Get Mystery Box with random crypto!

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

የሰርጥ አድራሻ: @fanatelevision
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 183.01K
የሰርጥ መግለጫ

This is FBC's official Telegram channel.
For more updates please visit www.fanabc.com

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-21 19:03:24
ኤቨርተን፣ ክሪስታል ፓላስ እና አስቶንቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሄዱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ኤቨርተን፣ ክሪስታል ፓላስ እና አስቶንቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

በዚህም ኤቨርተን ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ ክሪስታል ፓላስ ዌስትሃምን 5 ለ 2 ረትቷል፡፡

እንዲሁም ከመመራት ተነስቶ አስቶንቪላ ቦርንማውዝን 3 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል፡፡
14.1K viewsedited  16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 18:03:54
ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የተገናኙት ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል አንድ አቻ ተለያይተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቡናን ጎል አማኑኤል አድማሱ በጨዋታ ሲያስቆጥር የመቻልን ጎል ደግሞ ምንይሉ ወንድሙ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/243215
13.2K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 17:19:01
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ለ1 ሺህ 460 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ለ1 ሺህ 460 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም÷ የክልሉ መስተዳድር ም/ቤት ሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ለ2ኛ ዙር የሚሰጠውን ይቅርታ ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 431 ወንድ እና ለ29 ሴት ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል ብለዋል፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/242990
13.2K viewsedited  14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 16:42:51
በማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ ሚሊዮን ጨፎ የደቡብ አፍሪካ አቻዋን በበቃኝ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ እየተካሄደ ባለው የማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ የቦክስ ውድድር ሚሊዮን ጨፎ የደቡብ አፍሪካ አቻዋን በበቃኝ አሸንፋለች፡፡ በ60 ኪሎግራም የደቡብ አፍሪካ አቻዋን የገጠመችው ቦክሰኛዋ በውድድሩ ሁለተኛ ዙር ላይ ተጋጣሚዋ ላይ ባሰረፈችው ቡጢ በዳኛ ውሳኔ አማካኝነት በበቃኝ ማሸነፍ ችላለች። ማሸነፏን ተከትሎም ቦከሰኛዋ ወደ ቀጣይ ዙር…

https://www.fanabc.com/archives/242940
12.8K viewsedited  13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 14:30:00
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሣይንስ ሙዝየም የተከፈተውን የስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይን ጎብኝተዋል፡፡

ምክትል ጠቀላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ÷ የስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይው በተለያዩ ዘርፎች ትላልቅ ኃሳቦች፣ ትልሞች፣ ዲዛይኖች፣ ሞዴሎች፣ የምርት ሙከራዎችእንዲሁም ምርቶች የታዩበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህም ሀገራችን በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ለመሆን ትክክለኛ መንገድ ላይ ስለ መሆኗ ማሳያነው ብለዋል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/242962
13.4K viewsedited  11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 12:43:31
በኢራንና በእስራኤል መካከል የተፈጠረው ውጥረት የነዳጅ ዋጋ ላይ ተጽዕኖ አለማሳረፉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢራንና በእስራኤል መካከል የተፈጠረው ውጥረት በዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ተጽዕኖ ባለማሳረፉ በእስያ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ መቀነሱ ተገለፀ፡፡ ዓለም ዓቀፉ የነዳጅ ዋጋ ተመን አውጭ የሆነው ብረንት ኦይል እንዳስታወቀው÷ የነዳጅ ዋጋ ከወትሮው የዋጋ መቀዛቀዝ ያሳየ ሲሆን አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት እስከ 90 ዶላር እየተሸጠ ይገኛል፡፡ ባለፉት…

https://www.fanabc.com/archives/242418
13.3K viewsedited  09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 12:40:33
ጄኔራል አበባው የጽንፈኛ ሃይሎችን አመራሮች የመመንጠሩ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኑን ሸኔ እና የጽንፈኛውን ሃይል አከርካሪ በመስበር በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና ሰሜን ሸዋ ዞን አንጻራዊ ሰላም ማስፈን ተችሏል ሲሉ የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ገለጹ፡፡ ጄኔራል አበባው ታደሰ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና የሰሜን ሸዋ ዞን አሁናዊ…

https://www.fanabc.com/archives/242383
12.6K viewsedited  09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 10:45:37
ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ በአዲስ አባባ መካሄድ ጀምሯል። በጉባዔው የሃይማኖት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ አምባሳደሮች፣ የአፍሪካና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል። በአህጉርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ሠላምና ልማትን ማረጋገጥ፣ ሰብዓዊ ክብርን መጠበቅ፣ አካባቢን መጠበቅ፣ የጥላቻ ንግግርንና መጤ ጠልነትን በጋራ መከላከል የሚያስችል ምክክር…

https://www.fanabc.com/archives/242401
13.3K viewsedited  07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 21:20:33
ቅዱስ ጊዮርጊስና ባህር ዳር ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስና ባህር ዳር ከተማ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ።

ዛሬ ምሽት 1፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ ቸርነት ጉግሳ በ30ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ጎል ባህር ከተማ ሲመራ ቢቆይም፤ በጭማሪ ሰዓት 90+5' ላይ አማኑኤል ኤርቦ ባስቆጠራት ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

ቀን 10፡00 ላይ የተካሄደው የፋሲል ከነማ እና የሀምበሪቾ ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ መረጃ አመልክቷል።
14.8K views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 21:02:36
የለውጡ ዓመታት በጠንካራ የዲፕሎማሲ ጥረት በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው – አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የለውጡ ስድስት ዓመታት በጠንካራ የዲፕሎማሲ ጥረት በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ገለጹ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፉት ስድስት የለውጥ ዓመታት በዲፕሎማሲው መስክ የተከናወኑ ተግባራትን በማስመልከት ከሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡ በመድረኩም አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ፤ ሀገራዊ ለውጡ የፖለቲካ ባህልን የቀየረ፣ የዲፕሎማሲ ጥረትና…

https://www.fanabc.com/archives/242243
13.2K viewsedited  18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ