Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 24

2023-02-24 12:30:35
106 ሺህ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ የትምህርት ፕሮግራም ተካተዋል፡፡

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው ከ50 በመቶ በታች ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለአራት ወራት ያህል በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ይሳተፋሉ፡፡

የ Remedial ፕሮግራሙ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ውጪ ባሉ ሁሉም የመንግስት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች እና ፕሮፌሰሮች ኮሚቴ በማዋቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉት የትምህርት አይነት ይዘቶችን መለየቱን በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራሙ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ እንግሊዘኛ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና ሂሳብ የትምህርት አይነቶችን የሚወስዱ ሲሆን፤ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ እንግሊዘኛ፣ ማህበራዊ ሳይንስና ሂሳብ ትምህርት አይነቶችን እንደሚወስዱ መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ይዘቶቹን መሰረት አድርጎ በተቋማት የሚዘጋጅ (ከ30 በመቶ) እና በማዕከል የሚዘጋጅ (ከ70 በመቶ) የሚያዝ ፈተና በመፈተን በድምሩ 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ የሚያገኙ ተማሪዎች መደበኛ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመንግስት እና በግል ዩኒቨርሲቲዎች መቀጠል ይችላሉ ብለዋል፡፡

@News_for_Student
@News_for_Student
14.3K views09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 16:31:58
#ማስታወቂያ የአቅም ማሻሻያ (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያ ጊዜ መራዘሙን ስለማሳወቅ

በ 2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንድትችሉ ቀኑ የተራዘመ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴር!
@News_for_Student
@News_for_Student
15.6K views13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 10:32:25
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ የካቲት 15 እና 16/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
 
በየተመደባችሁበት ካምፓሶች ለምዝገባ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➧ ጉርድ ፎቶግራፍ (8)፣
➧ ብርድልብስና አንሶላ፣
➧ የስፖርት ትጥቅ።

ከተገለጹት ቀናት በፊት ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት #እንደማይሰጥ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

➤ በአዲስ አበባ የምትኖሩ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉት ➧የካቲት 17/2015 ዓ.ም

➤ የመልሶ ቅበላ አመልካቾች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ
➧ከየካቲት 15 እስከ 17/2015 ዓ.ም
@News_for_Student
@News_for_Student
14.3K views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 12:48:10
#ማስታወቂያ

በ2015 ትምህርት ዘመን ከትምህርት መስክ እና ተቋም ምደባ ጋር ተያይዞ የቀረቡ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ምላሽ በ

https://placement.ethernet.edu.et

ማየት የምትችሉ መሆኑንና ከዚህ በኋላ ከምደባ ጋር የተያያዘ ምንም አይነት ቅሬታ የማናስተናግድ መሆኑን እንገለጻለን።

ተማሪዎች የትምህርት ጥራትን ለማረጋጋጥ የጀመርናቸው የሪፎርም ሥራዎች እንዲሳኩ የበኩላችሁን እንድትወጡ እያልን በተመደባችሁበት የትምህርት መስክ እና ተቋም ህልማችሁ እንዲሳካና በቀጣይ ጠንካራ አገር ለመገንባት እንደ ህዝብ ለጀመርነው ተግባር ተገቢውን እውቀትና አስተውሎት የምትይዙበት ዘመን እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ እንመኝላችኋለን።

ትምህርት ሚኒስቴር!
@News_for_Student
@News_for_Student
17.2K viewsedited  09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ