Get Mystery Box with random crypto!

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽንን ጎበኙ አዲስ አበባ፣ | FBC (Fana Broadcasting Corporate)

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽንን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የስራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል፡፡

ጉብኝቱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ÷ በግብርና ዘርፍ ያገኘናቸው ስኬቶች በኢንዱስትሪው ዘርፍም በመደገም ላይ ናቸው ብለዋል።

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የተካሄደውን የመዋቅር እና የአመራር ለውጥ ተከትሎ ተቋሙ ሪቨርስ ኢንጂነሪንግ ዘዴን በመጠቀም የተለያዩ መሳሪያዎችን፣ ሮኬቶችን እና ታንኮችን ለማምረት አስደናቂ ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

እያደጉ ያሉ አቅሞች ብልፅግናን ከማረጋገጥ በተጨማሪ ለአህጉራችን ተስፋ እየሆኑ ነውም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

አክለውም ፥ በስኬቶቻችን ላይ በመመስረት እና በሰፊ የሰው ኃይላችን በመደገፍ በሁሉም ዘርፎች እና መስኮች እድገታችንን ማፋጠን ይኖርብናል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡