Get Mystery Box with random crypto!

#MoE ዲጂታል የተማሪዎች መታወቂያ ስርዓት ተግባራዊ መሆን ጀምሯል። ትምህርት ሚኒስቴር ከብሔ | ትምህርት ሚኒስቴር

#MoE

ዲጂታል የተማሪዎች መታወቂያ ስርዓት ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የዲጂታል መታወቂያ ስርዓትን በትምህርት ተቋማት መደበኛ የተማሪዎች መለያ አድርጎ መተግበር ጀምሯል።

የተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ የተማሪዎችን ማንነት በወጥነት ለመለየት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ስርዓቱ ከትምህርት ቤቶች እስከ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ የትምህርት ተቋማት የተማሪ ቅበላ፣ ፈተናና የማህደር አስተዳደር የመሳሰሉ ሥራዎችን ለማሳለጥ ያግዛል ተብሏል።

እስካአሁን 640 ሺህ ተማሪዎች ብሔራዊ መለያ ቁጥር ማግኘታቸውን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርአያሥላሴ ተናግረዋል። በ2016 የትምህርት ዘመን ስርዓቱን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሠራ ገልፀዋል።

@News_For_Student
@News_For_Student