Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-ETHIOPIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethiopia — TIKVAH-ETHIOPIA
ርዕሶች ከሰርጥ:
Ethiopia
Bankinginethiopia
Bankofabyssina
Banksinethiopia
Womensavingaccount
Update
Adwa
Amhara
Tigray
Tikvahfamilymekelle
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethiopia
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.30M
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-03-18 23:57:13
#ሲቢኢ #ዩኒቨርሲቲዎች #ኦዲት

" ባንኩ ላይ የሳይበር ጥቃት ደርሷል፤ ዝውውሩም አይታወቅም ብለው አስበው ነው ያደረጉት " - አቶ አቤ ሳኖ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ በዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ስለነበረው የመጋቢት 6 ለሊት የገንዘብ ዝውውር እና አጠቃላይ ወጭ ስለተደረገው / አሁን ስለተመለሰው የገንዘብ መጠን ምን አሉ ?

አቶ አቤ ሳኖ ፦

" የተቋረጠውን አገልግሎት ካስጀመርን በኃላ ወደ ግብይቶች ምርመራ ነው የገባነው።

በዛ ያለ ግብይት ያደረጉትን ለይተናቸው የፍትሕ አካላት እንዲያውቁት አድርገናል። በብዛት በዛ ያለ ቁጥር ያለው እጅግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ #በዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ነው።

ተማሪዎቹ (የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ) ያሰቡት ባንኩ ላይ የሳይበር ጥቃት ደርሷል ብለው ነው። ስለዚህ የሚደረገው ግብይት (ወጭ / ዝውውር) አይታወቅም ብለው ነው ያደረጉት።

አሁን ላይ ግን ግብይቱ እንደሚታወቅ ሲያውቁ የወሰዱትን ገንዘብ እየመለሱ ነው ያሉት። አሁንም እንዲመልሱ ነው የምንፈልገው።

የወሰዱትን ገንዘብ ከመለሱ ወደ ክስ አንሄድም። የማይመልሱ ከሆነ ግን የህግ እርምጃ እንወስዳለን።

ዝርዝር ጉዳዩ (ከገንዘብ ዝውውር/ወጭ የተደረገ/የተመለሰ) ኦዲት ተደርጎ ሲያልቅ ይቀርባል።

የኦዲት ሂደቱ ስላላለቀ በዚህ መካከል ሌሎች ነገሮችን ማንሳት ከፋይናንሻል ኦዲት አካሄድ ጋር የሚሄድ ስላልሆነ አንዳንድ የህጋዊ እርምጃዎችም ሊከተሉ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ስለሚፈልግ ነው። "

@tikvahethiopia
28.8K views20:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-18 21:29:24
#ፑቲን

አሜሪካ ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤቷ በኩል በሰጠችው መግለጫ ፤ የሩስያ ምርጫን " ኢ-ዲሞክራሲያዊ ነው " ስትል አጣጥላለች።

በከፍተኛ ልዩነት አሸንፈዋል የተባሉትን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንንም " እንኳን ደስ አልዎት " አንላቸውም ብላለች።

ሩስያን እስከ 2030 ለመምራት በበላይነት ፕሬዜዳንታዊ ምርጫውን ያሸነፉት ቭላድሚር ፑቲ ትላንት ድላቸውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ የአሜሪካን ዴሞክራሲ ወርፈዋል።

ምን አሉ ?

ቭላድሚፕ ፑቲን ፦

" ያካሄድነው ምርጫ ከአሜሪካ በላይ ተዓማኒ እና ግልጽ የሆነ ዓላማ ያለው ነው።

በአሜሪካ በፖስታ አማካይነት ድምጽ እንደሚሰጡት አይደለም። እዛ (አሜሪካ) ድምጽ በ10 ዶላር መግዛት ይቻላል።

የምርጫ ስርዓታቸው ኢ-ዴሞክራሲያዊ ነው።

ዓለም ሁሉ እዚያ እየሆነ ባለው ነገር ይስቃል (በአሜሪካ ዴሞክራሲ) " ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ፑቲን ፕሬዜዳንታዊ ምርጫውን በከፍተኛ ብልጫ ማሸነፋቸው ተከትሎ ፦
- ቻይና
- ህንድ
- ኢራን
- ሰሜን ኮሪያ
- ቬንዙዌላ #የደስታ መልዕክት ሲያስተላልፉ እነ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ ዩክሬን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ሌሎች አጋሮቻቸው ምርጫውን ኢ-ዴሞክራሲያዊ ሲሉ እያጣጣሉት ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
123.5K viewsedited  18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-18 20:47:26
#ነእፓ

በሀገሪቱ ያሉ የእርስ በርስ ግጭቶችን ለማስቆም “ ኢትዮጵያ በልጆቿ ትታረቅ ! ” በሚል የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የእርቅ እና የሰላም ሀሳብ ይዞ መቅረቡን አሳውቋል።

ፓርቲው በላከልን መግለጫ ፤ ሀገራችን በታሪኳ በርካታ በእርስ በእርስ ግጭቶችን ማስተናጓን ገልጿን።

ለ2 አመታት በትግራይ፣ በአማራ እና አፋር ክልሎች የተካሄደው ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ህይወት መቅጠፉን አመልክቷል።

አሁንም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የቀጠለው የወንድማማቾች ጦርነት የወገኖቻችንን ህይወት እየቀጠፈ እንደሚገኝ ገልጿል።

በየአካባቢው በተለኮሱ ጦርነቶች ሳቢያ ፦

- በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ውድ ህይወታቸውን እንዳጡ፣ አካላቸው እንደጎደለ፤

- እድሜ ልካቸውን ያፈሩት ንብረት እና የሀገራችን ኢትዮጵያ አንጡራ ሀብትም እንደወደመና እየወደመም እንደሚገኝ ገልጿል።

በእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናት ያለ አሳዳጊ፣ አረጋውያን ያለ ጧሪ ፣ አያሌ ኢትዮጵያውያን ለርሀብ፣ ለእንግልት፣ ለስደት እና ለሞት መዳረጋቸውን ገልጿል።

በየአካባቢው የተከሰቱ ግጭቶች ማህበራዊ ግንኙነታች እንዲበጣጠስ፣ በዜጎች መካከል ጥርጣሬ እንዲነግስ፣ ማህበራዊ ትስስራችን እንዲላላ፣ ጥላቻ፣ እልህ፣ በቀል እንዲስፋፋ፣ ስጋት እና ጭንቀት በዜጎች ልቦና እንዲሰፍን ማድረጋቸውንም አመልክቷል።

ነእፓ፤ ጦርነት መቼም ቢሆን የፖለቲካ ልዩነቶችን ለመፍታት የተሻለ አማራጭ አይሆንም ፤ የእርስ በእርስ ጦርነት አሸናፊና ተሸናፊ የሌለው የመጨረሻ ውጤቱ ሞት፣ ስደት፣ ስቃይ፣ ሀዘን ፣ የሀገር ድቀትና መፍረስ ነው ብሏል።

ላለፉት ዓመታት ሰላም እንዲሰፍን በተለያዩ መንገዶች ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን የሚገልጸው ነእፓ ሀገራችንን ለክፉ ችግር፣ ህዝባችንን ማባሪያ ለሌለው ሰቆቃ የዳረጉ ጦርነቶች እንዲቆሙ “ #ኢትዮጵያ_በልጆቿ_ትታረቅ ” በሚል ስያሜ አዲስ የእርቅ እና የሰላም ሀሳብ መንደፉን ይፋ አድርጓል።

ዋናው ዓላማ በመንግስት እና ከመንግስት ጋር ነፍጥ አንግበው በሚፋለሙ ማናቸውም ኃይሎች መካከል በሀገር ሽማግሌዎች፣ በኃይማኖት አባቶች እና በሌሎች ታዋቂ ስብእናዎች አማካኝነት እርቅ ማውረድ እንደሆነ ገልጿል።

በቀጣይ ሂደቱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎች ይሰጣሉ ብሏል።

@tikvahethiopia
143.1K views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-18 20:47:15
#ወጋገን_ባንክ

በአምስት የተለያዩ ቋንቋዎች የቀረበውን ደህንነቱ የተጠበቀ ፈጣን እና አስተማማኝ የወጋገን ሞባይል መተግበሪያ አሁኑኑ ከአፕስቶር ወይም ፕሌይስቶር በማውረድ ስልክዎ ላይ ይጫኑ፣ በቀልጣፋ አገልግሎታችን ህይወትዎን ያቅልሉ!

ስልክዎ ባንክዎ

ለተጨማሪ መረጃ በ866 ነፃ የስልክ መስመር ወደ ደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ይደውሉ፣ ይስተናገዱ::

Download now:

Android:https://play.google.com/store/apps/details?id=com.act.wegagen&hl

IOS:https://apps.apple.com/in/app/wegagen-mobile/id6472656143

#WegagenBank #WegagenMobile #MobileBanking

Follow us and get more information...

https://linktr.ee/WegagenBank
128.5K views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-18 18:25:30
#CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ምን አሉ ?

- " ችግሩ የተከሰተው አንድ ሂሳብ ማስታረቅ ቅልጥፍና እንዲያመጣ ታስቦ የተሰራ የሲስተም ማሻሻያ ሲተገበር ስህተት በመፈጠሩ ነው። የተፈጠረው ስህተት ለሌቦች ቀዳዳ ከፍቶ ነበር። "

- " የሲስተም ማሻሻያው የተተገበረው አርብ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ ነበር። ከሌሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ ችግር እንዳለ ሊለይ ችሏል። ይህን ተከትሎም አንዳንድ የተጠረጠሩ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ተደርጓል። ይህም ሆኖ ሙሉ በሙሉ ችግሩ ስላልቆመ ሁሉም የዲጂታል ባንክ ስርዓቶች እንዲቋረጡ ተደርጎ ነበር። "

- " ባንኩ ችግሩ በተከሰተበት ወቅት ከ490 ሺህ በላይ የገንዘብ ልውውጥ ተካሂዷን። ሌሊቱን ሙሉ ግብይት ሲፈጸምባቸው የነበረባቸው የባንክ ሂሳቦች በሙሉ እስኪጣራ ድረስ #እንዲታገድ ተደርጓል። "

- " በቀጣይ ከፍተኛ እና ያልተገባ ግብይት የፈጸሙ አካላትን እየለየን ለህግ የማቅረብ ስራ ይሰራል። "

- " የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በወንጀሉ ዋነኛ ተዋናይ መሆናቸው አሳዝኖናል። በየአካባቢው ያሉ የዲስትሪክት ኃፊዎች በየአካባው ከሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት ተማሪዎች የወሰዱትን ገንዘብ #እንዲመልሱ እየተደረገ ነው። "

- " ከተፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞ አጠቃላይ የደረሰው ጉዳት ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው። የችግሩ መሰረታዊ መንስዔ እና ያስከተለውን ጉዳትም ምርመራው ሲጠናቀቅ ይፋ ይደረጋል። "

- " ባንኩ ላይ የደረሰው ጉዳት ባንኩ ካለው ሀበት እና አቅም አንጻር የጎላ ተጽእኖ የለውም፤ ከደንበኞች ሂሳብ ጋርም አይገናኝም። " #አልአይን

@tikvahethiopia
189.2K views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-18 18:12:41
" ገንዘቡን ተመላሽ ባደረጉ ተማሪዎች ላይ ባንኩ ምንም አይነት ክስ አይመሰርትም " - ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቀናት በፊት ባንኩ ላይ አጋጥሞ ስለነበረው ችግር መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የባንኩ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ ናቸው።

ምን አሉ ?

የባንኩ ፕሬዜዳንት አርብ ለሊት ባንኩ አጋጥሞት በነበረው ችግር የደንበኞች የግል አካውንት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት እንደሌለ ገልጸዋል።

ባንኩ የውስጥ አሰራሩን ለማዘመን (የሲስተም ማሻሻያ) ሲያደርግ በነበረው እንቅስቃሴ ምክንያት በተፈጠረ ስህተት የአርብ መጋቢት 6 ለሊቱ ክስተት መፈጠሩን እና ጉዳዩ ከሳይበር ጥቃት ጋር የሚያያዝ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

" በተፈጠረ ስህተት ምክንያት ጤናማ ያልሆነ የገንዘብ እንቅስቃሴ ነበር " ብለዋል።

አርብ ለሊት ብቻ ከ490 ሺህ በላይ የገንዘብ ልውውጥ እንደነበር ገልጸዋል። ይህ የገንዘብ ልውውጥ ጤናማ የሆነውንም እንደሚጨምር ጠቁመዋል፡፡

" ገንዘብ በተለያየ መንገድ ጤናማ ባልሆነ መልኩ ከባንኩ በማውጣት ላይ በዋናነት የተሳተፉት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው " ሲሉ ገልጸዋል።

የድርጊቱ ተሳታፊ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በባንኩ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት የወሰዱትን ገንዘብ እየመለሱ እነደሆነና ገንዘቡን ተመላሽ ባደረጉ ተማሪዎች ላይ ባንኩ ምንም አይነት ክስ እንደማይመሰርት አሳውቀዋል።

አሁንም ያልመለሱ ስም ዝርዝራቸው የወጣ ተማሪዎች የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ አሳስበዋል።

ከዚህ ባለፈ ወደ ሌሎች ባንኮች የተደረጉ እና ጤናማ የማይመስሉ የገንዘብ ዝውውሮች ታግደው እንደሚገኙ አስረድተዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ በባንኩ ላይ ጉዳት መድረሱን ያልደበቁ ሲሆን ባንኩ አጠቃላይ ሀብት አንፃር ሲታይ በጣም አነስተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

የደንበኞች የግል አካውንት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት ባለመኖሩ የባንኩ ደንበኞች ምንም አይነት ስጋት እንዳይገባቸው ማለታቸውን የብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
180.7K viewsedited  15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-18 16:39:27
#NationalExam

" የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅት እየተገባደደ ነው ፤ ... በቀጣይ የፈተናው ሕትመት ይጀመራል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ለ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የፀጥታ ችግር በሌላባቸው አካባቢዎች ብቻ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው ሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተማሪዎች ምዝገባ ተካሂዶ መጠናቀቁን የገለጸው መ/ቤቱ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለብሄራዊ ፈተናው ምዝገባ ማከናወናቸውን ጠቁሟል።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሚገኙ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ በዚህ ሣምንት ይከናወናል ብሏል።

የፈተና ዝግጅት ሥራው የሀገሪቱን ሥርዓተ ትምህርት የተከተለ እና ተማሪዎቹን በአግባቡ መመዘን በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱን አገልግሎቱ ገልጿል።

የፈተናው ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን አመልክቶ በቀጣይ #የፈተናው_ሕትመት እንደሚጀመር አሳውቋል።

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የመስጫው የጊዜ ሰሌዳ ወደፊት ይፋ እንደሚሆንም የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
199.5K viewsedited  13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-18 16:13:44
#CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሞኑን " በሲስተም መበላሸት " ምክንያት አጋጥሞት ከነበረው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ያሉ ጉዳዮች ላይ ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ በዋና መ/ቤቱ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

@tikvahethiopia
194.1K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-18 16:04:36
#EthiopianAirlines

" ተፈፅሟል የተባለውን ሙስና እና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ናቸው ፤ ሰራተኞቹም በቁጥጥር ስር ውለዋል " - አቶ መስፍን ጣሰው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰሞነኛና በአየር መንገዱ እንቅስቃሴ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ " በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ለሚፈፀሙ ወንጀሎች አየር መንገዱን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ማድረግ ተቀባይነት የለውም " ብለዋል።

በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከአየር መንገዱ በተጨማሪ፦
- ኢሚግሬሽን ፣
- የጉምሩክ ፣
- የብሄራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ፌደራል ፖሊስ የራሳቸው ድርሻ አላቸው ሲሉ ገልጸዋል።

በቅርቡ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት መንገደኛ ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ሙስናና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች እንጅ የአየር መንገዱ ሰራተኞች አይደሉም ብለዋል።

" ወርቅና ብር ይዘው መውጣት አይችሉም " ሲሉ የነበሩት አካላት የጉምሩክ ክፍል ሰራተኞች እንደሆኑ ጠቁመዋል።

አቶ መስፍን ፤ ወርቅና ብር ይዘው መውጣት አይችሉም የተባሉት ደንበኛ ጉዳይ ዋነኛው ቅሬታ እንደነበር አስታውሰው " ድርጊቱን የፈፀሙ የከስተም ወይም የጉምሩክ ክፍል ሰራተኞች ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

ግለሰቦቹን በካሜራ እገዛ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን ተናግረዋል።

በቀጣይም አየር መንገዱ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን የማይታገስ መሆኑንና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል፡፡

በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ የደህንነት ካሜራዎች እንዳሉም ተሰምቷል።

መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም እና WMCC ነው።

@tikvahethiopia
185.2K views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-18 14:49:39
#ኢትዮጵያ

" የትጥቅ ትግል ላይ ያለውም ጫካ የገባውም በሰላም የሚታገለውም ለእኛ ሁሉም እኩል ልጆቻችን ናቸው " - ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ፤ በሀገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎች ያሉ ጦርነት / ግጭቶች ሀገራዊው የምክክር ሂደት እንዲጓተት ምክንያት እንደሆነ አሳውቀዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን ምን አሉ ?

- በተለያዩ የሀገሪቱ ቦታዎች ያሉት የሰላም እጦቶች የሀገራዊ የምክክሩ ስራ እንዲጓተት ሆኗል።

- በሄድንበት ህዝቡ " ሰላም ናፍቆናል ቶሎ ቶሎ በሉ ይላል " የሰላም እጦት ደግሞ ያንን ለማድረግ አይፈቅድም።

- " ተጓቷል " የሚባለው እውነት ነው። ሁሉም ጋር በየወረዳው ስንሄድ ያለው የሰላም ጥማት ነው።

- ህብረተሰቡ መጓጓዝ ይፈልጋል፣ ሰርቶ ማደር ይፈልጋል፣ ሰላም ይፈልጋል የሰላም እጦት ደግሞ ሁሉንም ህብረተሰቡን ነው የሚጎዳው ሴቶችን ፣ ወጣቶችን ህፃናትን።

- የሚሞቱት የኛው ልጆች ናቸው የሚገድሉትም ልጆቻችን ናቸው የነዚህ ልጆቻችን ጥያቄ በአጀንዳ መልክ ተቀርጾ ወደ ምክክር መመንዘር አለበት። ያ ነው የሚሻለው።

- አንዳንዶች " እናተ ከመጣችሁ ከተቋቋማችሁ (ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን) በኃላ ግጭቱ የበዛው " ይላሉ ከእኛ ጋር እነዚህ ግጭቶች / ጦርነቶች ምንም ግኙነት የላቸውም። እኛ ስርዓት ተከትለን አከታችነትና አሳታፊነትን ስለሚል አዋጁ ያንን ተከትለን ነው እየሰራን ያለነው።

- ሰላም ያልጠማው ወገን የለም። ሁሉም ማለት ይቻላል። በትጥቅ ትግል ላይ ያሉትም ቢሆን ሰላም ይጠላሉ ብዬ በጭራሽ አላስብም።

- እኛ በሶስት ዓመት ውስጥ ስራችንን ሰርተን ጨርሰን መውጣት አለብን ብለን እናስባለን ግን ከአቅማችን ውጭ የሆኑ ጉዳዮች ከተፈጠሩ እኛ ከምንፈታው አይደለም።

- የትጥቅ ትግል ላይ ያለውም ጫካ የገባውም በሰላም የሚታገለውም ለእኛ ሁሉም እኩል ልጆቻችን ናቸው። በችግሮቻቸው ዙሪያ እንድንመክር ጥሪ እያቀረብን ነው።

- ታጣቂዎችን ወደ ምክክር ለማምጣት በተዘዋዋሪ እንሞክራለን ፣ ጥሪ እናደርጋለን፤ ታጣቂዎች እዚህ አዲስ አበባ አካባቢ ይኑሩ አይኑሩ አላውቅም ግን ጥሪ እናደርጋለን። ልጆቻችን ናቸው።

- ኦሮሚያ ይሁኑ ፣ ቤኒሻንጉል ይሁኑ ፣ አማራ ይሁኑ በየቦታው ያሉት ሁሉም ልጆቻችን ናቸው (ታጥቀውም የሚንቀሳቁትን)። ልጆቻችን ወደ ትምህርት ቤት ፣ ወደ ስራ ፣ ወደ ልማት እንጂ መሳሪያ ታጥቀው አካል ጉዳት፣ ህይወት መጥፋት ውስጥ እንዲገቡብን አንፈልግም።

- ከሁሉ በላይ የጦርነት ክፋቱ አእምሮን #ይሰብራል የተሰበረ አእምሮ ደግሞ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሸጋገራል፤ ስለዚህ መቆም አለበት። ወደ ትጥቅ ያስገቧችሁን ምክንያቶች ወደፊት አምጧቸውና ተወያዩባቸው። ትጥቁን አስቀምጡትና ወደ ምክክሩ ኑ ! በእርግጠኝነት ወደ ምክክር የመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች መግባባታቸው አይቀርም።

- የአንድ ወገን ወገተኞች በጭራሽ አይደለንም። የምንደክመው ሀገራችን ሰላም እንድትሆን ብቻ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የፕሮፌሰር መስፍን አርአያን ቃል ያዳመጠው ለሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ከሰጡት ቃለምልልስ ነው።

@tikvahethiopia
189.7K viewsedited  11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ