Get Mystery Box with random crypto!

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

የሰርጥ አድራሻ: @fanatelevision
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 183.29K
የሰርጥ መግለጫ

This is FBC's official Telegram channel.
For more updates please visit www.fanabc.com

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-11-12 12:47:11
የግንባታ ሥራዎችን ከአንድ ማዕከል ሆኖ ክትትል ማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በተለያዩ አካባቢዎች የሚከናወኑ የግንባታ ሥራዎችን ከአንድ ማዕከል ሆኖ ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ የሚያስችለውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ይፋ አድርጓል፡፡ ኮርፖሬሽኑ የለውጥ ሥራዎችን ተግባራዊ በማድረግ የሚታዩ ውጤቶችን በማስመዝገብ ላይ መሆኑን የኮርፖሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) ገልጸዋል። ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶችን በፍጥነት፣ በጥራትና በተያዘላቸው በጀት…

https://www.fanabc.com/archives/221180
15.1K viewsedited  09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-12 12:45:57
ማስታወቂያ

በእረፍት ቀናት እና በበዓላት የባንካችን በር መዘጋት አያሳስብዎ! የህብር ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያን በማውረድ በማንኛውም ሰዓት የተሟላ የባንክ አገልግሎት ያግኙ!
https://www.hibretbank.com.et/hibir-mobile-landing-page/
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!
13.8K viewsedited  09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-29 18:17:33
በመዲናዋ 3 ሠራተኞችን ለህልፈት የዳረገው የሪል ስቴት ሕንጻ ግንባታ ሥራ እንዲቆም ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ባሳለፍነው ዓርብ የሪል ስቴት ሕንጻ ግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ 3 ሠራተኞች ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ የሕንጻው ግንባታ እንዲቆም መደረጉን የከተማዋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ ባሳለፍነው ዓርብ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 6 በጅምር ግንባታ ላይ የሚገኝ ባለ 9 ወለል የአርሂቡ ሪል ስቴት ሕንጻ ግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ 3 ሠራተኞች ሕይወት አልፏል፡፡

ሠራተኞቹ ሲሚንቶ ወደ ላይ የሚያወጡበት ጋሪ የተሸከመው የብረት ገመድ በመታጠፉ የብረት ገመዱን ለማስተካከል በእጃቸው ይዘው በሚያንቀሳቅሱበት ወቅት በአቅራቢያው ከነበረ የኤሌክትሪክ ገመድ ጋር በመገናኘቱ ከሕንጻው ወደ መሬት ወድቀው ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

ተጨማሪ አንድ ሰራተኛ ወደ ሕክምናተቋም መወሰዱን ያብራሩት አቶ ገዛኸኝ÷ሶስቱ ሠራተኞች ግን ወዲያውኑ ሕወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።
https://www.fanabc.com/archives/218827
13.1K viewsedited  15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-29 16:59:20
ኔታንያሁ እስራኤላውያን ለረጅሙና አስቸጋሪው ጦርነት እንዲዘጋጁ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ዜጎች ለረጅሙ እና አስቸጋሪው ጦርነት እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የእስራኤል ጦር በጋዛ ሃማስ ታጣቂዎች ላይ የሚያካሂደው ወታደራዊ እርምጃ ሁለተኛ ምዕራፍ መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ÷እስራኤላውያን ከፊታቸው ላለው ረጅም ትግል አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሃማስ ጋር እየተደረገ ያለውን ጦርነት የሀገሪቱ ሁለተኛ የነጻነት ጦርነት ነው ሲሉ ገልጸውታል።

በጦርነቱ የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት በሃማስ ላይ ከባድ ጉዳት ያደረሱ ከፍተኛ የአየር ድብደባዎች መካሄዳቸውን ነው ኔታንያሁ የገለጹት፡፡

የምንገኘው በመንገዱ መጀመሪያ ላይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ በጋዛ ሰርጥ ያለው ጦርነት ከባድ እና ረጅም ይሆናል ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን አር ቲ ዘግቧል።https://www.fanabc.com/archives/218830
13.7K viewsedited  13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-29 16:01:10
አትሌት ደሬሳ ገለታ በቤጂንግ ማራቶን ውድድር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ደሬሳ ገለታ እና አትሌት ይሁንልኝ አዳነ በቤጂንግ 2023 ማራቶን ውደድር አሸንፈዋል፡፡

አትሌት ደሬሳ ገለታ ርቀቱን 2 ሰዓት 7 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ መሆን ችሏል፡፡

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ይሁንልኝ አዳነ ደግሞ ርቀቱን 2 ሰዓት 7 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመጨረስ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል፡፡https://www.fanabc.com/archives/218821
13.2K viewsedited  13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-29 15:55:28
"ሥውር ውጊያ" ዘጋቢ ፊልም - ነገ ምሽት 3:00 ላይ ይጠብቁን
12.6K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-29 15:17:43
የህጻናት ካንሰር ሕክምናን በ8 ሳተላይት ክሊኒኮች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የህጻናት ካንሰር ሕክምናን በአራት ክልሎች በሚገኙ 8 ሳተላይት ክሊኒኮች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የካንሰር ህክምናን ተደራሽ ለማድረግ የሳተላይት ክሊኒኮችን ማደረጀት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል፡፡ በምክክር መድረኩ የዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች፣ የጤና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት፣ ባለድርሻ አካላት፣ አጋር ድርጅቶች እንዲሁም የክልል…

https://www.fanabc.com/archives/218815
13.1K viewsedited  12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-29 14:18:34
በ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ወጪ የተገዙ መኪናዎች ለክልሎች ተበረከቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴር ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ መኪናዎች እና ሌሎች ቁሶችን ለክልሎች አስረክቧል፡፡ በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፣ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር እና የክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ ተሽከርካሪዎቹ በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡትን ምርጥ ተሞክሮዎች በላቀ ደረጃ ለማስቀጠልና የግብርና…

https://www.fanabc.com/archives/218810
13.7K viewsedited  11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-29 12:36:54
በኮንታ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ገለፀ፡፡ በወረዳው ኦፓላሸ ቀበሌ በግምት ከምሽቱ 9 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 25 አባዎራዎችና 175 የቤተሰብ አባላት ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው…

https://www.fanabc.com/archives/218800
14.1K views09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-29 11:38:26
ለምክር ቤት አባላት “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሀሳብ ስልጠና መሰጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሀሳብ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠና መሰጠት ጀመረ። ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት እንደሚቆይ ኢዜአ ዘግቧል። በስልጠና ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የአፍሪካ አመራር ልህቀት…

https://www.fanabc.com/archives/218795
14.1K viewsedited  08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ