Get Mystery Box with random crypto!

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

የሰርጥ አድራሻ: @fanatelevision
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 183.29K
የሰርጥ መግለጫ

This is FBC's official Telegram channel.
For more updates please visit www.fanabc.com

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-02-05 10:10:37
የባሕር ዳር አባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ የአስፓልት ንጣፍ ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በባሕር ዳር ከተማ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የአባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የአስፓልት ንጣፍ ሥራ መጀመሩን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ገለጸ፡፡ ከሄኒ ጋርደን አደባባይ እስከ ዘንዘልማ መገንጠያ የሚዘልቀው 4 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የባሕር ዳር አባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ የአፈር ቆረጣና ሙሌት…

https://www.fanabc.com/archives/233728
13.7K viewsedited  07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-05 10:05:32
በቺሊ በተከሰተ ሰደድ እሳት ቢያንስ የ112 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቺሊ በተከሰተ የሰደድ እሳት አደጋ እስካሁን ቢያንስ የ112 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡ በቺሊ ቫልፓራሶ በተሰኘ ግዛት በሚገኝ ደን ላይ የተከሰተውን ሰደድ እሳት ተከትሎም የአስቸኳይጊዜ አዋጅ መታወጁን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ገብርኤል ቦሪክ አስታውቀዋል፡፡ በአደጋው ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል አብዛኛዎቹ በግዛቷ የሚገኝ የባሕር ዳርቻን ሲጎበኙ የነበሩ ሰዎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/233725
12.8K viewsedited  07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-05 09:22:46
በዲጂታል የነዳጅ ግብይት ሥርዓት ከ155 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዲጂታል የነዳጅ ግብይት ሥርዓት ከ155 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት መከናወኑን የነዳጂና ኢነርጅ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል ሥርዓት መካሄድ ከጀመረበት ሚያዝያ 2015 ጀምሮ እስካሁን ከ155 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት መፈጸሙን የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር በቀለች ኩማ ተናግረዋል፡፡ ግብይቱ በዲጅታል መሆኑ በዘርፉ ያለውን…

https://www.fanabc.com/archives/233705
12.8K viewsedited  06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-30 22:19:12

13.4K views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-25 14:46:19
በውጪ የሚኖሩ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በመዲናዋ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪን ተቀብለው ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በአዲስ አበባ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።

በዛሬው ዕለትም ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚዬምን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

በቀጣይም ብሔራዊ ሙዚዬምን እና እንጦጦ ፓርክን እንደሚጎበኙ የአዲስ አባበ ከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የጉብኝት ተሳታፊዎች አዲስ አበባ ከተማ እያሳየች ያለችው ዕድገት እና ሰላሟ በውጭ ከሰሙት የተለየ እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡

መታሰቢያ ሙዚዬሙ የዓድዋ ዘማቾችን ታሪክ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ በመሆኑ ትናንትን ከዛሬና ከነገ ያስተሳሰረ ትልቅ ስራ ነው ብለዋል፡፡

ጉብኝቱ በቱሪዝም ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ ነው ተብሏል።
12.8K views11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-27 14:09:57
ለሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን የተደረገ ጥሪ #BackToYourOrigins
12.6K viewsedited  11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-27 13:26:33
በያቤሎ ጠቅላላ ሆስፒታል መንታ ህጻናት ተጣብቀው ተወለዱ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ በያቤሎ ጠቅላላ ሆስፒታል መንታ ህጻናት ተጣብቀው መወለዳቸው ተገለጸ። የያቤሎ ጠቅላላ ሆስፒታል የጽንስና ማህጸን ስፔሻሊስት ዶክተር ዋሪዮ ዱባ እንደተናገሩት፤ የተወለዱት ህጻናት የተጣበቁት በደረት አካባቢ ነው። በሆስፒታሉ የቀዶ ህክምና ክፍል ሐኪም የሆኑት ዶክተር ግዛቸው ታከለ በበኩላቸው ተጣብቀው ለተወለዱት ህጻናት ተጨማሪ ምርመራና ህክምና እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

https://www.fanabc.com/archives/228379
13.2K viewsedited  10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-27 12:22:03
አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሉሜ ወረዳ በበጋ መስኖ የለማ የስንዴ ማሳ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ በበጋ መስኖ የለማ የስንዴ ማሳ ጎብኝተዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት÷ ከአራት ዓመታት በፊት በክልሉ በ7 ሺህ ሔክታር መሬት ላይ በመስኖ የተጀመረው የስንዴ ልማት አሁን ላይ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታርን ተሻግሯል። በምርት ዘመኑ…

https://www.fanabc.com/archives/228414
13.5K viewsedited  09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-27 11:23:42
ኒው ዴልሂ ከተማ እንቅስቃሴን በሚያውክ ከባድ ጭጋግ መዋጧ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ ዋና ከተማ ኒው ዴልሂ እና በሰሜን የህንድ አካባቢዎች ከፍተኛ ቅዝቃዜ እና ጥቅጥቅ ያለ ጭጋግ የጉዞ እንቅስቃሴን እያደናቀፈ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በዚህም የተነሳ በከተማዋ ከ100 በላይ በረራዎች እና 25 የባቡር ጉዞዎች እንዲዘገዩ መደረጋቸውም ተመላክቷል። ከተማዋ ከወቅቱ ጭጋጋማ ቀናት አንዱን እያስተናገደች ሲሆን÷ በዛሬው ዕለት የእይታ ሁኔታውም ከ50…

https://www.fanabc.com/archives/228397
13.5K viewsedited  08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-27 10:42:20
አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአሜሪካ አምባሳደር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው የጋራ በሆኑ ወቅታዊ፣ ሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

https://www.fanabc.com/archives/228383
12.9K viewsedited  07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ