Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seledadotio — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seledadotio
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.55K
የሰርጥ መግለጫ

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-07 20:01:21
ቶኪዮ አዲስ ባበለፀገችው መተግበሪያ የተነሳ ቱሪስቶች እየጎረፉላት ነው ተባለ

ቶኪዮ በሚገኝ ባቡር ጣቢያ ውስጥ የተለያዩ ሀገራት ቋንቋዎችን ከሚናገሩ ቱሪስቶች ጋር ገጽለገጽ በመተያየት የሚተርጉም የስክሪን አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል፡፡

በሴቡ ሺንጁኩ ባቡር ጣቢያ ፖሊግሎት የሚል መጠሪያ የተሰጠውና የገጽለገጽ መተያያ የመተርጎሚያ ስክሪን  1ሜትር በ40 ሳንቲሜትር ቁመት ያለው ሲሆን፤ በባቡር ጣቢያው ማዕከላዊ ስፍራ ላይ በምትገኝ አስተናጋጅ ድጋፍ ሰጪነት የውጭ ዜጎች የሚናገሩትን ቋንቋ ወደ ጃፓንኛ፤ የጃፓንኛውን ደግሞ እነሱ ወደሚናገሩት ቋንቋ በድምጽ እያሰማ በጽሁፍ ደግሞ ስክሪን ላይ ተርጉሞ እያሳየ በቀላሉ እንዲግባቡ አስችሏል፡፡

ጃፓን፤ በ12 የተለያዩ ቋንቋዎች የበለፀገውን የመተርጎሚያ ቴክኖሎጂ በባቡር ጣቢያው ውስጥ በመጠቀሟ በተግባቦት ችግር ምክንያት የሚቀሩ ቱሪስቶች እንዳይኖሩ ከማድረጉም በላይ ለጉብኝት የሚሄዱ የውጭ ዜጎችን ቁጥር እንደሚሳድገው የNHK ዘገባ አመልክቷል፡፡
793 views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 19:16:37
ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ለመሳተፍ ገና ካሁኑ ፍላጎታቸውን እያሳዩ ነው ተባለ

የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት በሚጀመረው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ውስጥ ለመሳተፍ ከወዲሁ ፍላጎታቸውን እያሳዩ መሆኑን የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አስታውቋል።

የካፒታል ገበያ ባለሃብቶች፣ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች ወይም መንግስት ለሚያስፈልጋቸው ኢንቨስትመንት ካፒታል በጥሬ ገንዘብ አልያም በአይነት የሚያሰባስቡበትና የሚያገኙበት ገበያ ነው፡፡

በተለይም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባሉበት ሆነው በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሳተፉ ሰፊ እድል ይፈጥራል የተባለ ሲሆን ይህም ካፒታል በማሰባሰብ፣ የገንዘብ ሥርዓቱን በአዲዲስ ፈጠራዎች በመደገፍ እና ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት የአገሪቱን ኢኮኖሚ ልማት ያግዛል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በቀላሉ ቢዝነስ ለመጀመር፣ ለማስፋፋት እና የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎችን በአፋጣኝ ለማግኘት እንዲሁም የውጭ ኢንቨስተሮችን በቀላሉ ለመሳብና ከትናንሽ ቢዝነሶች እስከ ትላልቅ ኮርፖሬሽኖች ለመመስረት እድል ይፈጥራል፡፡

ምንጭ - ኢዜአ
1.9K views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 18:50:21
ገና ሊለቀቅ ጥቂት ቀናት የቀረውን "ባርቢ" የተሰኘውን ፊልም ቬትናም በሃገሪቷ እንዳይታይ ከልክላለች።

ለምን ሲባል:-

ይህ ምናባዊ-አስቂኝ ፊልም ሊለቀቅ የታሰበው ሐምሌ 14, 2015 ነበር ነገር ግን ከ ፊልም ማስታወቅያው ላይ ባለው አንድ ትእይንት ሊከለከል ችሏል።

ታዲያ ይህ ትእይንት የሚያሳየው የ ቻይናን ካርታ ነበር እናም በካርታው ላይ ዘጠኝ ሰረዞች በቻይና ባህር ላይ አርፈው ይታያሉ እነዚህም ዘጠኝ ሰረዞች የሚያመለክቱት 3 ሚሊዮን ካሬ ኪሎሜትር የሚሸፍን ሃሌታው "ሀ" ቅርጽ ያለው የባህር ክፍል ሲሆን ይህ አካባቢ በ ነዳጅ እና በ ተፈጥሮ ጋዝ የበለጸገ ነው፤ ሆኖም ይህንኑ አከባቢ ቬትናም፣ ፊሊፒንስ፣ ብሩኔይ፣ ማሌዥያ እና ታይዋን ይገባኛል ጥያቄ ለረጅም ጊዜ ሲያቀቡ የቆዩ ቢሆንም ጉልቤዋ ቻይና ግን ጥያቄያቸውን ችላ በማለት በተለያዩ ታላላቅ ሚዲያዎች ላይ እነዚህ መሰመሮች እንዲታዩ እና የቻይና ባለቤትነቱን እንዲለመድ ግፊት እያደረገች ትገኛለች።

በዚህ ትእይንት ደስተኛ ያልሆነው የ ቬትናም ባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ይህ ፊልም በሃገሪቷ ውስጥ ጨርሶ እንዳይታይ አግዷል።
2.3K views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 18:40:10
Summer Python Programming.

ልጆችዎ በዚህ ክረምት መሰረታዊ የፕሮግራሚንግ እውቀት እንዲያገኙ ይፈለጋሉ?

የቴክኖሎጂ ተቀባይ ብቻ ሳይሆን የቴክኖሎጂ ፈጣሪ ለመሆን የፕሮግራሚንግ እውቀት ወሳኝ መሆኑንስ ያውቃሉ?

ኑ መሰረታዊውን የ21ኛው ክፍለ ዘመን ክህሎት እናስተዋውቆ::

በኮዲንግ ላይ ምንም አይነት እውቀት ወይንም የቀድሞ ልምድ አያስፈልግም, ፈላጎት ብቻ በቂ ነው

መሰረታዊ የፕሮግራሚንግ እውቀት, ለጀማሪ በሚሆን መልኩ የተዘጋጀ

ብቁ በሆኑ መምህራን

በተመጣጣኝ ዋጋ በ ወር 2000 ብር ብቻ


አድራሻ : 4 ኪሎ
በ ሳምንት 3 ሰዓት


ለመማር ማስተማር ስርአቱ ጥራት ሲባል ውስን ተማሪዎች ስለምናስተናገድ ፈጥነው ይመዝገቡ

ለመመዝገብ ከታች ያለውን link ይጠቀሙ ወይም ይደወሉልን

Register now: https://forms.gle/b1pU3C4C6GC61zmw5

ለበለጠ መረጃ :
@Abukiab or 0934170179


ፈጥነው ይመዝገቡ
2.4K views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 18:31:01
"ትልቅሰው ሪል እስቴት "
በመሃል ካዛንችስ እንደራሴ እጅግ ዘመናዊ  አፓርትመንቶችን እስከ ሰኔ 30 በማስተዋቂያ ዋጋ መሸጥ ጀምረናል ።
ትልቅ ሰው ሪል እስቴት
    የኔክሰስ ሆቴል
    የግራንድ ሆቴል
    የኢግል ፓክ ኢምፓርት ኤክስፓርት እና
    የስካይ ፔትሮሊየም እህት ኩባንያ ነው
ባለ 2 መኝታ
ባለ 3 መኝታ
የሚገርም ማራኪ እይታ ያላቸው !!!
ከአማራጭ አከፋፈል ጋር
100% በ1 አመት በ4ዙር
50/50 በባንክ

ለበለጠ መረጃ
@setu1988
0936606665
2.4K views15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 16:47:48
የመውጫ ፈተና መሰጠት ተጀመረ።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ ያደረገው የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን የመውጫ ፈተና በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀምሯል።

በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የመንግሥት እንዲሁም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ፈተናቸውን በ " ኦንላይን " መውሰድ ጀምረዋል። ዛሬ የመውጫ ፈተናቸውን መውሰድ የጀመሩት የጤና ተማሪዎች ናቸው።

በቀጣይ ሳምንት ሰኞ ደግሞ ከጤና ተማሪዎች ውጭ የሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች የመቅጫ ፈተናቸውን የሚወስዱ ይሆናል።

Via - Tikvahethiopia
3.6K views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 14:03:18
ከዘመዶቼ ይልቅ የምወደው ኔይማር ሀብቴን ይውረስ ያለው ሚሊየነር

አንድ ብራዚል ውስጥ የሚገኝ ልጥጥ ባለሃብት ለኔይማር ካለው ፍቅር የተነሳ ሲሞት ኔይማር ሙሉ ሃብቱን እንዲወርስ መናዘዙ ተሰምቷል።

ባለሀብቱ አጠቃላይ ያለው ንብረት በገንዘብ ሲተመን ወደ 200 ሚሊየን ዶላር  የሚደርስ ሲሆን በኔይማር ላይ የሚደርሱ ትችቶችንም በመቃወም ይታወቃል ተብሏል።

ያለው ይጨመርለታል እንዲሉ አበው ኔይማር አሁን ላይ የገንዘብ እጥረት ያለበት ሰው አይደለም ከፈረንሳዩ ሃብታም ክለብ ፒኤስጂ እንኳ በአመት ወደ 85 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ወደ ካዝናው ያስገባል።

Via - daily mail
4.7K views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 13:52:09
የድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አልበም የፊታችን አርብ እንደሚወጣ ተነገረ።

በሀገራችን የሙዚቃው ኢንዱስትሪ ውስጥ ስራዎቹን ለሙዚቃ አፍቃሪያን በማድረስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደማጭና ታዋቂ ለመሆን የቻለው የበርካታ ግጥምና ዜማ ደራሲ የሆነው ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አበበ 2ተኛ የሙዚቃ አልበም ይዞ መቷል።

"ማለፊያ" የሚል መጠሪያ ያለው ይህ የሙዚቃ አልበም ከአራት አመት በላይ የፈጀ ሲሆን ድምፃዊ ሱራፌል አበበ እና ሌሎች  በኢንዱስትሪው ውስጥ ስመ ጥር የሆኑ ባለሙያዎች  በግጥም በዜማ እንዲሁም በቅንብር አሻራቸውን ያሳረፉበት በርካታ ዝግጅት ሲደረግበት የነበረ ስለመሆኑም በመግለጫው ተገልጿል።

በኤላ ሪከርድስ አማካኝነት ሀምሌ 14  ለአድማጭ ይደርሳል።በሁሉም ዲጂታል ኘላት ፎርም ይገኛል 12 ያክል ትራክ ያለው ሲሆን  አንዳንድ በምስል የተሰሩም እንዳሉ ተመላክቷል።

Via - fastmereja
4.5K views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 13:26:06
ትላንት የወጡ የቶምቦላና መደበኛ ሎተሪዎች ማውጫዎች

ትላንት ሰኔ 29 ቀን 2015 ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አራት ሚሊዮን ያደገው አድማስ ዲጅታል ሎተሪና ሃያ ሚሊዮን ብር አሸናፊ የሚያደርገው ቶምቦላ ሎተሪ በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ ወጥተዋል።

Via - Beherawe_lotery
4.4K viewsedited  10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 12:05:23
ሂጅራ ባንክ የተቀማጭ ገንዘቡን 5 ቢሊዮን ብር ማድረሱን አስታወቀ፡፡

ባንኩ ሥራ በጀመረ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተቀማጭ ገንዘቡን 5 ቢሊዮን ብር ማድረሱን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። በተሰጠው መግለጫ የባንኩ የጥቅል ትርፍ መጠን 162  በመቶ ማሳደጉ ተገልጿል።

የደንበኞቹን ብዛትም 1 በመቶ 73 በመቶ ማሳደጉን የገለጸው ባንኩ የቅርንጫፎቹ  ብዛት  80 በመቶ እንደደጉም ተነስቷል። የባንኩ አጠቃላይ ሀብትም 7.1 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገልጿል።

ሸሪዓውን መሠረት ያደረገ ከወለድ ነፃ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝና በቀጣይም ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።

ምንጭ - ኢትዮ ኤፍ ኤም
4.7K views09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ