Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 23

2023-03-06 14:04:29
#JimmaUniversity

በ2015 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ እና የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 29 እና 30/2015 ዓ.ም በየተመደባችሁበት ካምፓስ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ10ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
➧ የ12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
➧ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡

የተመደባችሁበትን ካምፓስ ለማየት ተከታዩን ሊንክ ተጠቀሙ ➧ https://portal.ju.edu.et

@News_for_student
@News_for_Student
8.4K views11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 13:33:56
#WallagaUniversity

በ2015 ዓ.ም በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል የትምህርት ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን መጋቢት 7 እና 8/ 2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።


የምዝገባ ቦታ፦

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ➧ ነቀምቴ ካምፓስ

የማህበራዊ ሳይንስ ስማችሁ ከM-Z የሚጀምር ተማሪዎች ➧ ነቀምቴ ካምፓስ

የማህበራዊ ሳይንስ ስማችሁ ከA-L የሚጀምር ተማሪዎች ➧ ጊምቢ ካምፓስ

@News_for_Student
@News_for_Student
8.7K views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 11:30:43
#WolaitaSodoUniversity

በ2015 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ መጋቢት 1 እና 2/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት የሚጀመረው ➧ መጋቢት 4/2015 ዓ.ም

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ መሰናዶ ያለፋችሁበት ሰርተፍኬት፣
➧ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➧ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣
➧ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፣

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።
@News_for_Student
@News_for_Student
9.6K views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 06:31:20
#BahirDarUniversity

በ2015 ዓ.ም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ የካቲት 29 እና 30/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ ➧
በሰላም ካምፓስ እና በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ካምፓስ

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧የ8ኛ ክፍል ካርድ፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➧ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➧ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል።)

@News_for_Student
@News_for_Student
10.7K views03:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 16:01:40
የ2015 ዓ/ም ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆኗል።

በዚህ አመት የተዘጋጀው መቁረጨ ነጥብ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተሰላ በመሆኑ የሚያገለግለው ለ2015 ዓ.ም የስልጠና ዘመን ብቻ መሆኑን ተገልጿል።

በ2013/2014 የሥልጠና ዘመን በተለየየ ምክንያት ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ያልገቡ ተማሪዎች የሚስተናገዱት በ2014 ዓ.ም በነበረው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ይሆናል ተብሏል።

(የ2015 ዓ/ም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ውጤት ከላይ ተያይዟል)

ምንጭ፦ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር

@News_for_Student
@News_for_Student
13.1K views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 09:23:11
#DireDawaUniversity

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ መደበኛ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን ላለፉት ሁለት ቀናት ተቀብሏል።

መንግስት ከ1 ሺህ 500 በላይ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መመደቡ ይታወቃል።

@News_for_Student
@News_for_Student
11.5K views06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 21:33:40
ትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች የላፕቶፕ ሽልማት አበርክቷል።

መንግስት ለተማሪዎቹ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የስኮላርሺፕ ዕድል ማመቻቸቱንም አሳውቋል።

በርካታ ተማሪዎችን ያሳለፉ 20 ትምህርት ቤቶችም የዕውቅና ሰርተፊኬት እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
@News_for_Student
@News_for_Student
11.9K views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 16:43:26
#DebreMarkosUniversity

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ መደበኛ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው በ2015 ዓ.ም በመደበኛ መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ የካቲት 20 እስከ 21/2015 ዓ.ም እንደሆነ መግለጹ ይታወቃል።

መንግስት ከ1 ሺህ 300 በላይ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መመደቡ ይታወቃል።

@News_for_Student
@News_for_Student
11.9K views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 10:19:27
" የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ አላስተናግድም " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ከትላንትና ምሽት ጀምሮ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ምደባ ይፋ አድርጎ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ እየተመለከቱ ይገኛሉ።

በ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የተቋም ምደባቸውን 

- በWebsite: https://placement.ethernet.edu.et
- SMS: 9444 ላይ ነው እየተመለከቱ የሚገኙት።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ትምህርት ሚኒስቴር " የተቋም ይቀየርልኝ " ጥያቄ እንደማያስተናግድ አሳስቧል።

እንደትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ አጠቃላይ 106 ሺህ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ የትምህርት ፕሮግራም ላይ ተካተዋል፡፡

የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራሙ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ውጪ ባሉ ሁሉም የመንግስት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል።

@News_for_Student
@News_for_Student
13.1K views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 19:47:41
#ማስታወቂያ

የRemedial ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑንና በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋሞች በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ እንገልፃለን ።

ማሳሰቢያ :-
የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን።

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

Website:

https://placement.ethernet.edu.et
SMS: 9444

ትምህርት ሚኒስቴር
@News_for_Student
@News_for_Student
13.5K views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ