Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-10-10 06:49:44
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ውጤት ማየት ይጀምራል!

እውጤት እንዴት መመልከት ይቻላል?

በዌብ ሳይት ለማየት ፦

1. eaes.et ብለው ብሮውዘር ላይ ይጻፉ
2. በመቀጠልም በሚመጣው ገጽ ላይ የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) እና የመጀመሪያ ስም ይጻፉ
3. Check Result የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማግኘት ይችላሉ።

በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ፦

1. 6284 የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ብቻ ጽፎ አንዴ ብቻ በመላክ መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ።

በቴሌግራም ቦት ፦

1. @eaesbot ይፈልጉ

2. የሚመጡ አማራጮችን በመከተል የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ያስገቡ በመቀጠልም መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ፡፡

@News_for_Student
@News_for_Student
20.7K views03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-10 05:45:19
#Result

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ማክሰኞ በ29/01/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ ብሏል።

ተፈታኞች የሚከተሉትን 3 አማራጭ አድራሻዎችን #ብቻ በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ሲል ገልጿል።
    
በዌብ ሳይት፡- eaes.et
በአጭር የጽሁፍ መልዕክት፡- 6284
ቴሌግራም አድራሻ፡- @eaesbot

አገልግሎቱ ከላይ ከተገለጹት የውጤት መግለጫ አማራጮች ውጪ ሌላ የውጤት መግለጫ መንገዶች የሌሉ መሆኑን አሳውቋል።

ተማሪዎች በማመሳሰል " ውጤት እንገልጻለን " ከሚሉ ከማንኛውም አጭበርባሪዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል።

በተጨማሪ ተቋሙ ውጤት ለማሳየት ምንም ክፍያ የማይጠይቅ መሆኑን አስገንዝቧል።

እንዴት ውጤት ልመልከት ?

በዌብ ሳይት ለማየት ፦

1. eaes.et ብለው ብሮውዘር ላይ ይጻፉ
2. በመቀጠልም በሚመጣው ገጽ ላይ የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) እና የመጀመሪያ ስም ይጻፉ
3. Check Result የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማግኘት ይችላሉ።

በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ፦

1. 6284 የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ብቻ ጽፎ አንዴ ብቻ በመላክ መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ።

በቴሌግራም ቦት ፦

1. @eaesbot ይፈልጉ

2. የሚመጡ አማራጮችን በመከተል የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ያስገቡ በመቀጠልም መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ፡፡

@News_for_Student
@News_for_Student
20.5K views02:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 18:15:23
ውጤት እንዴት መመልከት ይቻላል ?

የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች መስከረም 29, 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/

በአጭር የጽሑፍ መልዕክት 6284

በቴሌግራም https://t.me/eaesbot

@News_For_Student
@News_For_Student
20.3K views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 14:00:12
ሚኒስትሩን ያስደናገጣቸው ቁጥር ?

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" ከዚህ ፈተና አንድ #ሊያስደነግጠን የሚገባ ነገር ከተፈተኑት ጠቅላላ ተማሪዎች ውስጥ 50 ከመቶ የሚሆኑት እና ከዛ በላይ 26 ከመቶ ነው ያገኙት።

ከ845 ሺህ ፤ 422,500 ሺህ ተማሪ ከ26 በታች ነው ያገኘው። እንደው ዝም ብሎ አንድ ተማሪ ፈተናውን በግምት ቢሞላ እንኳን ሊያገኘው የሚችለው ውጤት ነው።

ለዚህ ነው ከታች ጀምሮ በደንብ አጥርተን መስራት አለብን የምንለው። "

ስለ 2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ቁጥሮች ምን ይላሉ ?

- በ2015 የተፈተኑ ተማሪዎች ብዛት 845,099 ፤ 50 በመቶና በላይ ያመጡ 27,267 ተማሪዎች (3.2%) ብቻ ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ ፦
• ከተፈጥሮ ሳይንስ ያለፉ 19,017 ተማሪዎች
• ከማህበራዊ ሳይንስ ያለፉ 8,250 ተማሪዎች

- በማታ የተፈቱ 16,541 ያለፉ 12 ተማሪዎች ብቻ

- በግል የተፈተኑ 169,502 ያለፉ 498 ተማሪዎች ብቻ

- በመደበኛ የተፈተኑ 659,056 ያለፉ 26,757 ተማሪዎች ብቻ

- የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ት/ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች #አንድም_ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም / ምንም ተማሪ አላሳለፉም።

- በሀገሪቱ ካሉትና የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑት ትምህርት ቤቶች 42.8 በመቶ የሚሆኑት አንድም እንኳን ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።

- 27 ሺህ 267 ተማሪዎች በቀጥታ ፍሬሽ ማን ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ 160 ሺህ ገደማ ተማሪ በሬሜዲያል ይገባሉ።

@News_For_Student
@News_For_Student
19.7K viewsedited  11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 13:54:02
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገበው አማካይ ውጤት 28.65 ከመቶ ነው፡፡ አንድ ተማሪ በአማካኝ ከመቶ ያገኘው ውጤት ማለት ነው፡፡

ከፍተኛው ውጤት 30.99 ከመቶ በኬሚስትሪ ትምህርት ሲሆን ዝቅተኛው 25.62 በመቶ በማህበራዊ ሳይንስ ሒሳብትምህርት የተመዘገበ ነው፡፡

ሀገራዊ አማካይ ውጤቱ ከጾታ አንጻር ሲታይ የወንዶች አማካይ ውጤት 29.55 ከመቶ ሲሆን የሴቶች ደግሞ 27.64 ከመቶ ሆኗል።

@News_For_Student
@News_For_Student
17.1K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 13:14:05
ውጤት በምን ይታያል ?

" ነገ ጥዋት 12 ሰዓት ላይ በዌብሳይት እና በSMS ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ይቻላሉ። " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

@News_For_Student
@News_For_Student
17.5K views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 13:05:19
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ካነሷቸው ነጥቦች፦

በተፈጥሮ ሳይንስ መስክ 200 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት አምጥተዋል፡፡

በማህበራዊ ሳይንስ መስክ 15 ተማሪዎች ብቻ ከ500 በላይ ውጤት አምጥተዋል፡፡

በተፈጥሮ ሳይንስ ከፍተኛው ውጤት 649 ሲሆን በአዲስ አበባ የልደታ ክሩዝ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት፡፡

በማህበራዊ ሳይንስ ከፍተኛው ውጤት 533 ሲሆን የደብረ ማርቆስ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪ ነው፡፡

በከተማ ደረጃ አዲስ አበባ፣ ሀረሪ እና ድሬዳዋ የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩ ከተሞች ናቸው፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
15.8K viewsedited  10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 12:57:27
"አምስት ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸው ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ አሳልፈዋል፡፡"

"ሌሎች አምስት ትምህርት ቤቶች ድግሞ ካስፈተኗቸው ውስጥ 95 ከመቶ ተማሪዎቻቸውን አሳልፈዋል፡፡"

ከፍተኛ አፈጻጻም ያሳዩ አስር ትምህርት ቤቶች (በደረጃ)፦

1. አዲስ አለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት
2. ደሴ አዳሪ ትምህርት ቤት
3. ባህርዳር ስቴም ትምህርት ት
4. ሀይራንዚ አዳሪ ትምህርት ቤት (ስልጤ ዞን)
5. ልጅ ጎጎ አዳሪ ትምህርት ቤት (ሀድያ)
6. ኦዳ አዳሪ ትምህርት ቤት (አዳማ)
7. ኮተቤ ሼርድ ካምፓስ
8. የኔታ አካዳሚ
9. ወላይታሊቃ አዳሪ ትምህርት ቤት
10. ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት

@News_For_Student
@News_For_Student
16.0K views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 12:50:16
በአጠቃላይ በ2015 ዓ.ም ከተፈተኑ ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል፡፡

በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ ለፈተና ከተቀመጡ በድምሩ 845,677 ተማሪዎች 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡት 31, 224 ተማሪዎች ብቻ ናቸው፡፡

በዚህም 160 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎችን በሬሜዲያል ፕሮግራም ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚቀበሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ትህርት ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አለመቻላቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
15.8K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 12:38:38
ውጤቱ እንዴት ነው ?

ከፍተኛ ውጤት ተፈጥሮ ሳይንስ 649 ፤ የማህበራዊ ሳይንስ 533 ሆኖ ተመዝግቧል።

649 ያመጣችው የአዲስ አበባ ልደታ ክሩዝ ትምህርት ቤት ስትሆን 533 ያመጣው ከደ/ማርቆስ አዲስ አለማየሁ ትምህርት ቤት ነው።

በአጠቃላይ በ2015 ዓ/ም ከተፈተኑ ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡት።

@News_For_Student
@News_For_Student
15.0K views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ