Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ሪፖርተር - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_reporter — አዲስ ሪፖርተር - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_reporter — አዲስ ሪፖርተር - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @addis_reporter
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 40.65K
የሰርጥ መግለጫ

🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !
=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !
🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addis_reporter_bot
#ADDIS ABABA, ETHIOPIA

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-25 11:18:07
በአልጄሪያ በተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት የ34 ሰዎች ህይወት አለፈ

በመላው አልጄሪያ በተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት ቢያንስ 34 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የአልጄሪያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በ16 አውራጃዎች 97 ሰደድ እሳት በደን፣ በሰብል እና በእርሻ መሬት ላይ በትላንትናው እለት ጉዳት አድርሷል።

ወደ 8,000 የሚጠጉ የእሳት አደጋ ተከላካዮች እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰሩ መሆናቸውን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል። በተጨማሪም 26 ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን 1,500 ያህል ሰዎች በፌናያ፣ ቤጃያ፣ ዝባርባር እና ቡዪራ ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል። በቤጃያ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ 10 ወታደሮች መሞታቸውን የአልጄሪያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከአልጀርስ በስተምስራቅ ተራራማ ካቢሊ ክልል ውስጥ እጅግ በጣም ሰፊ የሆነ ሰደድ  እሣት በከፍተኛ ንፋስ እየተገፋ በቤጃያ እና ጂጄል የባህር ዳርቻ ከተሞች ወደሚገኙ የመኖሪያ አካባቢዎች እየተሰራጨ ይገኛል።የቃጠሎው መንስዔ ላይ የፍትህ አካላት ምርመራ መጀመራዠውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

በሰሜናዊ አልጄሪያ በቅርብ ቀናት ውስጥ ከፍተኛ ሙቀት እየተመዘገበ ሲሆን የሙቀት መጠኑ 48 ዲግሪ ሴንቲግሬድ  ደርሷል። በሰሜን አፍሪካ ውስጥ በተለያዩ ክልሎች ያለው የሙቀት መጠን ከመደበኛው እስከ 7 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ከፍ ብሏል።የአልጄሪያ የሚቲዎሮሎጂ ጽህፈት ቤት በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ከ48 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ የሙቀት መጠኑ እስከ ወሩ መጨረሻ ሊቀጥል እንደሚችል አስጠንቅቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
1 view08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-25 11:17:27 ኢትዮጲያ በ2015 ዓመት ከአህያ ስጋ የወጪ ንግድ 3 መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገቢ አገኘች

በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ የአህያ ስጋን ወደ ሆንግኮንግ በመላክ 3 መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር የውጪ ምንዛሬ ገቢ ማግኘቷን የእንስሳት ልማት ኢንስትቲዩት አስታውቋል፡፡በኢንስትቲዩቱ ምክትል ዋና  ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ሳህሉ ሙሉ በተለይ ከብስራት ሬድዮና ቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት፣ ከአህያ ስጋ ውጪ የአህያ ቆዳን እንደ ቻይና ያሉ ሃገራት ለመድሃኒትነት በስፋት ሲጠቀሙበት የሚስተዋል በመሆኑ የስጋ ምርቱን ወደ ሆንግኮንግ እንዲላክ ተደርጓል ብለዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
1 view08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-25 08:23:23
#ጤናመረጃ

የአብሽ 10 የጤና ጥቅሞች!


አብሽ ለጤና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ያውቃሉ?

ለልብ ድካም፣ ለደምግፊት፣ ኮሌስትሮል ለመቀነስ፣ ለጨጓራና በስካር በሽታ ለሚሰቃዩ ፍቱን መድሃኒት ነው::ገና ለወለዱ እናቶችም የጡታቸውን መጠን የተወሰነ ለመጨመር ይጠቅማል።

ጥቅሞቹ በዝርዝር ቀጥሎ ቀርበዋል፦

የስኳር በሽታን ለመቆጣጠር ይረዳል፦ አብሽ ደም ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን በመቆጣጠር ኢንሱሊን መቋቋምን ይቀንሳል።

የልብ በሽታን ያስወግዳል፦የልብ ጉዳትን ለመከላከልና ኦክሲዳቲቭ ውጥረት ለማስወገድ ይረዳል።

የወር አበባ ቁርጥማትን ያስታግሳል፦አብሽ ከቁርጥማት በተጨማሪ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽና ድካምን ለመቀነስ ይረዳል።

የጡት ወተት ምርትን ያሻሽላል፦አብሽን መጠጣት የወተት ምርትን የሚጨምር ውህድ ስላለው፤ ለሚያጠቡ እናቶች ይረዳል።

የምግብ መፍጨት ችግርን ይረዳል፦የሆድ ድርቀትንና ከጨጓራ መቆጣት የተነሳ ለሚከሰት የምግብ መፍጨት ችግርን ለመከላከል ይረዳል።

የጸጉር መሳሳትን ለመከላከልና ለፀጉር እድገት ጠቃሚ ነው።የተፈጨ አብሽን ሳይወፍር በብርጭቆ ውሀ በማዋሀድ መቀባት።

አብሽ መጠጣት አቅም ማጣትን ለማከምና የወሲብ ችሎታን ለመጨመር ይረዳል።

አብሽ መጠጣት ብጉርን ለመከላከል ይረዳል።

ፀረ-እርጅና ጥቅም አለው፦ለቆዳችን አስደናቂ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን የእርጅና ምልክትን እንደ የቆዳ መጨማደድና ቀጫጭን መስመርን ያስወግዳል።

ቆዳን ለማርጠብ፦ የአብሽ የሚሙለጨለጨው በሀሪ የደረቁ ቆዳዎችን በማስወገድ ቆዳችን እንዲረጥብ ይረዳናል።

አጠቃቀሙ፣ በ1ብርጭቆ ውሃ ውስጥ 2 የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ አብሽ በማዋሀድ መጠጣት። ተፈጥሯዊ ስለሆነ ምንም አይነት ጉዳት የለውም። ክብደት እንዳይጨምሩ በመጠኑ ይጠቀሙ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
1.6K views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-25 08:22:34
WORK VISA CANADA 2023
---—----------------------------      
     አስደሳች ዜና ለመላው ኢትዮጲያውያን

ከ 5000- በላይ ክፍት ቦታዎች በ0 አመት እና በልምድ

Number of Positions: 5000+ positions 0 EXP and with Exp

በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች የወጣ የስራ ማስታወቂያ

የኮንትራት ሰራ ወደ ካናዳ
የስራ ማስታወቂያ በ 0 ዓመትና በልምድ
የስራው አይነት ኮንትራት
ብዛት 5000+
ደሞዝ: በስምምነት $ በዶላር
አየር ትኬት በነፃ
ቪዛ በነፃ

ፈጥነው ታች ባለው ሊንክ ይመዝገቡ

Apply Now
                                 
https://addiszemenvacancy.com/2023/03/18/canada-jobs-2023/


---------Follow Our Website---------
                      
         https://addiszemenvacancy.com

------------- Telegram-----------
      https://t.me/addis_zemen_vacancy
1.5K views05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-25 08:22:22 መርጌታ  የተለያዬ ነገሮችን ለማሰራት ከፈለጉ በስልክ ደውለው ማውራት ይቻላል።
1.ለሀብት 
2.ለገበያ
3.ለብልት
4.ለትምህርት
5.ለመስተፋቅር
6. ለህመም
7.ለዓይነ ጥላ
8. ለበረከት
9. ለግርማ ሞገስ
10. ለትዳር
11. ለቁማር
12. ትዳር ለገረገረው መፍትሔ አለ

0938234097
ይደዉሉ::መርጌታየተለያዬ ነገሮችን ለማሰራት ከፈለጉ በስልክ ደውለው ማውራት ይቻላል።
1.ለሀብት 
2.ለገበያ
3.ለብልት
4.ለትምህርት
5.ለመስተፋቅር
6. ለህመም
7.ለዓይነ ጥላ
8. ለበረከት
9. ለግርማ ሞገስ
10. ለትዳር
11. ለቁማር
12. ትዳር ለገረገረው መፍትሔ አለ

0938234097
ይደዉሉ::
1.4K views05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 21:59:29
"ያልዘሩት አይበቅልም " እንደሚባለው የትግራይ ኦርቶዶክስን በመነጠል የህወሓትን እቅድ እንዲያስፈፅሙ የታቀደው ገና በ1971 ዓ.ም ነው።
የቀድሞው የህወሓት መስራች እና ታጋይ
ዶ/ር አረጋዊ በርሄ መፅሃፍ ላይ የተገኘ መረጃ ነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3.5K views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 17:29:42 ቅዱስ ሲኖዶስ በትግራይ የተፈፀመውን የዶግማ፣ የቀኖና እና አስተዳደራዊ ጥሰት አስመልክቶ ተወያይቶ ተገቢውን ለመወሰን ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪ አስተላለፈ
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ
  1. በክልል ትግራይ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በክልሉ ከሚገኙት አህጉረ ስብከት ጋር ተቋርጦ የነበረውን መዋቅራዊ ግንኙነት ችግር በውይይት እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪና ልዑካኑን በአካል ልኮ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ተብለው በሚጠሩበት በማዕከላዊ ትግራይ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 15 እና 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በተከናወነ ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት መፈጸሙን በመገናኛ ብዙኃን ለማወቅ ችለናል፡፡ በመሆኑም በዚህ የዶግማና የቀኖና ጥሰት ተግባር የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በእጅጉ አዝኗል፡፡ 

2. በመሆኑም የተከሰተው የዶግማ፣ የቀኖና እና አስተዳደራዊ ጥሰት አስመልክቶ ተወያይቶ ተገቢውን ለመወሰን ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪ ተላልፏል፡፡

3. የስብሰባው ቀን ሊራዘም የቻለው በውጭው ክፍለ ዓለማት ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት መገኘት ስላለባቸው የጉዞ ቀኑ እንዳያጥር እና በሀገር ውስጥ የሚገኙትም ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት ለአገልግሎት ወደ አህጉረ ስብከታቸው የሄዱ በመሆኑ ለመመለሻ የሚያስፈልገውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡

4. በየደረጃ ያሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሥራ ኃላፊዎች እና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ምዕመናን ከአሁን ቀደም በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በደረሰው ፈተና በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን በመቆም ላሳያችሁት ጽናት እያመሰገንን አሁንም በደረሰው ፈተና እንዳሁን ቀደሙ ሁሉ በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን ጸንታችሁ እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

5. በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ በትግዕስት እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡

6. ምንም እንኳን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ ጥሪው በደብዳቤ የተላለፈ ቢሆንም የመልእክቱ በፍጥነት መድረስ ካለው ስጋት አንጻር የችግሩን ተደጋጋሚነትና አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ክፍለ ዓለማት የምትገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ተጠቃላችሁ ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ እንድትመጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

7. ሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን ሚዲያዎችና ሌሎች መገናኛ ብዙኃን ይህን መልዕክት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን መልእክቱን በማስተላለፍ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ በቤተ ክርስቲያናችን ስም እንጠይቃለን፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4.6K views14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 16:00:11
400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ሥር ዋለ

መነሻውን ከጅቡቲ ወደብ አድርጎ መዳረሻውን ወረታ ከተማ ለማድረግ የተንቀሳቀሰው 400 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ የጫነ ተሳቢ ተሽከርካሪ፤ ከታሰበው ቦታ ሳይደርስ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

ሕገ ወጥ ድርጊቱ የተፈጸመው በባህርዳር ከተማ ሰባታሚት ቀበሌ ሐምሌ 16/2015 ሲሆን፤ አሽከርካሪው በአሳቻ ሰዓት በመጠበቅ ከሌሊቱ 6:00 ላይ የአፈር ማዳበሪያውን በሕገ ወጥ መንገድ ለግለሰቦች ሲያከፋፍል በኅብረተሰቡ ጥቆማ መያዙን የሰባታሚት ቀበሌ ፖሊስ ኦፊሰር ኮንስታብል ዮሐንስ ጥላሁን ተናግረዋል።

አብዛኛው ማዳበሪያ ሳይራገፍ ከነተሽከርካሪው ቢያዝም፤ ከ140 ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለግለሰቦች በሕገ ወጥ መንገድ መሰራጨቱ የተገለጸ ሲሆን፤ ፖሊስ ባደረገው ቤተ ለቤት ፍተሻ ከተሽከርካሪው ተራግፎ በግለሰቦች ቤት የተከዘነ በርካታ የአፈር ማዳበሪያ መገኘቱም ተነግሯል፡፡

በዚህም 89 ኩንታል ማዳበሪያ በአንድ ግለሰብ ቤት የተገኘ ሲሆን፤ 24 ኩንታል ማዳበሪያ ደግሞ በአንድ ግለሰብ ቤት በአልጋ ሥር እና በኩሽና ውስጥ መገኘቱ ተገልጿል።

አሽከርካሪው ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን ኮንስታብል ዮሐንስ ገልጸው፤ ኅብረተሰቡ እንደዚህ አይነት ሕገ ወጥ ተግባርን እንዲያወግዝ ጠይቀዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

አማራ ለሆኑ ብቻ

https://t.me/+fQqpVIV6_Q82ZGQ0
https://t.me/+fQqpVIV6_Q82ZGQ0
4.5K views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 14:58:10
ለኢትዮ ጅቡቲ ከባድ መከና አሽከርካሪዎች

ከቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል ጋር በተያያዘ ከዛሬ ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከጨለንቆ ከተማ እስከ ቀርሳ ከተማ ባለው ዋናው የተሸከርካሪ መንገድ ላይ ከባድ መኪና ማለፍ የተከለከለ መሆኑን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ እና የበዓሉ የጸጥታ ኮማንድ አሳውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4.2K views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 13:19:55
ትዊተር አርማውን ከምናውቃት ወፍ ወደ ‘ኤክስ’ ምልክት ሊቀይር መሆኑን ኢላን መስክ ገለጠ!

የትዊተር ባለቤት ኤላን መስክ የትዊተር ‘ሎጎ’ ከተለመደው የወፍ ምልክት ወደ ‘ኤክስ’ [X] ሊቀይር መሆኑን ገልጧል።የቢዝነስ አርማውን ወደ ኤክስ ኮርፕ የቀየረው መስክ “እንደውም ይህን ሊሆን የሚገባው ቀድሞ ነበር” ብሏል።

ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ቢሊየነሩ ልክ እንደ ቻይናው ዊቻት ኤክስ የተባለ “ሁሉን ያካተተ” መተግበሪያ የመሥራት ሐሳብ አለው።የትዊተር አርማ የሆነችው ወፍ እንደምትቀየር እሑድ ዕለት ያሳወቀው መስክ “በቃ ሁላችንም የትዊተር አርማን ቻው የምንልበት ጊዜ ተቃርቧል። ቀስ በቀስ ደግሞ ሁሉንም ወፎች” ብሏል።

የዛኑ ዕለት አዲስ ጊዜያዊ አርማ ይፋ እንደሚደረግም ያሳወቀው መስክ የእንግሊዝኛ ኤክስ ፊደል ምልክት ያለበት አርማ ለጥፏል።የትዊተር ሥራ አስፈፃሚ ሊንዳ ያካሪኖ በትዊተር ገፃቸው አርማ መቀየሩ አስደሳችና አዲስ ጅማሮ ነው ብላለች።በእስያ ሃገራት ለምሳሌ በሕንድ ፔይቲኤም፤ በኢንዶኔዥያ ደግሞ ጎጄክ የሚባሉ መተግበሪያዎች ሁሉን አቀፍና በርካቶች የሚጠቀሙባቸው ናቸው።

Via BBC

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

አማራ ለሆኑ ብቻ

https://t.me/+fQqpVIV6_Q82ZGQ0
https://t.me/+fQqpVIV6_Q82ZGQ0
4.4K views10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ