Get Mystery Box with random crypto!

የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ከመስከረም 21 እስከ 23/2016 ዓ.ም ይሰጣል። ፈተናው | ትምህርት ሚኒስቴር

የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ከመስከረም 21 እስከ 23/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

ፈተናው በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ተፈታኞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው Graduate Admission Testing (GAT) የመመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et ከመስከረም 11 እስከ 20/2016 ዓ.ም ድረስ በኦንላይን ማመልከት እንደሚገባቸው ሚኒስቴሩ ዛሬ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡

በየትኛውም የመፈተኛ ማዕከላት ፈተናውን ለመውሰድ ተፈታኞች ፎቷቸው ያለበት Test Admission Ticket (TAT) ይዘው መገኘት እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

የመግቢያ ፈተናውን ትምህርት ሚኒስቴር እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋራ የሚያስተዳድሩት ሲሆን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሚሰጥ ነው፡፡

የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና የማለፊያ ነጥብ በትምህርት ሚኒስቴር የሚወሰን መሆኑም ተመላክቷል።

(በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሜጄና (ዶ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@News_For_Student @News_For_Student