Get Mystery Box with random crypto!

አርሰናል ቶተንሃምን በማሸነፍ የዋንጫ ተፎካካሪነቱን አጠናክሯል አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 201 | FBC (Fana Broadcasting Corporate)

አርሰናል ቶተንሃምን በማሸነፍ የዋንጫ ተፎካካሪነቱን አጠናክሯል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠባቂው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ቶተንሃምን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

10 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ሳካ፣ ሀቨርተስ እና ሆይቤር (በራሱ ግብ ላይ) አስቆጥረዋል፡፡

ቶተንሃምን ከሽንፈት ያላዳኑትን ግቦች ደግሞ ሮሜሮ እና ሰን አስቆጥረዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም አርሰናል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እስከመጨረሻው የዋንጫ ተፎካካሪ የመሆን እድሉን ማጠናከር ችሏል፡፡

አርሰናል 80 ነጥቦችን በመያዝ በፕሪሚየር ሊጉ ደረጃ ሰንጠረዡ 1ኛ ላይ ሲቀመጥ ማንቼስተር ሲቲ ደግሞ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ76 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል፡፡