Get Mystery Box with random crypto!

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

የሰርጥ አድራሻ: @fanatelevision
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 183.29K
የሰርጥ መግለጫ

This is FBC's official Telegram channel.
For more updates please visit www.fanabc.com

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-12-10 04:01:27
ህጻናት ላይ የሚከሰተው የዐይን ካንሰር ምልክቶች እና ህክምናው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓይን ካንሰር (ረቲኖብላስቶማ) በዓይን የኋላኛው ክፍል ብርሃን መቀበያ ረቲና የሚነሳ የካንሰር ዓይነት ነው፡፡ የህጻናት የዓይን ካንሰር ህክምና ስፔሻሊስት ዶክተር አዲሱ ወርቁ ህጻናት ላይ ስለሚከሰተው የዓይን ካንሰር ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ በቆይታቸው እንደገለጹት ፥ የዓይን ካንስር አልፎ አልፎ በዘር ሊተላለፍ እንደሚችል የሚገለጽ ቢሆንም አብዛኛውን…

https://www.fanabc.com/archives/225920
13.7K viewsedited  01:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-09 18:56:16
የሱዳን ግጭት በሰለማዊ መንገድ እንዲፈታ ኢትዮጵያ ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች - ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ግጭት ሰለማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ኢትዮጵያ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ41ኛው የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ዛሬ ጠዋት ጅቡቲ በመገኘት ተካፍለዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ ‘’ወንድሜ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር...https://www.fanabc.com/archives/225923
16.6K viewsedited  15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-07 19:20:19
በሰላማዊ ሰልፍ ሽፋን አዲስ አበባን የሁከትና የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች ሴራ መክሸፉን የጋራ ግብረ- ኃይሉ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰላማዊ ሰልፍ ሽፋን አዲስ አበባን የሁከትና የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ የሽብር ተልዕኮ ተቀብለው በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች ሴራ መክሸፉን የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታውቋል፡፡ የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል እንዳስታወቀው÷ ፅንፈኛ ኃይሎች እና የሽብር ቡድኖች በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች በትጥቅ የታገዘ ግፍና ግድያ…

https://www.fanabc.com/archives/225619
13.9K viewsedited  16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-07 18:16:54
የቡና ግንድ አድርቅ በሽታን መከላከል የሚያስችል መድኃኒት በምርምር ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቡና ግንድ አድርቅ በሽታን መከላከል የሚያስችል መድኃኒት በምርምር ማግኘቱን አስታወቀ። ዩኒቨርሲቲው የቡና ግንድ አድርቅ በሽታን በምስራቅ አፍሪካ በምርታማነት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ያለመ አውደ-ጥናት አካሂዷል፡፡ የቡና ግንድ አድርቅ በሽታ መድኃኒት የሌለው ሲሆን በከፍተኛ ሁኔታ የቡና ምርታማነት ላይ ጉዳት እያደረሰ የሚገኝ ነው፡፡ ወደ…

https://www.fanabc.com/archives/225613
13.7K viewsedited  15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-18 04:19:28
የልጆችን በሽታ የመከላከል አቅም እንዴት መጨመር ይቻላል?

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ህጻናት በቀላሉ እንዳይታመሙ በሽታ የመከላከል አቅማቸው መጎልበት አለበት፡፡ ይህንንም ለማድረግ መሠረታዊ መርሆችን መከተል ይገባል፡፡ እነሱም፡- -ጡት ማጥባት፡- ቢያንስ ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ጡት ብቻ ማጥባት የራሱ የሆኑ ጠቀሜታዎችን የሚሰጥ ሲሆን÷ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጡት ማጥባት አለርጂ የመያዝ እድልን ይቀንሳል፡፡ – በየጊዜው እጅ መታጠብ፡- ልጆችን ሲያስነጥሱ፣ ሲያስሉ…

https://www.fanabc.com/archives/222159
13.6K viewsedited  01:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-18 02:19:54
በታዳጊ ሀገራት የጤና አገልግሎትን አስተማማኝ ለማድረግ የፀሐይ ኃይል አማራጭን መጠቀም እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2016 (ኤ ፍ ቢ ሲ) የፀሐይ ኃይል በታዳጊ ሀገራት የጤና አገልግሎትን አስተማማኝ ለማድረግና ህይወትን ለመታደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ሲሉ ባለሙያዎች ተናገሩ፡፡ በታዳጊ ሀገራት የሚገኙ ሁሉም የጤና ተቋማት በአምስት ዓመታት ውስጥ ከ 5 ቢሊየን ዶላር ባነሰ ወጪ የፀሐይ ኃይልን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ኃይል ሊያገኙ ይችላሉ ሲሉ ባለሙያዎች በCop28 የመከራከሪያ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/222164
13.5K views23:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-12 18:25:46
ማስታወቂያ

የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያዎን 
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት እና በሲቢኢ ብር  
ባሉበት፣ በየትኛውም ሰዓት፣ በማንኛውም የስልክ አይነት መቾትዎ እንደተጠበቀ በቀላሉ ይክፈሉ!
አሊያም በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የሲቢኢ ብር ወኪል ዘንድ በመሄድ መክፈል ይችላሉ፡፡
**

የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ካልሆኑ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመቅረብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉ ሲሆን፣ የሲቢኢ ብር አገልግሎት መጠቀም ካልጀመሩ ደግሞ

• ወደ *847# በመደወል፣ ወይም 
• የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ ተመዝግበው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡ 

ለበለጠ መረጃ ወደ 951 ነጻ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ።
የሲቢኢ ብር መተግበሪን ለማውረድ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
15.9K views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-12 17:45:49
በቤይሩት ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤይሩት ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች በተደረገው ውድድር የቦታውን ሪከርድ በመስበር አሸነፉ፡፡ በቤይሩት ማራቶን በወንዶች ጋዲሳ ጣፋ 02፡10፡34 በመግባት የቦታውን ሪከርድ በማሻሻል በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ጎጃም በላይነህ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል፡፡ እንዲሁም በሴቶች በተደረገው የማራቶን ውድድር ሙሉጎጃም ብርሃን 02፡19፡32 በመግባትና የቦታውን ሪከርድ በማሻሻል በአንደኝነት ስታጠናቅቅ ጌጤ…

https://www.fanabc.com/archives/221210
14.9K viewsedited  14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-12 16:56:04
ስዊዘርላንድ የኒውክሌር ኃይል የመጠቀም እቅዷን እንደምታራዝም ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አውሮፓዊቷ ሀገር ስዊዘርላንድ በኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ያሉ ሁሉም መሣሪያዎች በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኙ እስከሆነ ድረስ ሥራቸውን ይቀጥላሉ ስትል ገልፃለች፡፡ ስዊዘርላንድ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በኤሌክትሪክ አቅርቦት እጥረት ስጋት እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የኒውክሌር ኃይል አጠቃቀምን የማራዘም አዝማሚያ እየተስተዋለ መሆኑን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡ ሀገሪቱ እስከ…

https://www.fanabc.com/archives/221207
14.8K viewsedited  13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-12 15:37:28
በሶማሌ ክልል የኮሌራ በሽታ እንዳይስፋፋ እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በሶማሌ ክልል እየጣለ ያለውን ዝናብ ተከትሎ የኮሌራ በሽታ እንዳይስፋፋ ህብረተሰቡን በማስገንዘብ የቅድመ መከላከል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ሀዋ ሱሌማን እንደገለጹት÷ በክልሉ ጅግጅጋ እና ቀብሪበያህን ጨምሮ በአምስት ከተሞች የኮሌራ ወረርሽኝ ተከስቷል። በሽታውን ለመቆጣጠርም ቢሮው ከጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮዽያ ህብረተሰብ…

https://www.fanabc.com/archives/221204
14.4K viewsedited  12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ