Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fastmereja — FastMereja.com
የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.47K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-02-25 19:35:31
በተመሳሳይ ከፍታ ርቀት ላይ በመጓዝ ላይ የነበሩት የኳታር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስህተት ምክንያት ከመጋጨት ለጥቂት መትረፋቸዉ ተነግሯል።

ንብረትነቱ የኳታር አየር መንገድ የሆነዉ አዉሮፕላን ( ኳታር 6 ዩ) ከዶሃ ተነስቶ ወደ ኡጋንዳ ኢንቴቤ በ 38,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረ ቢሆንም በሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አዉሮፕላኑ ወደ 40,000 ጫማ ወደላይ እንዲወጣ ተነግሮታል።

በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 6 : 32 ገደማ በተመሳሳይ በ39,000 ጫማ ከፍታ ርቀት ላይ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ዱባይ ሲጓዝ ከነበረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን ( ኢቲ 602)
ጋር የተፋጠጠዉ የኳታር አዉሮፕላን ከመጋጨት ለጥቂት መትረፉ ተዘግቧል።

ሁለቱ ካፒቴኖች ስለ ክስተቱ ሲነጋገሩ የተቀረጹት ቅጂዎች ሁለቱም በሞቃዲሾ ከሚገኙ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የተሳሳተ መመሪያ እንደተቀበሉ ያሳያል ተብሏል።

በሁለቱም አውሮፕላኖች ላይ የተገጠመው የግጭት ማስወገጃ ሲስተም (TCAS) ወዲያውኑ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፣ ይህም በታዘዘው ከፍታ ላይ ሌላ አውሮፕላን መኖሩን በማመልከቱ ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት እንዲተርፍ ለማድረግ መቻሉ ዝግባዎች አመላክተዋል።

ይህን ተከትሎ በሞቃዲሾ የሚገኙት የፀጥታ ኃይሎች በሶማሊያ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የሆኑትን ሙባረክ ኑር አሊን በቁጥጥር ስር እንዲዉል አደርገዋል ሲል ካፒታል ነው የዘገበው።

@fastmereja
13.6K views16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-20 21:10:02
የወላይታ ሶዶ አውሮፕላን ማረፊያ
#FastMereja
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ አቅራቢያ የሚገነባውን የአውሮፕላን ማረፊያ ቦታን ጎበኙ

የወላይታ ሶዶ አውሮፕላን ማረፊያ አረካ ከተማ ሱማሞ ሜዳ ላይ የሚገነባው ቦታን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተመልክተዋል።

የግንባታ ሂደቱን ቶሎ ለማስጀመር የፕሮጀክቱ ስራ በሚከናወንበት አከባቢ ንብረትና ቤት ያላቸው አርሶአደሮችን ለማስነሳት ኮሚቴው ተዋቅሮ ስራውን እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@fastmereja
13.0K views18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-08 14:28:36
#ሹመት
1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን – የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
2. ትዕግስት ሃሚድ – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@fastmereja
15.1K views11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-01 12:16:22 1.1 ቢሊዮን ብር የወጣበት 9ኛው የኃይሌ ሆቴል በወላይታ ሶዶ ከተማ ተከፈተ!
#FastMereja
ከ14 ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ 2010 በኃይሌ ሪዞርት - ሀዋሳ የተጀመረዉ ጉዞ በአሁኑ ወቅት 8 ሆቴሎች እና ሪዞርቶችን በተለያዩ የሃገሪቷ ከፍሎች በሀዋሳ ፤ በአርባምንጭ ፤ በአዳማ ፤ በባቱ ፤ በጎንደር ፤ በሱሉልታ እና በአዲስ አበባ ገንብቶ በስራ ላይ ይገኛል።

ዘጠነኛ መዳረሻ የሆነው በደማቋ ወላይታ - ሶዶ ከተማ ባለ አራት ኮኮብ ሆቴል ተገንብቶ ተጠናቋል። ይህ በወላይታ ሶዶ የተገነባው ሆቴል 300 ለሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል ከመፍጠርም ባሻገር ከፍተኛ ጥራት ባለው የአገልግሎት ባህል ህብረተሰቡን ለማገልገል የቆመ መሆኑ ተገልጿል።

ሆቴላችን ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል የተለያየ አይነትና ስፋት ያላቸዉ 107 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የመመገቢያ አዳራሾች እንዲሁም ባሮች፣ ከ15 እስከ 500 ሰዎችን በምቾት ሊያስተናግዱ የሚችሉ ሰባት ሁለገብ አዳራሾች፣ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የበይነ መረብ (ኢንተርኔት) አገልግሎት፣ የእስቲም፣ የሳውና እና የማሳጅ አገልግሎት፣ የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎች (የመዋኛ ገንዳ እና ጂምናዚየም)፣ በቂ የሆነ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ለደህንነት ከተገጠሙ የ24 ሰዓት የጥበቃ ካሜራዎች።

የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎቹ በሚገባ የተሰናዱ እና የተዋቡ እንደሆኑ ተነግሯል፤ በውስጣቸውም ስማርት (Smart TV) ከተለያዩ የቻናል አማራጮች ጋር፣ የ24 ሰዓት የክፍል ውስጥ መስተንግዶ አገልግሎት፣ የአየር ማቀዝቀዣ (AC)፣ ከእፅዋት የተቀመሙ ተፈጥሮዊ የመታጠቢያ ሳሙናዎች፣ የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ እና የአደጋ ጊዜ መውጫ ያላቸው፣ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የበይነ መረብ(ኢንተርኔት) አገልግሎት የተሟላላቸው ናቸው::

ለግንባታው 1.1 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሆነ ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ ተናግሯል። በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ የክልል፣ የዞን እና የሶዶ ከተማ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ተገኝቷል።
12.7K views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-09 18:42:08
ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ ተወልዶ ላደገበት አከባቢ ምን ሰራ?
#FastMereja
ትምህርት ቤት
ሆስፒታል
የ4ጂ ኔትወርክ
በመንደሩ ላሉት ቤተሰቦች የገንዘብ ድጋፍ
ስታዲየም እና ያልተጠቀሱ በርካታ ድጋፍ አድርጓል

ለወገኖቹ እያደረገ ላለው ነገር በመላው ዓለም ከብር ያገኘ ተጨዋች ነው ማኔ!

@fastmereja
13.7K views15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-06 10:40:33
በ2007 ዓ.ም በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት ጥረት ሲያደርግ ህይወቱ ያለፈው ቢኒያም አድማሱ የህይወት ዘመን እውቅና ተሰጠው።

@fastmereja
14.1K views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-06 10:40:10
በሀረሪ ክልል የሚከበረው የሸዋል ኢድ በዓል በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ

የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት በመመዝገቡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ ኦርዲን ይሄንን ተከትሎም ሀረር በዩኔስኮ ሁለት ቅርሶችን ያስመዘገበች ብቸኛዋ የሃገራችን ያደርጋታል ብለዋል።

የክልሉ መንግስትም የዓለም ቅርስ የሆነውን የሸዋል ኢድ በዓል ለመጠበቅ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ የገለጹት ርእሰ መስተዳድሩ ቅርሱ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ለነበራቸው አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የሸዋል ኢድ በዓል ሀገራችን በማይዳሰስ ቅርስነት በዩኔስኮ የተመዘገበ 5ኛ ቅርስ ሆኗል።
ኢትዮጵያ ካሏት ደማቅ ማህበራዊ እሴቶች ውስጥ አንዱ የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር የአለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡም የቱሪስት ፍሰቱ እንዲጨምር ከማድረጉም ባለፈ የሀገር መልካም ገፅታ ለመገንባት የሚያግዝ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

@fastmereja
12.6K views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-01 16:08:22
የ12 ሚሊዮን ብር እድለኛ የሆነው የኮሌጅ ተማሪ
#FastMereja
የ3ኛ ዓመት የኮሌጅ ተማሪ ዮሴፍ መኮንን ይባላል ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ ልደታ ከ/ከተማ ሲሆን በልዩ ዕድል ሎተሪ 1ኛው ዕጣ የ 12,000,000 / አስራሁለት ሚሊዮን ብር/ ዕድለኛ ሆነዋል ፡፡

በገንዘቡም የምመረቀው በማርኬቲንግ ማኔጅመንት በመሆኑ ከትምህርቴ ጋር የሚሄድ ስራ እሰራበታለሁ ብለዋል ፡፡

@FastMereja
12.6K views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-29 19:07:36 የቦምብ ፍንዳታዎች በባሕር ዳር ከተማ
#FastMereja
በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባሕር ዳር በተለያዩ አካባቢዎች የቦምብ ፍንዳታ መድረሱ ተሰማ ። የቦምብ ፍንዳታዎቹ ትናንት በተለይ ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 16 እና ቀበሌ 13 ውስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች አካባቢ መድረሱ ተነግሯል ። በፍንዳታው በተማሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩም ተጠቁሟል ። በፍንዳታዎቹ ተማሪዎች መደናገጣቸው እና ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ወደ ቤት ለመውሰድ ሲሯሯጡ መታየታቸውን ዶቼ ቬለ ዘግበዋል።

ከፍንዳታው በኋላ ዛሬ በአንዳንድ ትምሕርት ቤቶች ፈተና ቢኖርም አብዛኞቹ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አለመሄዳቸውንም ዶቼ ቬለ አክሎ ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ በተለይ ቀበሌ 14 አካባቢ በምሽት መጠጥ ቤቶች አካባቢ በተከታታይ ቀናት ፍንዳታዎች ነበሩ ተብሏል ። ሌሊቱን ደግሞ ባሕር ዳር ከተማ ማር ዘነብ በተባለው ቀበሌ የተቀበረ ቦምብ ፈንድቶ ከፍተኛ ንዝረት መከሰቱን የዶቼ ቬለ ዘገባ ያሳያል።

@FastMereja
13.2K views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-27 16:49:32
አርቲስት ዳንኤል ተገኝ የዲጅታል እቁብ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተሾመ
#FastMereja
ዲጅታል እቁብ አርቲስት ዳንኤል ተገኝን የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር በማድረግ የፊርማ ስነ ስርዓት ዛሬ ህዳር 17/2016 ዓም አድርጓል። የብራንድ አምባሳደር አርቲስት ዳንኤል ተገኝ ለሁለት አመት በሚቆየው ውል ዲጂታል እቁብን በቢልቦርድ፣ በሚዲያዎች ላይ እንደሚያስተዋውቅ የተገለፀ ሲሆን ድጅታል እቁብን በመወከል የተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ በመገኘት ድርጅቱን እንደሚያስተዋውቅ ተገልፇል።

ዲጅታል እቁብ እቁብን በዲጅታል መንገድ በማምጣት የነጋዴዎች እቁብ፣ የአሽከርካሪዎች እቁብ፣ የሰራተኞች እቁብ፣ የድርጅት እቁብ፣ የማህበረሰብ እቁብ፣ የአይነት እቁብ በተባሉ የእቁብ አይነቶች እየሰራ ያለ ተቋም ነው።

በአሁኑ ወቅት በቀን፣ በሳምንት እና በወር እቁብ የሚጥሉ ከ10ሺ በላይ እቁብተኞች እንደሚገኙ ተነግሯል።

@fastmereja
12.9K views13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ