Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚቀበለው በምደባ ሳይሆን | ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚቀበለው በምደባ ሳይሆን በውድድር ብቻ እንደሚሆን አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ክፍያ የሚፈጽሙ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን “በልዩ” ሁኔታ ለማስተማር እንዳቀደም ገልጿል።

ተቋሙ ይህን ያለው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን አስመልክቶ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዛሬ ነሐሴ 16/2015 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ተቋሙ ራስ ገዝ ለመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን መግለጫውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው ወደ ራስ ገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር “ሁለት ዓመት ባልሞላ” ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱን ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ መሆኑን ተከትሎ የሥራ ነፃነትን የሚያጎናጽፉ የሕግ ማሻሻያዎች እያደረገ እንደሚገኝ መግለጡ ይታወሳል፡፡ (ተጨማሪ ይኖረናል)

@News_For_Student
@News_For_Student