Get Mystery Box with random crypto!

በቺሊ በተከሰተ ሰደድ እሳት ቢያንስ የ112 ሰዎች ሕይወት አለፈ አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 | FBC (Fana Broadcasting Corporate)

በቺሊ በተከሰተ ሰደድ እሳት ቢያንስ የ112 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቺሊ በተከሰተ የሰደድ እሳት አደጋ እስካሁን ቢያንስ የ112 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡ በቺሊ ቫልፓራሶ በተሰኘ ግዛት በሚገኝ ደን ላይ የተከሰተውን ሰደድ እሳት ተከትሎም የአስቸኳይጊዜ አዋጅ መታወጁን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ገብርኤል ቦሪክ አስታውቀዋል፡፡ በአደጋው ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል አብዛኛዎቹ በግዛቷ የሚገኝ የባሕር ዳርቻን ሲጎበኙ የነበሩ ሰዎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/233725