Get Mystery Box with random crypto!

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

የሰርጥ አድራሻ: @fanatelevision
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 185.01K
የሰርጥ መግለጫ

This is FBC's official Telegram channel.
For more updates please visit www.fanabc.com

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2023-10-22 20:24:02
የፕሪሚየር ሊጉ ሁለት መርሐ ግብሮች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሦስተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያ አዳማ ከተማ ከሀምበሪቾ ዱራሜ እንዲሁም ኢትጵያ ቡና ከባህር ዳር ከተማ 2 አቻ ተለያይተዋል፡፡ ለአዳማ ከተማ አብዲሳ ጀማል እና ዮሴፍ ታረቀኝ እንዲሁም ለሀምበሪቾ ዱራሜ በፍቃዱ አስረሳኸኝ እና ዳግም በፍቃዱ ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡ በውጤቱ መሰረት አዳማ ነጥቡን ወደ 5 ከፍ በማድረግ የነበረበትን…

https://www.fanabc.com/archives/217826
13.5K viewsedited  17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-22 19:10:02
አመራሩ የሕዝቡን እርካታ በሚያረጋግጥ ሁኔታ በይበልጥ ውጤት ለማምጣት እንዲተጋ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ማዕከላት ሲሰጥ የነበረው ሁለተኛው ዙር የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተጠናቋል፡፡

ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን ግብዓት ተግባራዊ በማድረግ የሕዝቡን እርካታ በሚያረጋግጥ ሁኔታ በሰላም፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ በይበልጥ ውጤት ለማምጣት እንዲተጉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ አሳስበዋል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/217802
14.0K viewsedited  16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-22 18:36:32
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራን መረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራን በዛሬው ዕለት መርቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ “ሁሉም በየመስኩ አድርጎ በማሳየት፣ ሆኖ በመገኘት እና በጎ አርዓያ በመሆን ኃላፊነቱን ቢወጣ ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር በመሆኗ ዛሬ የዘራነው መልካም ዘር ነገ መልካም ውጤት ያመጣል” ብለዋል።

ዛሬ የተመረቀው የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራ ለሕፃናት እና ለወጣቶች አገልግሎት የሚውል መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
13.7K viewsedited  15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-22 17:42:06
በትምህርት ቤት ምገባ አዲስ አበባ ልምድ የሚቀሰምባት ከተማ ሆና ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትምህርት ቤት ምገባ መርሐ ግብር አዲስ አበባ ሌሎች ሀገራት ልምድ የሚቀስሙባት ከተማ ሆና መመረጧን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ በፓሪስ በተካሄደው የዓለም የትምህርት ቤት ምገባ ጥምረት መድረክ ላይ አዲስ አበባ ሌሎች ሀገራት ልምድ የሚወስዱባት ከተማ ሆና መመረጧን ገልጸዋል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/217776
13.4K views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-22 16:43:18
2ኛው ዙር የአመራሮች ስልጠና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ማዕከላት ሲሰጥ የነበረው ሁለተኛው ዙር የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ ”ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሐሳብ በ10 ማዕከላት ከመስከረም 29 ቀን 2016 ጀምሮ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ስልጠናው÷ በአመራሩ ዘንድ የተግባርና የሐሳብ አንድነት በማምጣት ሀገራዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያስችል አቅምና ክኅሎት መፍጠሩ ተገልጿል፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/217756
13.9K viewsedited  13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-22 16:19:46
የወል እውነትን በመያዝ ለዘላቂ ሰላም መሥራት እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚያስተሳስሩ የወል እውነቶችን በመያዝ ለሀገራዊ አንድነት፣ ዘላቂ ሰላምና ልማት በጋራ መሥራት እንደሚገባ የሰላም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ “የሰላምና የሀገር ግንባታ መሰረታውያን ሀገራዊ ጥቅሞች፣ የጋራ ማንነቶች፣ ሀገራዊ እሴቶችና ሴኩላሪዝም” በሚል መሪ ሐሳብ ከሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ውይይት ተካሂዷል፡፡ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደአ በመድረኩ…

https://www.fanabc.com/archives/217749
13.3K viewsedited  13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-22 15:20:41
ቦርዱ በአዋሽ አርባ የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን የሰብዓዊ አያያዝ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ በአማራ ክልል ተፈጠሮ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ሳቢያ በወንጀል ተጠርጥረው በአዋሽ አርባ የማቆያ ማዕከል የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን የሰብዓዊ አያያዝ ሁኔታ ተመልከተ፡፡ ከምልከታው ጎን ለጎንም የቦርዱ አባላት ከተጠርጣሪዎቹ ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸው ወቅትም÷ በአማራ ክልል በተከሰተው የጸጥታ መደፍረስ ተሳትፎ የነበራቸውን ተጠርጣሪዎች ለይቶ…

https://www.fanabc.com/archives/217725
13.6K viewsedited  12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-22 15:10:11
አውስትራሊያዊቷ ዋናተኛ በጀርባ ዋና ስፖርት የዓለም ክብረወሰንን ሰበረች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ የዋና ስፖርት ውድድር አውስትራሊያዊቷ ዋናተኛ ኬይሊ ማክዊን የጀርባ ዋና የዓለም ክብረወሰንን ሰብራለች፡፡ ኬይሊ ማክዊን 50 ሜትሩን የዋና ርቀት ለማጠናቀቅ 26 ሰከንድ ከ86 ማይክሮ ሰከንድ ፈጅቶባታል፡፡ በዚህም በቻይናዊዋ አትሌት ሊዩ ዥያንግ በ2018 ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን በ12 ማይክሮ ሰከንድ ማሻሻል ችላለች፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/217721
12.9K viewsedited  12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-22 14:56:31
የቻይና - አፍሪካ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና - አፍሪካ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የልምድ ልውውጥ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

መድረኩ የቻይና - አፍሪካን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር የተደረገው ስምምነት ወደ ተግባር የተገባበት ማሳያ መሆኑን የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ቻይና በሰው ኃይል ልማት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በመምህራን ስልጠና ዘርፎች የምታደርገውን ድጋፍ ማጠናከሯንም ነው የገለጹት፡፡

https://www.fanabc.com/archives/217715
12.8K viewsedited  11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-22 13:58:50
ማስታወቂያ

እንዴት የሞባይል ባንኪንግ ‘QR’ አገልግሎት ተጠቅመው ገንዘብ መቀበል/ክፍያ መፈፀም ይችላሉ?
     *************************
1. ገንዘብ ላኪውና ተቀባዩ አንድ ላይ የማይገኙ ሲሆን
• ገንዘብ ተቀባዩ በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያው ላይ የሚገኘውን የ ‘QR’ ኮድ ምልክት ይጫኑ፤
• ከሚመጡት አማራጮች ‘ገንዘብ ለመቀበል’ ‘Receive Money’ የሚለውን ይምረጡ፤
• ‘የገንዘብ መጠን እና ምክንያት’ ‘Amount and Reason’ የሚለውን ይምረጡ፤
• የገንዘብ መጠን እና  ምክንያቱን አስገብተው ‘ቀጥል’ ‘Continue’ የሚለውን ይጫኑ
• ‘ያጋሩ’ ‘Share’ የሚለውን ይጫኑ፣
• ‘በማስፈንጠሪያ መልክ ያጋሩ’ ‘Share as a link’ የሚለውን ተጭነው ‘እሺ’ ‘Ok’ የሚለውን ይምረጡ፣
• በSMS፣ በቴሌግራም እና በሌሎችም መልእክት መላላኪያ መንገዶች ተጠቅመው ማስፈንጠሪያውን ለገንዘብ ላኪው ይላኩ፣
• ገንዘብ ላኪው በመልእክት የደረሰውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመክፈት የሚላከውን የገንዘብ መጠን እና ምክንያት አረጋግጦ ገንዘብ ማስተላለፍ/ክፍያ መፈፀም ይችላል፡፡
2. ገንዘብ ላኪውና ተቀባዩ በተመሳሳይ ቦታ የሚገኙ ከሆነ
• ገንዘብ ተቀባዩ በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያው ላይ የሚገኘውን የ ‘QR’ ኮድ ምልክት ይጫኑ፤
• ከሚመጡት አማራጮች ‘ገንዘብ ለመቀበል’ ‘Receive Money’ የሚለውን ይምረጡ፤
• ገንዘብ ላኪው በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያው ላይ የሚገኘውን የ ‘QR’ ኮድ ምልክት ተጭኖ
ከሚመጡት አማራጮች ‘ስካን ኪው አር’ ‘Scan QR’ የሚለውን ይምረጡ፤
• የሚላከውን የገንዘብ መጠን እና ምክንያት በማስገባት ገንዘብ በቀላሉ መላክ/ክፍያ መፈፀም ይቻላል፡፡
13.5K views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ