Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-11-06 06:37:39
በአማራ ክልል ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተማሪዎቻቸውን እንደማይጠሩ ተገለፀ

በዐማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ምክንያት፣ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ መደበኛ ሥራቸው በቅርቡ እንደማይመለሱ፣ የክልል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም አስታውቋል፡፡

የፎረሙ ዋና ጸሐፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ በነበራቸው ቆይታ፣ በክልሉ የሚገኙ ዐሥሩም ዩኒቨርሲቲዎች፣ የክልሉ ጸጥታዊ ኹኔታ እስኪሻሻል ድረስ ተማሪዎቻቸውን እንደማይጠሩ፣ የጋራ መግባባት ላይ እንደደረሱ ገልጸዋል፡፡

ተለዋዋጭነት ባለው የክልሉ ጸጥታ ምክንያት መንገድ መዘጋቱ፣ ተማሪዎች ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ግጭት ቢነሣ ዩኒቨርሲቲዎቹ ሓላፊነት መውሰድ ስለማይችሉ፣ እንዲሁም ከምግብ ጀምሮ ለዩኒቨርሲቲዎች ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ያቀርቡ የነበሩ አካላት፣ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ማስታወቃቸው፣ ለፎረሙ ውሳኔ መሠረት እንደኾኑ ጸሐፊው አስረድተዋል፡፡

ይኹንና ያነጋገርናቸው ተማሪዎች፣ በአሁኑ ሰዓት ዩኒቨርሲቲዎቹ ቢጠሯቸው እንደሚገቡ ገልጸዋል፡፡ የተማሪዎቹ ወላጆች በአንጻሩ፣ የፎረሙን ውሳኔ እንደሚቀበሉት ተናግረዋል ሢል የአሜሪካ ድምፅ ነው የዘገበው።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.4K views03:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-05 07:22:53
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 66.96 በመቶዎቹ 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸው ተገለፀ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ በማኅበራዊ ገፁ ባወጣው መልዕክት እንደገፀው ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 73.09% በተፈጥሮ ሳይንስ እና 51.38% በማኅበራዊ ሳይንስ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ማግኘታቸውን አሳውቋል።

በክልሉ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን በድረ-ገጽ eaes.et ወይም በቴሌግራም ቦት @eaesbot ላይ መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች በአገልግሎቱ ድረ-ገጽ ላይ እንዲሁም በትግራይ ትምህርት ቢሮ በአካል በመቅረብ እስከ ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም ድረስ ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተመላክቷል።

በተያያዘ በክልሉ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 657 ከፍተኛው ውጤት ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል።

ሙሴ ኪዳነ የተባለ የቀላሚኖ ትምህርት ቤት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ከፍተኛውን ውጤት ያመጣው ተማሪ መሆኑን ለመመልከት ችለናል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.3K views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-04 07:42:31
የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተፈታኞች አቅም ማሻሻያ (Remedial Program) መከታተያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

@News_For_Student
@News_For_Student
14.5K views04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-03 18:23:18
የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆኗል

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስሥት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት ትምህርታቸውን ለምትከታተሉ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

የተመደባችሁቀትን ተቋም በተከታዮቹ አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል፦

Website: https://result.ethernet.edu.et/

Telegram bot: @moestudentbot

@News_For_Student
@News_For_Student
14.6K views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-03 18:22:34 የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል።

ከላይ በተራ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የRemedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 255 ያመጡ

የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 234 ያመጡ

የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 218 ያመጡ

የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 200 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 224 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 210 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 192 ያመጡ

ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 180 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 210 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 210 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 180 ያመጡ

አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 180 ያመጡ

ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ500 ነጥብ 150 ያመጡ

ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ500 ነጥብ 150 ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.6K views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-02 06:19:09 በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች #የዩኒቨርሲቲ_ምደባን አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ ማብራሪያ

የተማሪ ምደባ መስፈርቶች፡-

1. በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1,000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመጀመሪያ የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል።

2. የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

3. የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የቅበላ አቅም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ተማሪዎች 46 ዩኒቨርሲቲዎች ለምርጫ ቀርበውላቸዋል፡፡

4. የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ የትምህርት ፕሮግራሞችና የተመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራም መሰረት ያደረገ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

5. በተቋማት የጾታ ተዋፅኦን ለመጠበቅ በሚኖረው የምደባ ስርዓት የጾታ ተዋፅኦና ሚዛን እንዲጠበቅ ተደርጓል።

6. የምደባ ስርዓቱ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚመደቡ ተማሪዎችን ተዋጽኦ በጠበቀ መልኩ እንዲሆን ያግዛል፡፡

7. የምደባ ስርዓቱ ተማሪዎች ያስመዘገቡትን ውጤት ታሳቢ ያረገ ሲሆን ይህም ተመሳሳይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች አንድ ላይ እንዳይመደቡ በማድረግ የተለያየ ችሎታና ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎችን ቀላቅሎ ለማስተማር ያግዛል፡፡

8. የምደባ ስርዓቱ እንደ ወሊድ ያሉ ልዩ ሁኔታዎችን ያማከለ ነው፡፡ በመሆኑም በመሰል ሁኔታ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመቀጠል የሚቸገሩ ከሆነ ትክክለኛ ለውጥና ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡

9. በምደባ ወቅት የጤና ችግር ኖሮባቸው ትክክለኛ የሕክምና ማስረጃ ላላቸው ተማሪዎች ምደባው በተለየ መልኩ ሊታይ ይችላል፡፡

10. ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትዮች ካሉ የምደባ ስርዓቱ ከፍተኛ ነጥብ ያገኘው/ችው ተማሪ ከተመደበበት/ችበት የትምህርት ተቋም ቀሪው መንትያ ደግሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቀጥታ ይመድባል።

11. የምደባ ሲስተሙ የአካል ችግር ላለባቸው ተማሪዎች እኩል ዕድሎችን የሚሰጥ ሲሆን ልዩ ፍላጎቶቻቸውን እና ለምደባ መስፈርቶቻቸውን ግምትውስጥ በማስገባት የሚሰራ ይሆናል።

@News_For_Student
@News_For_Student
12.9K views03:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-01 06:59:00
የ2023 የታዳጊ ሳይንቲስቶች ሽልማት አሸናፊ የሆነው የ14 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ሔማን በቀለ 25,000 ዶላር ተበረከተለት።

በአሜሪካ ቨርጂንያ ነዋሪ የሆነው ታዳጊ ሔማን ሽልማቱን ያገኘው የቆዳ ካንሰርን ለማከም የሚያስችል ሳሙና በመፍጠሩ ነው።

ሳሙናው በአነስተኛ ዋጋ ($.50) ለገበያ የሚቀርብ መሆኑ ተመልክቷል።

"ታዳጊዎች በዓለም ላይ መልካም ተፅዕኖ መፍጠር እንደሚችሉ አምናለሁ" የሚለው የዘጠነኛ ክፍል ተማሪው ሔማን፤ ለባዮሎጂ እና ቴክኖሎጂ ትምህርት አይነቶች ሁሌም ልዩ ፍላጎት እንደነበረው ይገልፃል።

ውድድሩ የፈጠራ ሃሳቡን ለማውጣትና ውጤታማ እንዲሆን ጥሩ አጋጣሚ እንደፈጠረለት ገልጿል።

ላለፉት አራት ወራት በውድድሩ ለመጨረሻ ዙር ከደረሱ ሌሎች ዘጠኝ ተወዳዳሪዎች ጋር America’s Top Young Scientist ለመባል ብርቱ ፉክክን ሲያደርግ ቆይቷል።

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የፈጠራ ውጤቱን የበለጠ በማበልፀግና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት በማቋቋም ሳሙናውን ለሚፈልጉ ሰዎች በአነስተኛ ዋጋ ለማቅረብ እንደሚፈልግ ተናግሯል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.7K views03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-31 08:22:54
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ትምህርት ዘመን የመደበኛ መርሐግብር #የነባር ሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 21 እና 22/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በሌላ በኩል በ2016 ዓ.ም በመደበኛ እና በተከታታይ መርሐግብር በሁለተኛ ዲግሪ ለመማር አመልክታችሁ የብሔራዊ መግቢያ ፈተና (GAT) ፈተና ያለፋችሁ፥ የውጤታችሁን ማስረጃ በመያዝ ከጥቅምት 19 እስከ 21/2016 ዓ.ም በየትምህርት ክፍላችሁ እንድታመለክቱ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክቶች ከላይ ተያይዘዋል።)

@News_For_Student
@News_For_Student
14.8K views05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-30 06:47:00
#SamaraUniversity

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የ2016 የትምህርት ዘመን የነባር መደበኛ ተማሪዎች (የ2ኛ ዓመት 2ኛ ሴሚስተር እና ከ3ኛ ዓመት ጀምሮ የሆኑ የ1ኛ ሴሚስተር) ምዝገባ የሚካሔደው ጥቅምት 28 እስከ 29/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በቅጣት ለመመዝገብ ➧
ጥቅምት 30/2016 ዓ.ም

ትምህርት የሚጀመረው ➧
ኅዳር 03/2016 ዓ.ም

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@News_For_Student
@News_For_Student
13.0K views03:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-29 07:44:27
በ2016 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ለመከታተል ተመዝግባችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን የመግቢያ ፈተና ማለፋችሁን የሚገልጽ መረጃ በመያዝ ከጥቅምት 19 እስከ 23/2016 ዓ.ም ምዝገባ እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የ2ኛ ዲግሪ አመልካቾች የመጀመሪያ ዲግሪ ፤ የ3ኛ ዲግሪ አመልካቾች የመጀመሪያ እና የ2ኛ ዲግሪ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት በፖስታ ሳጥን ቁ. 21 ወይም በኢሜይል አድራሻዎች official@amu.edu.et / our@amu.edu.et በኩል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማስላክ ይጠበቅባችኋል።

@News_For_Student
@News_For_Student
14.7K views04:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ