Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2023-06-05 09:11:59
ራያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአካል ቀርበው እንዲመዘገቡ ጥሪ አቀረበ።

ራያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና ተከታታይ ትምህርት መርሐ ግብር ትምህርታቸውን ለመከታተል ቀደም ሲል ዩኒቨርሲቲዉ ባወጣዉ ማስታወቅያ መሰረት የተመዘገቡ (የዩኒቨርሲቲዉና ከሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያመለከቱ) ተማሪዎች ሰኔ 6 እና 7 / 2015 ዓ.ም በራያ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት በአካል በመገኘት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።

@News_for_student
@News_for_student
5.5K viewsedited  06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 09:39:02
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች ምረቃ

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ከሐምሌ 10 እስከ 17/2015 ዓ.ም ማካሄድ እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የሚሳተፉ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች ብቻ እንደሚሆኑ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች የተላከ ደብዳቤ ያሳያል፡፡

@News_for_student
@News_for_student
6.9K views06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 09:48:56 አገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡባቸው እና የምረቃ ቀናት እንዲሁም የሬሜዲያ ፈተና ወጤት አያያዝ ላይ ቅያሪ ተደርጓል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ/ም ያስተላለፈውን ሴርኩላር በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልል ት/ቢሮ አመራሮች ጋር በድጋሚ ግንቦት 22 ቀን 2015 በበይነ-መረብ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ መሰረትም ፦

- ፈተናዎች የሚሰጡባቸው ቀናት፣

- የተማሪዎች ምረቃ በዓል፣

- የሪሜዲያል ፈተና ውጤት አያያዝ በተመለከተ ቅያሪ መደረጉን ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች በፃፈው ደብዳቤ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ የተላከውን ደብዳቤ #ትክክለኝነት ከሚመለከታቸው አካላት አረጋግጧል።

በዚህም ፦

- በ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ ፤ ተቋማት ፊተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 30 ከመቶ፣ #በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 70 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደት እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

- በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ ውጤት ሐምሌ 10 ቀን የሚገልጽ ይሆናል ተብሏል።

- የተማሪዎችን ምረቃ በተመለከተ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ ማካሄድ የሚቻል መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ ናቸው ብሏል።

- የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 16 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

@News_for_student
@News_for_student
13.4K viewsedited  06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 07:18:17
በ2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከሐምሌ 03 እስከ 13 /2015 ዓ.ም እንደሚከናወን ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ያደረገውን ወይይት ተከትሎ አገር አቀፍ የመውጫ ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡ በዚህም፡-

➤ በሰኔ 2015 ዓ.ም ሞዴል የመውጫ ፈተና ይሰጣል።

➤ የመውጫ ፈተናው ከሐምሌ 03 እስከ 08/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

➤ ውጤት ከሐምሌ 09 እስከ 10/2015 ዓ.ም በተቋማቱ ይገለጻል፡፡ (ተማሪዎች ከሐምሌ 08 ጀምሮ የፈተና ቁጥራቸውን በማስገባት ኦንላይን ማየት ይችላሉ።)

➤ የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ከሐምሌ 10 እስከ 17/2015 ዓ.ም ይከናወናል፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት

@News_for_student
@News_for_student
12.5K views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 07:18:58
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በአንድ ጊዜ 600 ተፈታኞችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ የፈተና ማዕከል እያደራጀ መሆኑን ገለጸ።

ማዕከሉ ከሐምሌ 03 እስከ 13/2015 ዓ.ም በኦንላይን ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ዝግጁ ይሆናል ተብሏል፡፡

በዩኒቨርሲቲው በመደበኛ፣ በርቀት እና በክረምት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ ከ3 ሺህ በላይ የ2015 እጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን እንደሚወስዱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ለመውጫ ፈተናው የተለያዩ ዝግጅቶች እያደረገ መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፤ ለተፈናው ጥቅም ላይ የሚውል መተግበሪያ ሶፍትዌር በዩኒቨርሲቲው የአይሲቲ ባለሙያዎች መልማቱንም ተናግረዋል።

@News_for_student
@News_for_student
11.2K views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 18:45:54
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የኦዲት ምርመራ

የ2013 ሂሳባቸው ኦዲት ከተደረገ 37 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ “ምንም ጉድለት ያልተገኘባቸው” ሁለቱ ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

ኦዲት ከተከናወነባቸው 37 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ 18 ያህሉ ወይም 48.6 በመቶ የሚሆኑት “ተቀባይነት የሚያሳጣ” ደረጃ ላይ እንደሆኑ ተረጋግጧል ብሏል ሚኒስቴሩ።

የኦዲት ምርመራ ከተደረገባቸው መካከል “ጥቂት ጉድለት” የተገኘባቸው 17 ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ማክሰኞ በተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

ከ37ቱ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ “ምንም ጉድለት” እንደሌለባቸው የተረጋገጡት ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ መሆናቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ “የእርምት እርምጃ ለመውሰድ እና ማስተካከያ ለማድረግ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመወያየት አቅጣጫ” ማስቀመጡንም ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

“በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ማስተካከያ ስለመደረጉ ተገቢው ክትትል እና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል” ብለዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@News_for_student
@News_for_student
12.0K views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-27 06:26:25
በ2014 ዓ.ም የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የነበሩና በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማጠናከሪያ ትምህርት ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች የሪሚዲያል ፈተና የሚሰጠው ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም እንደሆነ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በቀን ግንቦት 15/2015 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሰራጨው ደብዳቤ፤ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ፈተናውን ውጤታማ በሆነ ሁኔታ እንዲሰጡ አሳስቧል።

@News_for_student
@News_for_student
12.5K viewsedited  03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 06:55:02
የዩኒቨርሲቲዎች የምግብ በጀት ጥያቄ

ዩኒቨርሲቲዎች በቀን አንድ ተማሪ ለመመገብ በመንግሥት የተመደበላቸው 22 ብር በጀት በቂ አለመሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

በተሻሻለው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የምግብ የበጀት ተመን፤ ዩኒቨርሲቲዎች አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ 22 ብር ብቻ ተመድቦላቸዋል።

ይሁን እንጂ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከተለያዩ በጀቶች በማዛወር እስከ 80 ብር በመመደብ ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ እንደሚገኙ ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልጸዋል።

ይህን በማድረጋቸውም የተቋማቱ የኦዲት ግኝት ላይ ተጽዕኖ እያደረገባቸው እንደሆነም ሚኒስትሩ አመልክተዋል።

በዚህ ሁኔታ መቀጠል አይቻልም የተባለ ሲሆን ለምግብ በጀት እጥረቱ መፍትሔ ለማበጀት ሚኒስቴሩ አማራጭ የፋይናንስ መንገዶችን እያጠና መሆኑን ገልጿል።

@News_for_student
@News_for_student
11.5K views03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 09:24:52
ኢትዮጵያን ወክለው በ7ኛው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር የሚሳተፉ ዘጠኝ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ቻይና አቅንተዋል፡፡

ውድድሩ (Huawei ICT Competition 2022-2023 Global Final) ከግንቦት 16 እስከ 20/2015 ዓ.ም በቻይና ሼንዘን ከተማ ይካሄዳል፡፡

ተማሪዎቹ በመጨረሻው ዙር ዓለም አቅፍ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ ቻይና ያቀኑት፤ የተለያዩ አገር አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ውድድሮች ላይ ተሳትፈው በየደረጃው በአሸናፊነት ማጠናቀቃቸው ተከትሎ ነው።

ዘጠኙ ተማሪዎች ከጎንደር፣ ዋቸሞ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች የተገኙ ናቸው።

@News_for_student
@News_for_student
11.6K views06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-23 14:52:27
ዘንድሮ 240 ሺህ ሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ

በ2015 በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተሰበሰበው መረጀ መሠረት 240 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች በበይነ-መረብ የመውጫ ፈተና ለመስጠት መዘጋጀቱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቋል።

ሚኒስቴሩ ይህ ያስታወቀው የ9 ወራት የአፈፃፀም ሪፖርቱን ለህ/ተ/ም/ቤት እያቀረበ በሚገኝበት በአሁን ሰዓት ነው።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ በ2015 በመጀመሪያ ዲግሪ ኘሮግራም ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ብሉ -ኘሪንት የተዘጋጀ መሆኑና የመውጫ ፈተና የክፍያ ተመን ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱን ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት አብራርተዋል።

የመውጫ ፈተናን ለመተግበር የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱንም የገለፁት ሚኒስትሩ፤ የመውጫ ፈተና ስትራቴጂ ማስፈፀሚያ መመሪያ እና የድርጊት መርሃ-ግብር ዝግጅት መጠናቀቁንም አብራርተዋል።

በመውጫ ፈተና የሚካተቱ የትምህርት ዓይነቶች (ኮርሶች) ተለይተው፤ በቅድመ-ምረቃ በሚሰጡ በሁሉም የትምህርት መስኮት የፈተና ንድፍ ማሳያ መዘጋጀቱንም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል።

@News_for_student
@News_for_student
13.0K views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ