Get Mystery Box with random crypto!

ኔታንያሁ እስራኤላውያን ለረጅሙና አስቸጋሪው ጦርነት እንዲዘጋጁ አሳሰቡ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18 | FBC (Fana Broadcasting Corporate)

ኔታንያሁ እስራኤላውያን ለረጅሙና አስቸጋሪው ጦርነት እንዲዘጋጁ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ዜጎች ለረጅሙ እና አስቸጋሪው ጦርነት እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የእስራኤል ጦር በጋዛ ሃማስ ታጣቂዎች ላይ የሚያካሂደው ወታደራዊ እርምጃ ሁለተኛ ምዕራፍ መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ÷እስራኤላውያን ከፊታቸው ላለው ረጅም ትግል አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሃማስ ጋር እየተደረገ ያለውን ጦርነት የሀገሪቱ ሁለተኛ የነጻነት ጦርነት ነው ሲሉ ገልጸውታል።

በጦርነቱ የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት በሃማስ ላይ ከባድ ጉዳት ያደረሱ ከፍተኛ የአየር ድብደባዎች መካሄዳቸውን ነው ኔታንያሁ የገለጹት፡፡

የምንገኘው በመንገዱ መጀመሪያ ላይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ በጋዛ ሰርጥ ያለው ጦርነት ከባድ እና ረጅም ይሆናል ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን አር ቲ ዘግቧል።https://www.fanabc.com/archives/218830