Get Mystery Box with random crypto!

በውጪ የሚኖሩ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በመዲናዋ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው አዲስ አበ | FBC (Fana Broadcasting Corporate)

በውጪ የሚኖሩ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በመዲናዋ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪን ተቀብለው ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በአዲስ አበባ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።

በዛሬው ዕለትም ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚዬምን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

በቀጣይም ብሔራዊ ሙዚዬምን እና እንጦጦ ፓርክን እንደሚጎበኙ የአዲስ አባበ ከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የጉብኝት ተሳታፊዎች አዲስ አበባ ከተማ እያሳየች ያለችው ዕድገት እና ሰላሟ በውጭ ከሰሙት የተለየ እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡

መታሰቢያ ሙዚዬሙ የዓድዋ ዘማቾችን ታሪክ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ በመሆኑ ትናንትን ከዛሬና ከነገ ያስተሳሰረ ትልቅ ስራ ነው ብለዋል፡፡

ጉብኝቱ በቱሪዝም ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ ነው ተብሏል።