Get Mystery Box with random crypto!

የጤና ሚኒስቴር በ10ኛ ዙር የሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከወሰዱ ውስጥ 45.7 | ትምህርት ሚኒስቴር

የጤና ሚኒስቴር በ10ኛ ዙር የሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከወሰዱ ውስጥ 45.7 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ማለፋቸው ተገለጸ።

ሚኒስቴሩ በ2015 ዓ.ም ጥር ወር የሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ውጤት ይፋ አድርጓል።

ለፈተና ከተቀመጡቱ 19,681 ውስጥ 8,993 ተፈታኞች ፈተናውን ያለፉ ሲሆን ይህም 45.7 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ማለፋቸውን ያሳያል፡፡

የብቃት ምዘና ፈተናውን ከወሰዱ የመንግስት ተማሪዎች ውስጥ 60.7 በመቶ የሚሆኑት ያለፉ ሲሆን በግል ከተፈተኑ ተማሪዎች ደግሞ 34.5 በመቶ የሚሆኑት ማለፋቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

በአጠቃላይ 21 ሺ ባለሙያዎች ለፈተና የተመዘገቡ ሲሆን 19,681 ተመዛኞች ፈተናውን መውሰዳቸው ታውቋል።

ሞባይል ስልክ እና ለሌላ ሰው ለመፈተን የሞከሩ 40 ተፈታኞች ከፈተናው እንዲታገዱ መደረጉም ተገልጿል።

@News_for_student
@News_for_student