Get Mystery Box with random crypto!

#AddisAbaba ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ዘመኑ የመ | ትምህርት ሚኒስቴር

#AddisAbaba

ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ስራ በይፋ ይጀምራል።

ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ባገኘነው መረጃ ከዛሬ ጀምሮ በከተማው ውስጥ በሚገኙት ሁሉም የትምህርት ተቋማት የ2016 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ስራ የሚጀምር ይሆናል።

ዛሬ ለሚጀምረው ትምህርት በየክፍለ ከተሞቹ የሚገኙት የትምህርት ፅህፈት ቤቶች እንዲሁም የትምህርት ተቋማት በቂ የሆነ ዝግጅት አድርገው የተማሪዎችን ለዓመቱ ትምህርት መገኘት ብቻ እየጠበቁ ይገኛሉ ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ፤ ለ2016 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ዝግጅት በከተማው ያሉ ትምህርት ቤቶችን የማደስ፣ ግብዓቶችን የማሟላት ፣ ከአጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰቡ ጋር የመምከር ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።

በዛሬዉ ዕለት በከተማዋ ትምህርት የሚጀምረው #በሁሉም የትምህርት ተቋማት ውስጥ ነው።

@News_For_Student
@News_For_Student