Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-07-05 06:43:03
በሬሜዲያ ፈተና ሂደት ወቅት ባጋጠሙ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔዎች አሳልፏል።

የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ረሜዲያል ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ሰኔ 26/2015 ዓ.ም በዩኒቨርስቲዎች መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በፈተና ሂደት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።

1) ሰኔ 26/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ።

2) ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊት በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም እንዲሰጥ።

3) በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች በተያዘው ፕሮግራም መሰረት ይሰጣል።

NB. ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ይፋ ባደረገው መረጃ ትላንት ፈተናውን መሰጠት ከጀመረ በኃላ አጋጥመዋል ያላቸውን ችግሮችን በዝርዝር ይፋ አላደረገም።

@News_For_Student
@News_For_Student
9.9K views03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 21:37:03 " ውሳኔው ተገቢነት የሌለው ነው ፤ ፈተናው ከተቻለ አሁን ካልሆነ በቅርብ ቀናት ውስጥ ሊሰጥ ይገባል " - ተማሪዎች / የተማሪ ወላጆች

የሬሜዲያል መርሀግብር ሲከታተሉ ቆይተው ፈተናው ወደ መስከረም 2016 ዓ/ም የተሸጋገረባቸው ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳሳደረባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ እና ወላጆቻቸው ለወራት ያህል ገንዘባቸውን እየከፈሉ ትምህርቱን ከተከታተሉና የመጀመሪያ ቀን ፈተና ከወሰዱ በኃላ ሚኒስቴሩ ፈተናው ወደ መስከረም ወር መራዘሙን ማሳወቁ ፍፁም ተገቢ አይደለም በማለት ተቃውመዋል።

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልል ከተሞች የሚገኙ ተማሪዎች ውሳኔ እንዲቀለበስ የሚመለከታቸውን አካላት ተሰባስበው ለመጠየቅ ጥረት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ለአብነት በአዲስ አበባ 4 ኪሎ፤ ትምህርት ሚኒስቴር አካባቢ ጥያቄ አለን ያሉ ተማሪዎች ተሰባስበው ጥያቄያቸውን ለማቅረብ ጥረት አድርገዋል፤ ከጅማ እንዲሁም ከሀዋሳ የግል ተፈኞች ጥያቄያቸውን ተሰባስበው ለማሳመት እንደጣሩ ለመረዳት ችለናል።

ውሳኔውን ቅሬታ አሳድሮብናል ያሉት የሬሜዲያል የግል ተፈታኝ ተማሪዎች፤ " ብዙ መሰዋትነት ከፍለን ነው የተማርነው ፤ ከቤተሰብ ተለይተን የቤት ክራይ እየከፈልን የት/ት ወርሀዊ ክፍያ እየከፈልን የተማርንም አለን፤ ቤተሰብም እኛን ለማስተማር ሲል ከፍተኛ ዋጋ ከፍሏል ፤ ይህን ሁሉ ተቋቁመን ለ4 ወር ያክል ቆይተን አሁን ፈተናውን እኛ የግል ት/ት ቤት ተማሪዎች ብቻ አትፈተኑም መባላችን ትክክል አይደለም፤ ይህ ውሳኔ ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና ያደርስብናል " ሲሉ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ የተማሪ ወላጆች ውሳኔው ልጆቻቸው ብዙ የደከሙበትን ጥረት ወደኃላ የሚመልስ መሆኑን በመግለፅ፤ በጥናታቸው ላይ የሚያሳድረውን ስነልቦናዊ ጫና በመገንዘብ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔውን በማጠፍ ልጆቻቸው ፈተናቸውን ልክ እንደ ሌሎች ተማሪዎች በተመሳሳይ ጊዜ እና ወቅት እንዲወስዱ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ፈተናውን አሁን ካልተቻለም ደግሞ የተማሪዎች ለፈተናው ያደረጉት ዝግጅት ብዙ ሳይጠፋባቸው በአጭር ቀናት ውስጥ እንዲሆን ተማሪዎቹ እና ወላጆቻቸው ጠይቀዋል።

ተማሪዎቹም ሆኑ ወላጆቻቸው በአሰራር ጉድለት እና በተፈጠረው ችግር ይህ ውሳኔ መተላለፉ በተማሪዎች ህይወት፣ ጊዜ እና እድሜ ላይ ጫና እንዳለው አስረድተዋል። ለዚህ የአሰራር ጉድለት ተወቃሹ ሚኒስቴሩ ሆኖ ሳለ ይህን መሰሉ ውሳኔ ተላልፎ በተማሪዎች ላይ ለሚደርሰው ጫና ማነው ተጠያቂው ? ሲሉም ጠይቀዋል።

በተወሰነው ውሳኔ " የተማሪዎች ሞራል ሊጎዳ አይገባም " ያሉ አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ደግሞ ፤ ተፈጠረ የተባለው ችግር የት እና በማን ተፈጠረ የሚለውን ተጣርቶ ውሳኔ ሊተላለፍ ይገባ ነበር የጅምላ ውሳኔ ተገቢ አይደለም ብለዋል።

" ከጅምሩ እንዲህ ያለ ስጋት ካለ ሁሉም የግል ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪ በመንግስት ዩኒቨርሲቲ ገብቶ እንዲፈተኑ ማድረግ ይቻል ነበር፤ ከዚህ አለፍ ሲልም ሚኒስቴሩ Plan B ሊኖረው ይገባ ነበር " ሲሉ ውሳኔውን ተቃውመዋል። ፈተና በተቻለ ፍጥነት በአጭር ጊዜ ቢሰጥ ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር፤ ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ  ወደ ፊት  በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም  እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል።

@News_For_Student
@News_For_Student
10.1K views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 20:42:48
ለሁለት ቀናት በክልል አቀፍ እና ከተማ አቀፍ ደረጃ ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ ተጠናቋል። 

ፎቶ ፦ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

@News_For_Student
@News_For_Student
9.3K views17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 12:08:14
ትላንት ሰኔ 26/2015 ዓ.ም የተሰጡ የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች እንዲሰረዙ እና ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ የትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

ሚኒስቴሩ የሬሜዲያል ፈተና አሰጣጥን በተመለከተ ትናንት ምሽት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶችና ኃላፊዎች ጋር ያደረገውን ውይይት ተከትሎ ነው ውሳኔውን ያሳለፈው፡፡

ከዚህ ቀደም በሁሉም የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት ተይዞ የነበረው እቅድ ላይም ማሻሻያ ተደርጓል፡፡

በዚህም በተለይ ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደፊት በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም 2016 ዓ.ም እንዲሰጥ ሚኒስቴሩ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በመንግሥት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ ተማሪዎችን በተመለከተ፤ ፈተናውን ወደ መስከረም ወር ማስተላለፉ በተማሪዎችና በተቋማት ላይ የሚያሳድረው ጫና ከፍተኛ እንደሚሆን ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል፡፡

በመሆኑም ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተዘጋጁትን ፈተናዎች በመለወጥ፣ ፈተናዎች ኢንክሪፕትድ ሆነው ለዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ደርሰው እንዲባዙ እና ሁሉም ፈተናዎች በተመሳሳይ ሰዓት ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ እንዲሰጡ ተወስኗል፡፡

ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ በሚሰጡት በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ የሚመዘኑ መሆኑን ሰምተናል፡፡

የፈተና ጥያቄዎች ለዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ከመድሳቸው በፊት ተማሪዎች ከቀኑ 6፡00 ላይ ተፈትሸው ወደ መፈተኛ አዳራሽ ገብተው፣ ፈተናውን እንዲጠባበቁ በማድረግ ሊፈጸሙ እንደሚገባ ሚኒስቴሩ ማሳሰቡን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው መረጃ ያስረዳል።

@News_For_Student
@News_For_Student
11.1K views09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 07:02:37
የጤና ሚኒስቴር ለጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና የፊታችን አርብ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል።

የብቃት ምዘና ፈተናው ትምህርት ሚኒስቴር ከሚሰጠው የመውጫ ፈተና ጋር በማቀናጀት እንደሚሰጥ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

ፈተናው የፊታችን አርብ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ ያረጋገጠው ሚኒስቴሩ፤ ፈተናው በኮምፒውተር እንደሚሰጥ ጠቁሟል።

እያንዳንዱ ተፈታኝ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት የቅድመ ፈተና መለማመጃ መውሰድ ይጠበቅበታል።

በፈተናው ዕለት (ሰኔ 30/2015 ዓ.ም) ተፈታኞች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡

ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች ወደ ፈተና ክፍል ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡

ፈተናውን በድጋሜ የምትወስዱ ተመዛኞች ወደ ፈተና ጣቢያ ስትሄዱ የፈተና መለያ ቁጥር QR Code የያዘ ስሊፕ Print አድርጋችሁ መያዝ ይኖርባችኋል።

@News_For_Student
@News_For_Student
10.9K views04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 11:23:48
የሪሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ዛሬ መሰጠት ይጀምራል፡፡

በ2014 ዓ.ም የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የነበሩና በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማጠናከሪያ ትምህርት ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች የሪሚዲያል ፈተና ከዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን ለሚሰጡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የላከው የጊዜ ሰሌዳ እንደሚያሳየው ፈተናው ዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 መሰጠት ይጀምራል፡፡

የፈተና የፍተሻና የክፍል ቅድመ ዝግጅት በየዕለቱ ከቀኑ 8:00 የሚጀምር ሲሆን ፈተናው ደግሞ ከቀኑ 9:00 መሰጠት ይጀምራል። (የፈተናው መርሃ ግብር ከላይ ተያይዟል፡፡)

ተፈታኝ ተማሪዎች ለፍተሻ እና የክፍል ቅድመ ዝግጅት ሥራ 8:00 ላይ በመፈተኛ ክፍላቸው  በር ላይ እንዲገኙ ተብሏል፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
12.5K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 08:11:43
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻያ አገር አቀፍ ህዝባዊ ንቅናቄ በይፋ ተጀምሯል።

በንቅናቄው በመላ ኢትዮጵያ ያሉ ከ50 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እንደሚሰራ የትምህርት ሚኒስቴር መግለጹ ይታወቃል፡፡

በንቅናቄው የኀብረተሰቡን ዕውቀት፣ ሃብት እና ጉልበት በማሰባሰብ ትምህርት ቤቶችን ደረጃቸውን የጠበቁ ለማድረግ ይሰራል ተብሏል።

@News_For_Student
@News_For_Student
11.5K views05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 19:15:25
#Reminder

የስምንተኛ ክፍል ፈተና ለሁለት ቀናት ሰኔ 26 እና 27/2015 ዓ.ም በመላ አገሪቱ በከተማ እና በክልል ደረጃ ይሰጣል።

ፈተናዎቹ ሙሉ ቀን (ጠዋት እና ከሰዓት) እንደሚሰጡ ተገልጿል።

ተፈታኞች እርሳስ፣ ላጲስ እና ማስመሪያ ብቻ ወደ ፈተና ማዕከላት ይዘው መሔድ እንደሚችሉ ተመላክቷል።

ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ታብሌት፣ ጆሮ ማዳመጫ፣ ዲጂታል ሰዓት እንዲሁም ማንኛውንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን ይዞ በፈተና ማዕከላት መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
12.1K viewsedited  16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 10:35:01
በኦሮሚያ ክልል ከ484 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና ይሰጣል።

በኦሮሚያ ክልል 484,994 የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ቡልቶሳ ሂርኮ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ከነገ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚሰጠውን የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የተሳካ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን ኃላፊው ገልጸዋል።

ፈተናው በ1,441 የፈተና ጣቢያዎች ውስጥ ይሰጣል።

@News_For_Student
@News_For_Student
12.0K views07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 08:16:29
#ይመልከቱ #ይለማመዱ #ይዘጋጁ

የመውጫ ፈተና ኦንላይን አገባብ፣ አጠቃቀም እና አፈታተኑን የሚያሳይ አጋዥ ቪዲዮ

3.2 MB

@News_For_Student
@News_For_Student
11.6K views05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ