Get Mystery Box with random crypto!

አርአያ ተስፋማርያም/Araya Tesfemariam

የቴሌግራም ቻናል አርማ arayanews — አርአያ ተስፋማርያም/Araya Tesfemariam
የቴሌግራም ቻናል አርማ arayanews — አርአያ ተስፋማርያም/Araya Tesfemariam
የሰርጥ አድራሻ: @arayanews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.86K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች🇪🇹

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-02-27 18:51:37
የመከላከያ ሰራዊት ለሀገራዊ ደኅንነት የመጨረሻው ምሽግ በመሆኑ ለሕዝባችን እና ሀገራችን ደኅንነት ሁልጊዜም እንሠራለን ሲሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ፡፡
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ የአየር ጥበቃ ፖሊስ አባላቱን እና ቴክኒሻኖች አስመርቋል፡፡
በዚሁ ወቅት የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ባደረጉት ንግግር÷ በርካታ ልፋትን አከናውናችሁ የማዕረግ ሽልማትን ያገኛችሁ የአየር ሃይል አባላትና ቤተሰቦች ለዚህ ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
አየር ሃይል የሀገሪቱ መከላከያ ክንድ መሆኑን ጠቅሰው÷ ይሄንን ኃይል ማጠንከር ብቻ ሳይሆን የባህር ሃይል አቅምንም በመጨመር ከፍ ማለት እንደሆነ ተናግረዋል።
አሁን ላይ ኢትዮጵያ ትልቅ የምድር ሃይል አቅምን ገንብታለች ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ÷ አየር ሃይላችንንም በከፍተኛ አቅምና ችሎታ የጠነከረ ለማድረግ በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በዘመነ ህውሓት የአየር ሃይሉን አቅም በአቅሙ ወደታች የሆነ እና የብሄር ብሄረሰብ ተዋጽኦም ያልነበረው ተቋም አድርጎት እንደነበረ አስታውሰው÷ ኢትዮጵያ ለስሙ ብቻ አየር ሃይል አላት ተብሎ ለውድቀት እንድትዳረግ ያደረገ የህውሓት የሴራ ውጤት እንደነበረም ገልጸዋል፡፡
የሀገሪቱን የፓይለት ባለሙያዎች ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን÷ ከውጭም ሌሎቹን ማሰልጠን የሚችል አቅም ተፈጥሯል ነው ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ አየር ሃይል የአፍሪካ የልምድ መውሰጃ ማዕከል እንዲሆን እየተሰራ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን÷ ባለፉት ሁለት አመታት በተሰራው ስራም ለውጥ ማምጣት ተችሏል ተብሏል።
አየር ሃይሉ የደረሰበትን ከፍታ በሽብር ቡድኑ ላይ ያከናወነው የጀግንነት ተግባር እና ጀብዱ ማሳያ እንደሆነ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
10.5K views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 23:46:21
እንኳን ለከተራና ለብርሐነ ጥምቀቱ በዓል በሠላም አደረሣችሁ!
14.4K views20:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-12 17:35:43
የተመድ ውሳኔ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው
_የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ህወሓትን ለምን በክፉ ዓይን አየሽብኝ በሚል በኢትዮጵያ የሚሰሩትን ኬንያዊቷን የሥራ ኃላፊ ከሀላፊነት ማንሳቱን ተከትሎ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።

አሸባሪውን ድርጅት “ቆሻሻ“ እና “ጨካኝ” በሚል የገለጹትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አለቆችን ለአማጺው ቡድን ይወግናሉ በሚል ያጋለጡት በኢትዮጵያ የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ ዋና ኃላፊ ሞሪን አቺንግ ከኒውዮርክ በተላለፈ ትዕዛዝ በትላንትናው ዕለት ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ተደርጓል።

ይሄንን ተከትሎም ኬንያዊያንን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ውሳኔውን በመቃወም ላይ ይገኛሉ። ሞሪን አቺንግ ስለትግራይ ሁኔታ ሀሳባቸውን ባጋሩበት የድምፅ ቅጂ ላይ “ህወሓቶች ከሳዑዲ ዓረቢያ የሚመለሱ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ እያሴሩ ነው፤ እና ከዚያ ከሩዋንዳ ምን አይነት የሽምቅ ውጊያ እንቅስቃሴ እንደሚጀመር አታውቁም። ብቻ ግን ያለው ነገር ቆሻሻ ነው” በማለት ገልፀዋል።

ተመድ 7 የድርጅቱ ሰራተኞች ከዚህ ቀደም ከአሸባሪው ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ቅሬታ ችላ ብሎ ቡድኑ እያደረሰ የሚገኘውን ጥፋት ብሎም የተመድን ያልተገባ አቋም የተቹትን ኃላፊ ከሥራ ማሰናበቱ የድርጅቱን ገለልተኛነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ሆኗል።

የተመድን እርምጃ በመቃወም ድምጻቸውን ካሰሙት መካከል የሆኑ ኬንያዊያን ”በጥቁር አድሏዊነት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኬንያዊቷን ሞሪን አቺንግ ለእውነት በመቆማቸው እና ህወሓት በኢትዮጵያ ውስጥ የፈጸማቸውን ጭካኔ በማውገዛቸው ከሥራ አግዷቸዋል። ማስፈራራት ቢኖርም እንኳን ኬንያውያን ሁል ጊዜ ለኢትዮጵያ ይቆማሉ።“ በሚል ገልጸዋል።
31.3K views14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-20 17:17:24 ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በመላው ኢትዮጵያ የሚታየውን የሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ አስመልክቶ ግምገማ ማካሄዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ። በስብሰባው ላይ የሀገሪቱን ጸጥታ እና ደኅንነት ሊያስጠብቁ የሚችሉ ቀጣይ ተግባራት እንዲከናወኑ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
28.4K views14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-19 18:40:17 Channel name was changed to «አርአያ ተስፋማርያም/Araya Tesfemariam»
15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-05 16:32:22 ሽፍታው የ30 አመት የመስረቅ የመዝረፍ የመዋሸት የመግደል ልምድ ነው ያላቸው ኢትዮጵያ በቃችሁ ብትላቸው እናፈርስሻለን አሏት ግን አትችሉም ብለዋቸዋል ልጆቿ ኢትዮጵያ ትቀጥላለች ሽፍታውና ጠላቶቿ ግን ይቀበራሉ።
37.0K views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-31 15:53:11 ተስፋ የቆረጠው የሽፍታው መሪ ደብረፅዮን ለአንቶዮ ጎቴሬዝ አደራድሩኝ እያለ መለመን ይዟል። ለድርድር የተላኩት የሀገር ሽማግሌዎች ክብር አዋርደው እንደመለሱ እንዴት እንደረሱት ይገርማል።የተሰጣችሁን እድል አበላሽታችኋል። ከዚህ በኋላ ያላችሁ እድል መተሰር አልያም መሞት ነው።
42.6K views12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-28 16:35:03 የትግራይ ተወላጆች አሸባሪው ህወሓትን ለመታገል ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ

"ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ" ብሎ የተነሳውን አሸባሪውን ህወሓት ለመታገል ቁርጠኛ መሆናቸውን በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ተናገሩ።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በክፍለ ከተማው ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ወቅት እንደተገለጸው፤ አሸባሪው ህወሓት ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የክፋት፣ የጥላቻና የዘረኝነት እንቅስቃሴዎችን ሲያራግብ ቆይቷል።

አሸባሪው ህወሃት የዘራውን አሉታዊ አስተሳሰብ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከውስጡ አውጥቶ የአሸባሪውን የክፋት አመለካከት በጽኑ ሊታገለው እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በመድረኩ አስተያየታቸውን የሰጡት ወይዘሮ ንግስቲ አበበ፤ አሸባሪው ህወሓት በሴራ ፖለቲካ ዘረኝነት እንዲስፋፋና ዜጎች እርስ በርስ እንዲጋጩ አድርጓል፤ እያደረገም ነው።

ይህ የሽብር ቡድን ለእኩይ ዓላማው ሲል የትግራይ ወጣቶችና ህፃናትን በማስገደድ ለጦርነት በመማገድ እያስጨረሰ መሆኑንም አንስተዋል።

አሸባሪው ሕወሃት ለህዝብ የማይጠቅም መሆኑን ጠቁመው፤ ቡድኑን ለማስወገድ እስከ መጨረሻው ለመታገል ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።

የቡድኑን ዓላማ ለማስፈፀም በአዲስ አበባ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አካላትን በማጋለጥ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ገልጸው፤ "እኔ እያለሁ ኢትዮጵያ አትፈርስም" ብለዋል።

በማንኛውም መንገድ የአገር ሰላምን ለማደፍረስ ከሚያሰሩ አካላት መራቅ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ሌላው የክልሉ ተወላጅ አቶ ማቲዎስ ገብረሥላሴ፤ “ዜጎች ሁሉ የኢትዮጵያን አንድነት ለማስቀጠል መስራት ይኖርባቸዋል” ብለዋል።

ትግራይ የኢትዮጵያ ጠንካራ መሰረት መሆኗን የተናገሩት አቶ ተካ አበበ፤ የአሸባሪውን ሴራ ለመቀልበስ የትግራይ ህዝብ እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን በአንድነት መቆም እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ለማዳን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም በአንድነት ሊቆም እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ሌላኛዋ የክልሉ ተወላጅ ወይዘሮ መሰሉ ረዳ እንደገለጹት፤ አሸባሪው ህወሓት የትግራይ ህዝብ እርዳታ እንዳያገኝ በማድረግ ለክልሉ ሕዝብ ጠላትነቱን በማስረጃ አረጋግጧል።

ይህ የሽብር ቡድን ዳቦ ሊሰጣቸው የሚገባ የትግራይ ህፃናትን ከእናቶቻቸው ጉያ ነጥቆ ሀሺሽ በመስጠት ወደ ጦርነት መማገዱ የሚያሳዝንና ሊወገዝ የሚገባው ድርጊት እንደሆነም አመልክተዋል።

በተለይም "ለክልሉ ሕዝብ ደህንነት የአካባቢው ተወላጆች ይህንን የሽብር ቡድን በጋራ መታገል አለብን" ብለዋል።

"እኔ ያልመራኋት ሀገር ትፍረስ" በማለት የሽብር ተግባር የሚፈጽመው አሸባሪው ህወሃት ለትግራይም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደማይጠቅም አብራርተዋል።

የክፍለ ከተማው የህዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ዘመን ተስፋዬ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ አሸባሪው ህወሓት ከውጪ ሀይሎች ጋር በመሆን ሀገር የማፍረስ እንቅስቃሴውን በጋራ መመከት ይገባል።

አሸባሪው ቡድን የከፈተውን የውክልና ጦርነት በመመከት ረገድ የክልሉ ተወላጆች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም ጠይቀዋል።

በተለይም በአዲስ አበባ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች የከተማውን ሰላምና ፀጥታ በማስጠበቅና የኢኮኖሚ አሻጥርን በመዋጋት የበኩላቸውን መወጣት እንደሚገባቸው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
43.5K views13:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-24 17:41:40 ''ኢትዮጵያ ትስዕር''
29.7K views14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-23 17:32:53
የኢትዮጵያ መከላከያ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፣ ከሶማሊያ አቻቸው ጋር በፀጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ።

የሶማሊያ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል አዲዋ የሱፍ ራጌ አድስ አበባ በመምጣት ከኢትዮጵያው አቻቸው ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ጋር በተወያዩበት ወቅት ፣ ሶማሊያ ወደፊት በወታደራዊ መስክ እራሷን ችላ ለመቆም በምታደርገው ጥረት ዙሪያ ተወያይተዋል።

በሶማሊያ ውስጥ የሚገኘው አሸባሪ ቡድን አልሸባብ በሶማሊያ ህዝብ ላይ የሚያደረሰውን ጫና በመቀነስ ረገድ በአሚሶም ጥላ ስር ለግዳጅ የተሰማራው የኢትዮጵያ ሰራዊት የማይተካ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል።

ጀነራሉ አክለውም የሶማሊያን ሰላም ለማስጠበቅ ቃል እየገቡ ከሚሄዱት የውጭ ሀገራት ይልቅ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ጎረቤት ሀገሮች የሰሩት ተግባር ፅኑ ወዳጅነት በቃላት የሚነገር ብቻ ሳይሆን በተግባር የሚረጋገጥ መሆኑ ማሳያ መስታወት ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያው የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ በበኩላቸው ፣ ሶማሊያ ራሷን ለመቻል በምታደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ ትብብር እና አጋርነት እንደማይለያት ቃል ገብተዋል።

የጎረቤት ሀገር ሰላም የእኛም ሰላም ፤ የጎረቤት ሀገር ሰላም መናጋት የእኛም ስጋት በመሆኑ የጋራ ጠላታችንን እስከ መጨረሻው ለመደምሰስ ዝግጁ ነን ማለታቸውን ውይይቱን የተከታተሉት በመከላከያ ውጭ ግንኙነት የሁለትዮሽ ትብብር ጉዳዮች ዳይሬክተር ኮ/ል የኑስ ሙሉ ተናግረዋል ፡፡

ብርሀን እንዳየሁ
ፎቶግራፍ እፀገነት ዴቢሳ
31.7K views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ