Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ 3 ሠራተኞችን ለህልፈት የዳረገው የሪል ስቴት ሕንጻ ግንባታ ሥራ እንዲቆም ተደረገ አዲስ | FBC (Fana Broadcasting Corporate)

በመዲናዋ 3 ሠራተኞችን ለህልፈት የዳረገው የሪል ስቴት ሕንጻ ግንባታ ሥራ እንዲቆም ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ባሳለፍነው ዓርብ የሪል ስቴት ሕንጻ ግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ 3 ሠራተኞች ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ የሕንጻው ግንባታ እንዲቆም መደረጉን የከተማዋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ ባሳለፍነው ዓርብ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 6 በጅምር ግንባታ ላይ የሚገኝ ባለ 9 ወለል የአርሂቡ ሪል ስቴት ሕንጻ ግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ 3 ሠራተኞች ሕይወት አልፏል፡፡

ሠራተኞቹ ሲሚንቶ ወደ ላይ የሚያወጡበት ጋሪ የተሸከመው የብረት ገመድ በመታጠፉ የብረት ገመዱን ለማስተካከል በእጃቸው ይዘው በሚያንቀሳቅሱበት ወቅት በአቅራቢያው ከነበረ የኤሌክትሪክ ገመድ ጋር በመገናኘቱ ከሕንጻው ወደ መሬት ወድቀው ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

ተጨማሪ አንድ ሰራተኛ ወደ ሕክምናተቋም መወሰዱን ያብራሩት አቶ ገዛኸኝ÷ሶስቱ ሠራተኞች ግን ወዲያውኑ ሕወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።
https://www.fanabc.com/archives/218827