Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-10-13 15:02:12
645 ውጤት ያስመዘገበችው ተማሪ ረቂቅ አሸናፊ

የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተናዋን በሀዋሳ ኮምቦኒ ትምህርት ቤት የወሰደችው ተማሪ ረቂቅ አሸናፊ 645 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች።

ተማሪ ረቂቅ ከመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷ ጀምራ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ታጠናቅቅ እንደነበር ትናገራለች። ለፊዝክስ ትምህርት ደግሞ የተለየ ፍቅር እንዳላት ገልጻለች።

ከዚህ በላይ ውጤት ጠብቃ እንደነበር የምትናገረው ተማሪ ረቂቅ፤ ሳትዘናጋ በማጥናቷ ስኬታማ መሆኗን ትናገራልች፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
16.1K views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-13 13:18:14
በትግራይ ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ተጠናቀቀ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል አገራዊ ፈተና በተረጋጋ እና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ተጠናቋል ሲል አሳውቋል።

የቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ ፤ዥ አገር አቀፍ ፈተናው በተያዘለት ዕቅድ እንዲጠናቀቅ ያደረጋችሁ ከፌደራል እስከ ትምህርት ቤቶች እና ዩንቨርሲቲዎች ያላችሁ ተቋሞች፣ የትምህርት ኣመራሮች እና መምህራን፤ ከፌደራል እስከ ወረዳ ያላችሁ የፀጥታ እና ደህንንት ተቋሞች እና ኣመራሮች፤ ከተለያዩ ኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲዎች የተውጣጣችሁ ፈታኞች የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን "  ብለዋል።

ሃላፊው " ፈተናው በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ  ተፈታኝ  ተማሪዎቻችን ከናንተ የሚጠበቀው ሁሉ ስለደረጋችሁ ለናንተም የላቀ ምስጋና ይገባቹሃል " ሲሉ አክለዋል። 

ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ/ም  ለአራት ተከታታይ ቀናት በትግራይ ክልል ሲሰጥ የቆየውን የ12 ክፍል አገራዊ ፈተና ከ9,000 በላይ ተማሪዎች መፈተናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያሳያል።

ብሔራዊ ፈተናው የተሰጠው በመቐላ፣ አዲግራት፣ አክሱምና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ነው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና ውጤቱን ባጠረ ጊዜ ለማሳወቅ እንደሚሰራ ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መስከረም 28 /2016 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የትግራይ ተፈታኞቹን ውጤት በአንድ ሳምንት ውስጥ ለማሳወቅ ይሰራል።

የሚያልፉ ተማሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ውጤታቸው ከተገለጸ ተማሪዎች ጋር አብረው ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ መግለፃቸው አይዘነጋም።

@News_For_Student
@News_For_Student
16.0K views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-13 06:52:39 የ12ኛ ክፍል ውጤት ቅሬታ ፎርም አሞላል ቅደም ተከተል እንዴት ነው?

በቅድሚያ ወደ http://eaes.et ግቡ

በመቀጠል እንደተለመደው ሬጂስትሬሽን ቁጥር እና ስማችሁን አስገቡ

ከዚያም ከውጤት ማሳያው ሥር በታች በኩል በአረንጓዴ ቀለም ላይ ያረፈ
submit your complain if any
የሚለውን ተጫኑ


በመቀጠል ከሚመጡት የቅሬታ አይነቶች ውስጥ እናንተ ቅሬታ ማቅረብ የገለጋችሁበትን አንዱን ምረጡ።

የስም ስህተት ፣ የተሳሳተ ፎቶ ግራፍ ፣ የተሳሳተ የትምህርት መስክ (ሶሻል/ናቹራል) ፣ የተሳሳተ ጾታ ፣ የተሳሳተ ውጤት ፣ የተሳሳተ የዕይታ ሁኔታ (ማየት የሚችል/ማየት የተሳነው) ምርጫ እና ሌላ የሚል ይሰጣችኋል።

ለምሳሌ፦

ውጤቱ ላይ ከሆነ ቅሬታ ማቅረብ የፈለጋችሁት  Result problem  የሚለውን ተጫኑ

ከዚያም ከእያንዳንዱ ትምህርት ውጤት ጎን  ቅሬታ መጻፊያ ያመጣላችኋል

ከዚያም ቅሬታ ማስገባት የፈለጋችሁበት የትምህርት አይነት ጋር በመሄድ ቅሬታችሁን መጻፍ እና ስትጨርሱ submit የሚለውን ተጫኑ።

ማስታወሻ

ቅሬታ የምታስገቡት በሥራ ሰአት ቢሆን ይመረጣል።
@News_for_Student
@News_for_Student
15.3K views03:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-11 21:57:43 የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት ወር ላይ እንዲሰጥ ከወዲሁ ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛል።

የአሁኑ ፈተና ድብልቅ / ሃይብሪድ መሆኑን ከቀናት በፊት መግለጫ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ድብልቅ ፈተና ማለት ግማሹ ኦንላይን (የኢንተርኔት ችግር የሌለባቸው አካባቢዎች) ፤ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከዚህ ቀደም ሲሰጥ በነበረበት አካሄድ በወረቀት ነው የሚሰጠው።

ይህ የፈተና አሰጣጥ አካሄድ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ ፣ በመንግሥት በጀት ፣ በትምህርት ቢሮዎች ላይ ጫናውን እንደሚቀንስ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ምንም እንኳን የመግዛት አቅም ባይኖረውም ለፈተናው የሚሆኑ #ታብሌቶችን ከመንግሥት ተቋማት ጋር በመነጋገር ለፈተናው ጊዜ በመውሰድ ፈተናውን በድብልቅ እንደሚሰጥ አመልክቷል።

የ2016 ዓ/ም ፈተና ድብልቅ በሆነ መንገድ እንዲሰጥ ከወዲሁ ዝግጅቶቹ እየተደረጉ ሲሆን የሶፍትዌር ስራው ከወዲሁ መጠናቀቁ ተገልጿል።

የዘንድሮውም ምዝገባ በኦንላይን ሲሆን፣ ተፈታኞች በአካል ተገኝተው ፎቶ እንዲነሱ ይደረጋል ፤ በዚህ ረገድ ቁጥጥሩ ጠበቅ እያለ ይሄዳል ተብሏል።

የተሻሉ የፈተና አዘጋጆች፣ ፈተናዎች እንዳይሰረቁ የሳይበር ጥበቃ፣ የደህንነት ካሜራዎች ፣ የተቋማት ትብብር (ኢንሳ፣ ፈተናዎች አገልግሎት) ፣ ጥንቃቄ የተሞላበት የፈተና ህትመት ዝግጅት ከዚህ ቀደሙም በተሻለ መልኩ ጠንካራ ስራ በጋራ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከወዲሁ እራሳቸውን ለመመዘኛ ፈተናው ብቁ እና ዝግጁ እያደረጉ መሄድ ያለባቸው ሲሆን መምህራን፣ ወላጆች፣ መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተማሪዎችን እያገዙ ለፈተናው እንዲዘጋጁ ማደርግ አለባቸው።

በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ገብተው ባለፉት ሁለት ብሄራዊ ፈተናዎች ማለትም በ2014 እና 2015 ከተፈተኑት አጠቃላይ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዛ በላይ አምጥተው ያለፉት እጅግ ጥቂት ናቸው።

በ2014 ፈተና 896,520 ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት 30,034 ወይም 3.3 በመቶ ብቻ ሲሆኑ በ2015 ፈተና 845,099 ተማሪዎች ተፈትነው ማለፍ የቻሉት 27,267 ወይም 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው።

@News_For_Student
@News_For_Student
16.9K views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-11 13:08:49
የ2015 ዓም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት 6284፣ በዌብሳይት eaes.et እንዲሁም በቴሌግራም ቦት @eaesbot የሬጅስትሬሽን ቁጥር በማስገባት ማየት እንደሚቻል መገለጹ ይታወቃል።

ውጤት የመመልከቻ አማራጮች ላይ ማለትም eaes.et ፣ eaes.gov.et ፣ eaes.edu.et ከገባችሁ በኋላ Forgot Admission Number የሚለውን በመጫን፣ Your Name, Father's Name, Grand Father's Name በሚሉት ላይ ስማችሁን እስከአያት ስትሞሉ ካለምንም ID ይሠራል።

ተማሪዎች በትዕግስት በመሞከር ውጤታቸውን እንዲያዩ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መክሯል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.1K views10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-11 08:02:37
#ሀናን_ናጂ_አህመድ

በኢትዮጵያ ደረጃ የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው የክሩዝ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ናት።

ተማሪ ሀናን ናጂ አህመድ በተፈጥሮ ሳይንስ 649 ውጤት በማስመዝገብ ከዘንድሮ ተፈታኞች በቀዳሚነት ተቀምጣለች፡፡

ተማሪ ሀናን ናጂ ባስመዘገበችው ውጤት በጣም ደስተኛ መሆኗን ገልጻለች።

በቀጣይም ለበለጠ ውጤት እንደመትተጋ ተናግራለች፡፡

የክሩዝ ሁተኛ ደረጃ ት/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኝ የግል ትምህርት ቤት ነው፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
14.2K views05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-10 20:10:41
በውጤትዎ ላይ ቅሬታ አለዎት?

በ2015 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተያ ውጤት ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተፈታኞች eaes.et ላይ እስከ ጥቅምት 05/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ድረስ ቅሬታችሁን በኦንላይን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አግልግሎት ገልጿል።

የ12ኛ ክፍል ውጤት ዛሬ ከሰአት ጀምሮ ተማሪዎች መመልከት እንደቻሉ ተሰተውሏል።

@News_For_Student
@News_For_Student
18.3K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-10 11:26:33
የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት

ውጤት በዌብሳይት eaes.et ላይ ፣ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት በ6284 ፣ በቴሌግራም ቦት @eaesbot ላይ " ሬጅስትሬሽን ቁጥር " በማስገባት ማየት እንደሚቻል ተገልጿል።

ነገር ግን በርካታ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ውጤት ለማየት መቸገራቸውን ጠቁመዋል።

" በአንድ ግዜ ተማሪዎችና ወላጆችን ጨምሮ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰው ውጤት ለማየት እየሞከረ ስለሆነ መጨናነቅ መፈጠሩን " ከፍተኛ የአገልግሎቱ አመራር ተናግረዋል፡፡

ውጤት ሙሉ በሙሉ ስላልተለቀቀ ተማሪዎች ውጤታችሁን በትዕግስት እንድትጠብቁ  እያሳሰብን ውጤት ሲለቀቅ  በዚሁ ቻነል በፍጥነት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

@News_For_Student
@News_For_Student
23.4K viewsedited  08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-10 08:27:11
የውጤት ማያ ዌብሳይቱ registration number እና school code ይጠይቅ ነበር አሁን ላይ ግን registration number እና name ሆኗል ፣ ሰርቨሩ በመስተካከል ላይ ነው።

ተማሪዎች ውጤታችሁን በትዕግስት እንድትጠብቁ  እያሳሰብን ውጤት ሲለቀቅ  በዚሁ ቻነል በፍጥነት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

@News_For_Student
@News_For_Student
22.9K views05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-10 08:14:59
ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ውጤት ከ1 ሰዓት ጀምሮ መመልከት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ያሳወቀ ቢሆን በተለያዩ ቦታዎች ተለቀቀ የሚባለው ከእውነት የራቀ ነው ።

የ2015 ፈተናን ከ800 ሺህ በላይ ተማሪዎች መፈተናቸው ይታወቃል።

ተማሪዎች ውጤታችሁን በትዕግስት እንድትጠብቁ  እያሳሰብን ውጤት ማያ ሊንክ ሲለቀቅ  በዚሁ ቻነል በፍጥነት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

@News_For_Student
@News_For_Student
21.3K views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ