Get Mystery Box with random crypto!

' የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ አላስተናግድም ' - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር ከትላንትና | ትምህርት ሚኒስቴር

" የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ አላስተናግድም " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ከትላንትና ምሽት ጀምሮ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ምደባ ይፋ አድርጎ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ እየተመለከቱ ይገኛሉ።

በ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የተቋም ምደባቸውን 

- በWebsite: https://placement.ethernet.edu.et
- SMS: 9444 ላይ ነው እየተመለከቱ የሚገኙት።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ትምህርት ሚኒስቴር " የተቋም ይቀየርልኝ " ጥያቄ እንደማያስተናግድ አሳስቧል።

እንደትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ አጠቃላይ 106 ሺህ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ የትምህርት ፕሮግራም ላይ ተካተዋል፡፡

የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራሙ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ውጪ ባሉ ሁሉም የመንግስት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል።

@News_for_Student
@News_for_Student