Get Mystery Box with random crypto!

#ማስታወቂያ የአቅም ማሻሻያ (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያ ጊዜ መራዘሙ | ትምህርት ሚኒስቴር

#ማስታወቂያ የአቅም ማሻሻያ (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያ ጊዜ መራዘሙን ስለማሳወቅ

በ 2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንድትችሉ ቀኑ የተራዘመ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴር!
@News_for_Student
@News_for_Student