Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ጊዮርጊስና ባህር ዳር ከተማ አቻ ተለያዩ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) | FBC (Fana Broadcasting Corporate)

ቅዱስ ጊዮርጊስና ባህር ዳር ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስና ባህር ዳር ከተማ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ።

ዛሬ ምሽት 1፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ ቸርነት ጉግሳ በ30ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ጎል ባህር ከተማ ሲመራ ቢቆይም፤ በጭማሪ ሰዓት 90+5' ላይ አማኑኤል ኤርቦ ባስቆጠራት ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

ቀን 10፡00 ላይ የተካሄደው የፋሲል ከነማ እና የሀምበሪቾ ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ መረጃ አመልክቷል።