Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-08-24 08:39:44
#Update

" ፈተናው ተራዝሟል ፤ ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እናሳውቃለን " - ትምህርት ሚኒስቴር

ከዚህ ቀደም ፈተናቸውን ያልወሠዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ተራዝሟል።

ፈተናው ከነሐሴ 23 እስከ 26/2015 ዓ.ም በኦንላይን ይሰጣል ተብሎ እንደነበር አይዘነጋም።

ይሁን እንጂ በኢንተርኔትና ተዛማጅ ምክንያቶች ፈተናው መራዘሙን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል።

ሚኒስቴሩ ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

@News_For_Student
@News_For_Student
15.8K views05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-23 07:27:15
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚቀበለው በምደባ ሳይሆን በውድድር ብቻ እንደሚሆን አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ክፍያ የሚፈጽሙ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን “በልዩ” ሁኔታ ለማስተማር እንዳቀደም ገልጿል።

ተቋሙ ይህን ያለው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን አስመልክቶ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዛሬ ነሐሴ 16/2015 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ተቋሙ ራስ ገዝ ለመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን መግለጫውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው ወደ ራስ ገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር “ሁለት ዓመት ባልሞላ” ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱን ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ መሆኑን ተከትሎ የሥራ ነፃነትን የሚያጎናጽፉ የሕግ ማሻሻያዎች እያደረገ እንደሚገኝ መግለጡ ይታወሳል፡፡ (ተጨማሪ ይኖረናል)

@News_For_Student
@News_For_Student
15.8K views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-21 08:04:52
#ቴክኖሎጂ

ምንም አይነት ኬሚካልም ሆነ ኤሌክትሪክ ሳይጠቀም ውሃን የሚያጣራ ቴክኖሎጂ ለዕይታ ቀረበ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባዘጋጀው ኤግዚቢሽን ለዕይታ የቀረበው ቴክኖሎጂ፤ በአለም ጤና ድርጅት የሦስት ኮከብ ደረጃ ያገኘ መሆኑ ተገልጿል።

ለአያያዝና ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ መንገድ መዘጋጀቱ የተገለጸው ቴክኖሎጂው፤ በተለያየ መጠንና አይነት መቅረቡ ተገልጿል።

በሀፍ አስመጪና እቃ አቅራቢ ንግድ ሥራ አማካኝነት የተዘጋጀው ቴክኖሎጂ በቅርቡ በአዲስ አበባ መቅረብ ይጀምራል ተብሏል። #MoWE

@News_For_Student
@News_For_Student
15.0K views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-20 08:21:46
በአፋር ክልል የ123 ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እየተሠራ ነው።

በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ንቅናቄ ከሐምሌ 05/2015 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሔደ እንደሚገኝ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አብዱ ሐሰን ገልጸዋል።

ንቅናቄው በክልሉ በወረዳ ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል ያሉት ኃላፊው፤ አርብቶ አደሩ በገንዘብ መዋጮ፣ በጉልበቱ እንዲሁም የእንስሳት መዋጮ በማድረግ እየደገፈ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል።

ዓለም አቀፉ የህጻናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉንም ጠቅሰዋል።

መርሃ ግብሩ ለአምስት ዓመት የሚቀጥል ሲሆን በዘንድሮው ዓመት ብቻ 123 ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ታቅዷል ብለዋል።

@News_For_Student
@News_For_Student
15.3K views05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-19 09:47:45
#SalaleUniversity

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የሬሚዲያል ተማሪዎችን ውጤት ይፋ አድርጓል።

በዩኒቨርሲቲው የአቅም ማሻሻያ (ሬሚዲያል) ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የቆያችሁ ተማሪዎች ውጤታችሁንን በተቋሙ ድረ-ገጽ ላይ በመግባት ማየት ትችላላችሁ፡፡

ውጤት ለማየት፦
www.slu.edu.et/remedial/index.php

Note: የዩኒቨርሲቲ መታወቂያ ቁጥር እና ሙሉ ስም ማስገባት እንዳትዘነጉ

@News_For_Student
@News_For_Student
15.1K views06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-18 15:15:18
#ማስታወሻ

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሬሜዲያል ፈተና ከነሐሴ 23 እስከ 26/2015 ዓ.ም እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ ይታወቃል።

ፈተናው በሁለት የመንግሥት እና በ143 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማካካሻ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

ያስታውሱ፡-

• ፈተናው በበይነ መረብ ይሰጣል
• የፊዚክስ እና የታሪክ ኮርሶች በሪሜዲያል ፈተና ውስጥ አይካተቱም

@News_For_Student
@News_For_Student
15.1K views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-17 21:12:49
የሬሚዲያል ትምህርታቸውን በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የተከታተሉ የአቅም ማሻሻያ (የሬሚዲያል) ተማሪዎች ከውጤት መዘግየት ጋር የተያየዘ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አድርሰዋል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና የውጭ ግንኑነት ዳይሬክቶሬትን ጠይቀናል፡፡

ከ12ኛ ክፍል የመለልቀቂያ ፈተና ጋር በተያያዘ የሬሚዲያል ተማሪዎች ውጤት መገለፅ ከነበረበት ጊዜ የተወሰነ መዘግየት ማጋጠሙን ዳይሬክቶሬቱ ገልጿል፡፡

አሁን ላይ የሬሚዲያል ተማሪዎች ውጤት የማደራጀት ሥራ በመጠናቀቁ በቀጣይ ሁለት ቀናት ውስጥ ይፋ ይደረጋል ተብሏል፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
14.6K views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-15 20:08:09
#DambiDolloUniversity

ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሬሚዲያል ተማሪዎችን ውጤት ይፋ አድርጓል።

በዩኒቨርሲቲው የአቅም ማሻሻያ (ሬሚዲያል) ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የቆያችሁ ተማሪዎች ውጤታችሁንን በተቋሙ የቴሌግራም ገጽ ላይ በመግባት ማየት ትችላላችሁ፡፡

ውጤት ለማየት፦
https://t.me/DaDUempower

@News_For_Student
@News_For_Student
13.3K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-15 17:26:18
#MoE

በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የፕሮግራሞች አከፋፈት  የዩኒቨርስቲዎችን የትኩረትና ተልእኮ ልየታ የተከተለ እንዲሆን አቅጣጫ ተሰጠ::

በ2016 የትምህርት ዘመን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የፕሮግራሞች አከፋፈት  የዩኒቨርስቲዎችን የትኩረትና ተልእኮ ልየታ የተከተለ እንዲሆን  በትምህርት ሚኒስቴር ነሃሴ 09/2015ዓ. ም በተጻፈ ደብዳቤ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

እስካሁን  በመሰጠት ላይ ያሉ የቅድመና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በ2016 ዓ.ም በዝርዝር ተፈትሸውና  ተገምግመው  ከዩኒቨርስቲዎች ልየታ ጋር መጣጣማቸውን የማረጋገጥ ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በጻፉት ደብዳቤ የታቀዱ አዳዲስ ፕሮግራሞች ለመክፈት የሚደረጉ ጥናቶች ባሉበት እንዲቆዩ፣ መጪው የትምህርት ዘመን የመንግስት  ዩኒቨርስቲዎች በአዳዲስ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እንዳይቀበሉ እንዲሁም  በቦርድ በጸደቁና በትምህርት ሚኒስቴር በተመዘገቡ አዳዲስ ፕሮግራሞችም ዩኒቨርስቲዎች ተማሪ መቀበል እንዳይጀምሩ አሳስበዋል።

አዳዲስ የትምህርት ፕሮግራሞች ባሉበት እንዲቆዩ የተወሰነው የትምህርት ፕሮግራሞች ተገምግመው ከዩኒቨርስቲዎች ተልዕኮና ትኩረት ጋር መጣጣማቸው  እስኪረጋገጥ ድረስ አዳዲስ ፕሮግራሞችን የመክፈት ስራ መግታት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል።

(ደብዳቤውን ከላይ  ተያይዟል)

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@News_For_Student
@News_For_Student
12.9K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-14 10:50:48
ጅማ ዩኒቨርሲቲ የሬሚዲያል ተማሪዎችን ውጤት ይፋ አድርጓል።

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (ሬሚዲያል) ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የቆያችሁ ተማሪዎች ውጤታችሁን በተቋሙ ድረ-ገጽ ላይ በመግባት ማየት ትችላላችሁ፡፡

ውጤት ለመመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦ https://portal.ju.edu.et/

@News_For_Student
@News_For_Student
13.8K views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ