይችላል ተብሏል።

https://survey.amu.edu.et/remedial/

ተቋሙ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚቀርብ የቅሬታ ማመልከቻ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አሳውቋል።

መረጃው ፦ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ነው።

@News_For_Student
@News_For_Student
17.8K views05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 21:14:12 የ3 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሆኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ለመውጫ ፈተና ወደ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንደተመደቡ ከተነገራቸውና ወደዛው ካቀኑ በኃላ ዛሬ አመሻሹን ደግሞ አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ መሆኑና ነገ ጥዋት 1 ሰዓት እንዲደርሱ እንደተናገራቸው ጠቁመዋል።

እነዚህ ተማሪዎች የአልካን፣ የልደታ፣ እና የአፍሪካ የፋርማሲ ተማሪዎች ናቸው።

ተማሪዎቹ ወደ አዳማ እንዲሄዱ ሲነገራቸው እያንዳንዱን ወጪ ምግብ፣ እና ትራንስፖርት ጨምሮ እራሳቸው እንደሚሸፍኑ ተነግሯቸው እንደነበር ለቲክቫህ ጠቁመዋል።

አዳማ እንዲደርሱ የተነገራቸው 8 ሰዓት ላይ ሲሆን እዛ ከደረሱ በኃላ የመለማመጃ ፈተና እንደሚፈተኑ፣ የመፈተኛ ክፍላቸውን እንደሚያውቁ፣ ID እንደሚሰጣቸው ተነግሯቸው ነበር ፤ ነገር ግን እኚህ ሁሉ ተማሪዎች የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች ይዘው አዳማ ከደረሱ በኃላ ቦታው መቀየሩንና ነገ ጥዋት አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ግቢ እንዲደርሱ እንደተነገራቸው ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ እንዲህ ያለው እጅግ በጣም ያልተገባ ድርጊት እንዳሳዘናቸው ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ፈተናው በተቃረበበት በዚህ ወቅት መሰል የተንዛዛ አሰራር በፍፁም ሊኖር እንደማይገባና የሚማለከተው አካል የመፍትሄ እርምጃዎችን እንዲወስድ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

በነገው ዕለት ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ እንደተዘጋጁ መልዕክት የላኩ ተማሪዎች እዛም ሲደርሱ እንዲህ ያለውን ነገር እንዳይገጥማቸው ስጋት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

በዚህ አይነት ሁኔታ በፈተና አወሳሰድ ሂደቱ ላይ ችግሮች ቢያጋጥማቸው ተጠያቂነት ሊኖር እንደሚገባ አመልክተዋል።

የተማሪዎቹን ጥያቄ በተመለከተ የተቋሞቻቸውን ኃላፊዎች ለማግኘት ጥረት ብናደርግም አልተሳካም ምላሽ አለኝ የሚል አካል ምላሹን መስጠት ይችላል።

@News_For_Student
@News_For_Student
2.6K views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 20:36:09
ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በድጋሚ ማሳሰቢያ ተሰጣቸው።

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ወደሚያስፈትኑበት የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመሔድ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያጠናቅቁ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በድጋሜ አሳስቧል።

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የሚያስፈትኗቸውን ተማሪዎች ፦

- ፎቶ፣
- የይለፍ ቃል፣
- የተጠቃሚ ሥም እና የትምህርት ቤት ህጋዊ መታወቂያ በመያዝ ወደተመደቡበት ተቋም በመሔድ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ አስታውሷል።

ባለስሥልጣን መስሪያ ቤቱ ፤ በአሁኑ ወቅት ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረሶኛል ባለው መረጃ መሰረት ከላይ የተዘረዘሩ ጉዳዮችን በማሟላት ያቀረቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አነስተኛ ናቸው።

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ አላስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች ባለማሟላታቸው ምክንያት ተማሪዎች ለፈተና የማይቀመጡበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ባለሥልጣኑ ገልጿል።

በዚህም ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊነት የሚወስዱ መሆኑን ባለሥልጣኑ ጠቁሟል።

(ባለሥልጣኑ ዛሬ ያወጣው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።)

@News_For_Student
@News_For_Student
3.3K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 17:45:48
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች እየተሰጠ የሚገኘው መልቀቂያ ፈተና አራተኛ ቀኑን ይዟል።

የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ መስክ ተፈታኝ ተማሪዎች ዛሬ የእንግሊዝኛ ትምህርት ፈተና ወስደዋል።

የሪሚዲያል ፈተናው ነገ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም በሚሰጠው የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና ይጠናቀቃል፡፡

የሪሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 26/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን የመጀመሪያ ቀን የተሰጡ የሪሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች (ፊዚክስ እና ታሪክ) እንዲሰረዙና ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ የትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑን ይታወቃል።

@News_For_Student
@News_For_Student
4.7K views14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 16:13:36
በትግራይ ክልል የስምንተኛ ክፍል ፈተና ለሁለተኛ ቀን እየተሰጠ ነው።

ፈተናው በክልሉ በ75 ወረዳዎች በ1,007 ትምህርት ቤቶች እስከ ነገ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል።

ከ60 ሺህ በላይ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን እነወሰዱ ነው የተባለ ሲሆን በ518 ትምህርት ቤቶች ፈተናውን መስጠት አለመቻሉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

@News_For_Student
@News_For_Student
5.1K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 18:08:47
በደቡብ ክልል ለሌሎች ተማሪዎች የስምንተኛ ክፍል ፈተና ሊፈተኑ የሞከሩ ሁለት የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በደቡብ ኦሞ ዞን ሁለት የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ለሌሎች የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ለመፈተን ሲሞክሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ሌላ ሰው እንዲፈተንላቸው የመለያ ቁጥራቸን የሰጡ ሁለት ተማሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

አራቱ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

በክልሉ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ለሁለት ተከታታይ ቀናት ተሰጥቶ ትላንት ተጠናቋል።

@News_For_Student
@News_For_Student
8.1K views15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ