Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-09-18 08:07:45
#AddisAbaba

ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ስራ በይፋ ይጀምራል።

ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ባገኘነው መረጃ ከዛሬ ጀምሮ በከተማው ውስጥ በሚገኙት ሁሉም የትምህርት ተቋማት የ2016 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ስራ የሚጀምር ይሆናል።

ዛሬ ለሚጀምረው ትምህርት በየክፍለ ከተሞቹ የሚገኙት የትምህርት ፅህፈት ቤቶች እንዲሁም የትምህርት ተቋማት በቂ የሆነ ዝግጅት አድርገው የተማሪዎችን ለዓመቱ ትምህርት መገኘት ብቻ እየጠበቁ ይገኛሉ ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ፤ ለ2016 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ዝግጅት በከተማው ያሉ ትምህርት ቤቶችን የማደስ፣ ግብዓቶችን የማሟላት ፣ ከአጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰቡ ጋር የመምከር ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።

በዛሬዉ ዕለት በከተማዋ ትምህርት የሚጀምረው #በሁሉም የትምህርት ተቋማት ውስጥ ነው።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.4K views05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-16 14:07:11
#Grade8

የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል  ክልል አቀፍ የፈተና ውጤትን በቀን 04/01/2016 ዓ.ም ይፋ አድርጓል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ማየት ይችላሉ ተብሏል።

#ማስታወሻ ፦ በቅድሚያ ቪፒኤን ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡

ሲስተሙን ለመጠቀም:- URL ለይ
1) ይህን ሊንክ  https://sidama.ministry.et  ይጫኑ
2) ፊት ለፊት በሚታየው  ቅጽ(form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር ያስገቡ
4) " ዉጤት ይመልከቱ " የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
15.5K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-16 14:04:31
የአጠቃላይ ትምህርት የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደር

ማሳሰቢያ :- ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ታሳቢ ይደረግ

@News_For_Student
@News_For_Student
14.8K views11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-16 07:23:03
በ2016 ዓ.ም. መደበኛ የመማር ማስተማር ስራዉ ከመጪው ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ይጀምራል!

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከመስከረም 7 ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማር ስራዉ እንደሚጀመር አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ "የጋራ መግባባት ለዉጤታማ መማር ማስተማር"  በሚል መሪ ቃል የ2016 ትምህርት ዘመን አጀማመርን በሚመለከት በከተማዋ ከሚገኙ ከሁሉም ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን ጋራ ዉይይት እያካሄደ ይገኛል።

@News_For_Student
@News_For_Student
14.2K views04:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-14 07:46:42
#MoE

ዲጂታል የተማሪዎች መታወቂያ ስርዓት ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የዲጂታል መታወቂያ ስርዓትን በትምህርት ተቋማት መደበኛ የተማሪዎች መለያ አድርጎ መተግበር ጀምሯል።

የተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ የተማሪዎችን ማንነት በወጥነት ለመለየት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ስርዓቱ ከትምህርት ቤቶች እስከ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ የትምህርት ተቋማት የተማሪ ቅበላ፣ ፈተናና የማህደር አስተዳደር የመሳሰሉ ሥራዎችን ለማሳለጥ ያግዛል ተብሏል።

እስካአሁን 640 ሺህ ተማሪዎች ብሔራዊ መለያ ቁጥር ማግኘታቸውን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርአያሥላሴ ተናግረዋል። በ2016 የትምህርት ዘመን ስርዓቱን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሠራ ገልፀዋል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.3K views04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-13 16:53:28
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት መቼ ይገለጻል?

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤትን ቶሎ ለማድረስ በሙሉ አቅም እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል፡፡

ፈተናውን የማረም ሥራ በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ማንጠግቦሽ አዳምጤ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

ከመስከረም 07 እስከ 11/2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን ጨምሮ ውጤት ለመግለፅ መታሰቡን ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡

"ምናልባትም እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ውጤቱ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል" ተናግረዋል፡፡

በነሐሴ መጨረሻ በሰጡት መግለጫr የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም አጋማሽ ድረስ ይፋ ይደረጋል ብለው እንደነበር አይዘነጋም።

በትግራይ ክልል በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ለነበሩ ተማሪዎች ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ.ም የመልቀቂያ ፈተናው ይሰጣል መባሉ ይታወቃል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.7K views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-12 06:29:16
የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ከመስከረም 21 እስከ 23/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

ፈተናው በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ተፈታኞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው Graduate Admission Testing (GAT) የመመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et ከመስከረም 11 እስከ 20/2016 ዓ.ም ድረስ በኦንላይን ማመልከት እንደሚገባቸው ሚኒስቴሩ ዛሬ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡

በየትኛውም የመፈተኛ ማዕከላት ፈተናውን ለመውሰድ ተፈታኞች ፎቷቸው ያለበት Test Admission Ticket (TAT) ይዘው መገኘት እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

የመግቢያ ፈተናውን ትምህርት ሚኒስቴር እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋራ የሚያስተዳድሩት ሲሆን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሚሰጥ ነው፡፡

የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና የማለፊያ ነጥብ በትምህርት ሚኒስቴር የሚወሰን መሆኑም ተመላክቷል።

(በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሜጄና (ዶ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@News_For_Student @News_For_Student
14.8K views03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-10 07:09:04
የ 2015 የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት እስከ መስከረም 15 ድረስ ይፋ ይሆናል መባሉ ይታወሳል።

ተማሪዎች ውጤታችሁን በትዕግስት እንድትጠብቁ  እና Share እና Follow በማድረግ እንድትከታተሉን እያሳሰብን ውጤት ሲለቀቅ  በዚሁ @News_For_Student ቻነል በፍጥነት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

@News_For_Student
@News_For_Student
14.5K views04:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-09 12:02:53
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ የማካካሻ (ሬሜዲያል) ትምህርት ተከታታዮች ፈተና የሚሰጥበትን አቅጣጫ አስቀምጧል።

(ከላይ ያንብቡ)

@News_For_Student
@News_For_Student
13.3K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-09 07:15:22
ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016  የማካካሻ (Remedial) ትምህርት ፈተና እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
 
ትምህርት ሚኒስቴር የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፈተና ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016 እንደሚሰጥ ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

ፈተናው በ30 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚከናወን ይሆናል።

የሚሰጠው ፈተና የማካካሻ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም የተሰጠውን የማዕከል ፈተና ላልወሰዱ  ተማሪዎች መሆኑ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ ከመስከረም 7- 10/2016 ዓ.ም ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና #በወረቀት የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከ50 % በታች ሆኖ ወደከፍተኛ ትምህርት መግባት ያልቻሉ እና በአንጻራዊነት የተሻለ ውጤት የነበራቸው ወደ 200ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአንድ ሴሚስተር የማካካሻ ትምህርት መውሰዳቸው ይታወቃል።

የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፈተና የሚሰጠው ተማሪዎቹ በተቋማት እና በማዕከል የሚሰጠውን ምዘና ወስደው በሚያስመዘግቡት ውጤት መሠረት ከ2016 ዓ.ም ፍሬሽማን ተማሪዎች ጋር የከፍተኛ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ነው።

@News_For_Student
@News_For_Student
12.8K views04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ