Get Mystery Box with random crypto!

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት መቼ ይገለጻል? የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤትን ቶሎ ለ | ትምህርት ሚኒስቴር

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት መቼ ይገለጻል?

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤትን ቶሎ ለማድረስ በሙሉ አቅም እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል፡፡

ፈተናውን የማረም ሥራ በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ማንጠግቦሽ አዳምጤ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

ከመስከረም 07 እስከ 11/2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን ጨምሮ ውጤት ለመግለፅ መታሰቡን ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡

"ምናልባትም እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ውጤቱ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል" ተናግረዋል፡፡

በነሐሴ መጨረሻ በሰጡት መግለጫr የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) የ12ኛ ክፍል ውጤት እስከ መስከረም አጋማሽ ድረስ ይፋ ይደረጋል ብለው እንደነበር አይዘነጋም።

በትግራይ ክልል በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ለነበሩ ተማሪዎች ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ.ም የመልቀቂያ ፈተናው ይሰጣል መባሉ ይታወቃል።

@News_For_Student
@News_For_Student