Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 18

2023-04-29 07:58:34
#MoH

ጤና ሚኒስቴር በግንቦት 2015 ዓ.ም ለሚሰጠው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ምዝገባው እስከ ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም ብቻ ይከናወናል።

የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ተቋማት ተመዛኞች hple.moh.gov.et ላይ በመግባት በኦንላይን እንድትመዘገቡ ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ከተጠቀሰው ጊዜ ውጪ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ #የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

የግል ትምህርት ተቋማት አዲስ ተመዛኞች ከምዝገባ በፊት የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በማረጋገጥ ስማችሁን ወደ ጤና ሚኒስቴር ማስላክ ይጠበቅባችኋል፡፡

ማንኛውም ተመዛኝ ምዝገባ ሲያደርግ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር የያዘ ወረቀት (ስሊፕ) print አድርጎ መያዝ ይጠበቅበታል። #ጤና_ሚኒስቴር

@News_for_student
@News_for_student
5.2K views04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 12:56:25
#ያስታውሱ

የ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ ሚያዝያ 20/2015 ዓ.ም ከሰዓት 11:30 ይጠናቀቃል።

ከዛሬ 11:30 በኋላ በግለሰብም ሆነ በተቋም የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን #እንደማያስተናግድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማሳወቁ አይዘነጋም።

@News_for_student
@News_for_student
5.8K viewsedited  09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 17:49:35
" የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና  ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

ፈተናው ልክ እንደባለፈው አመት በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን  አብራርተዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በ2016 ዓ.ም የሚካሄደው ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸው የእለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡

ምንጭ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@News_for_student
@News_for_student
8.7K views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 09:38:38
የ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ነገ ሚያዝያ 20/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

ምዝገባው ከመጋቢት 20/2015 ዓ.ም ጀምሮ በኦንላይን ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል።

ከሚያዚያ 20/2015 ዓ.ም በኋላ በግለሰብም ሆነ በተቋም የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን እንደማያስተናግድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማሳወቁ አይዘነጋም።

@News_for_student
@News_for_student
6.6K views06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 11:30:41
ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ለአምስት ቀናት ተራዝሟል።

ምዝገባው ከመጋቢት 20/2015 ዓ.ም ጀምሮ በኦንላይን ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል።

የተፈታኞቹ ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንደሚካሄድ የትምህትርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ከሚያዚያ 20/2015 ዓ.ም በኋላ በግለሰብም ሆነ በተቋም የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን #የማያስተናግድ መሆኑን አገልግሎቱ አሳስቧል።

በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ2015 ትምህርት ዘመን ፈተና የመፈተኛ ጊዜን ከምዝገባው መጠናቀቀ በኋላ የሚገለጽ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

@News_for_student
@News_for_student
4.6K views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 12:26:26
#AASTU

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ በሴሚሰተሩ አጋማሽ ላይ የተመዘገባችሁ ተማሪዎች የመጀመሪያው ዓመት የመጀመሪያው ቀን ትምህርት የሚጀመረው ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

@News_for_student
@News_for_student
2.2K views09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 08:26:07
በትግራይ ክልል መደበኛ ትምህርት ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም ይጀመራል።

በትግራይ ክልል ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል መደበኛ ትምህርት ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም እንደሚጀመር የጊዜያዊ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የጊዜያዊ መንግስት በተቋቋመባቸው የክልሉ አካባቢዎች መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንደሚጀመር የቢሮው ኃላፊ ኪሮስ ጉኡሽ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

"በክልሉ ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ 2.4 ሚሊዮን ተማሪዎችን ወደ ትምህርታቸው ለመመለስ ምዝገባ እንደሚደረግ" ኃላፊው ገልጸዋል።

@News_for_student
@News_for_student
2.4K views05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 07:05:44
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገባችሁና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት የተሰጠውን ነፃ የትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ ተማሪዎች በተከታዩ ሊንክ አማካይነት የማመልከቻ ፎርሙን መሙላት ትችላላችሁ፦

http://survey.ethernet.edu.et/index.php/518562?lang=en

የማመልከቻ ፎርሙን መሙላት የሚቻለው ከዛሬ ሚያዝያ 09 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ቀናት ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

በማመልከቻ ፎርሙ ልትሞሏቸው የሚገቡ፦

➧ የ12ኛ ክፍል ውጤት ኮፒ፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኮፒ፣
➧ ግለ ታሪክ (CV) ኮፒ፣
➧ የልደት የምስክር ወረቀት ኮፒ እና
➧ ሌሎች በፎርሙ የተጠቀሱ መረጃዎች።

መረጃዎቹ ተጣርተው ለፈተና የሚቀረቡ ተማሪዎችን ዝርዝር በቀጣይ እንደሚያሳውቅ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

@News_for_student
@News_for_student
2.8K views04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 20:16:17
የጤና ሚኒስቴር በ10ኛ ዙር የሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከወሰዱ ውስጥ 45.7 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ማለፋቸው ተገለጸ።

ሚኒስቴሩ በ2015 ዓ.ም ጥር ወር የሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ውጤት ይፋ አድርጓል።

ለፈተና ከተቀመጡቱ 19,681 ውስጥ 8,993 ተፈታኞች ፈተናውን ያለፉ ሲሆን ይህም 45.7 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ማለፋቸውን ያሳያል፡፡

የብቃት ምዘና ፈተናውን ከወሰዱ የመንግስት ተማሪዎች ውስጥ 60.7 በመቶ የሚሆኑት ያለፉ ሲሆን በግል ከተፈተኑ ተማሪዎች ደግሞ 34.5 በመቶ የሚሆኑት ማለፋቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

በአጠቃላይ 21 ሺ ባለሙያዎች ለፈተና የተመዘገቡ ሲሆን 19,681 ተመዛኞች ፈተናውን መውሰዳቸው ታውቋል።

ሞባይል ስልክ እና ለሌላ ሰው ለመፈተን የሞከሩ 40 ተፈታኞች ከፈተናው እንዲታገዱ መደረጉም ተገልጿል።

@News_for_student
@News_for_student
452 viewsedited  17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 09:21:59
#AddisAbabaEducationBureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሞዴል ፈተና ለ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች እየሰጠ ነው።

ሞዴል ፈተናው ዛሬ መጋቢት 29/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀው ሞዴል ፈተናው፤ ተማሪዎች ራሳቸውን ለዋናው ፈተና ዝግጁ እንዲያደርጉ ያስችላል ተብሏል።

@News_for_student
@News_for_student
1.5K views06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ